top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የሰው ህሊናግፍና ቅሌት ያዘቦት ወግ በሆነበት በዚህ ዘመን “የሰው ህሊና” የት ገባ ብለህ ሳትጠይቅ ያደርክበት ቀን አለ? በርግጥ ህሊና የሚባል ነገር ራሱ ይኖራል? አንድን እሥረኛ ሽንት ቤት እንዳይሄድ በመከልከል የሚቀጣ የወህኒ ጠባቂ ባለበት አገር ውስጥ የህሊናን መኖር ብጠራጠር ይፈረድብኛል?በሀዲስ አለማየሁ “የልምዣት” ውስጥ ፈረደ መንፈቁና አዝማሪው ውቤ በግጥም የተሟገቱት ትዝ ይለኛል። አቶ ፈረደ በእግዜርና በህሊና ፍርድ ተስፋ የሚያደርጉ ሊቅ ናቸው። እንዲህ ይላሉ፤

እግዜር ሰውን ፈጥሮ- የውቀትን እስትንፋስ- እፍ ሲል ባፍንጫው ህግን ሲሠራለት- ምስክር ይሆን ዘንድ – ለኋላው መቀጫው ድሮውን ተናግሯል- በምጻት መሆኑን- የሱ ፍርድ መስጫው እስከ ምጽአት ድረስ- እንደራሴ አድርጎ- ሊፈርድ የወከለው አምላካዊ ባህርይው- ከፍጥረት ለይቶ- ለሰው ያካፈለው እውነተኛ ዳኛ አድልኦ የሌለው ባንሰማ ነው እንጂ- ህሊና ነበረ- በውስጣችን ያለው።

አዝማሪው ውቤ ያቶ ፈረደ ሀሳብ አልተዋጠለትም ፤ እንዲህ ሲል ይመልሳል ፤

አይ አቶ ፈረደ- ብልህ ናቸው ስንል- ለካስ ሞኝ ናቸው ውሸትና ስርቆት- መግደልና ቅምያ- የሆነ ኑሯቸው ደጋግመው ደጋግመው- የተመላለሱ በወንጀል ሥራቸው ገና ድሮ ድሮ- ታሞ ተሰቃይቶ – ሞቶ ህሊናቸው የነበረበቱ- ቦታው እንኳ ፈርሶ- ጠፍቶ ከውስጣቸው ከወዴት መጥቶ ነው- ወዴትስ ሆኖ ነው- የሚፈርድባቸው? እንግዲያስ እግዚአብሄር- ከህሊና በቀር- ምን ከንቱ ፈጠረ ወይ ከሁሉ አልጠፋ- ወይ ከሁሉ አልኖረ ታዛዦችን ሁሉ – በጸጸት ሠንሠለት- አሥሮ ያስቸገረ ለማይታዘዙት- የግፍ መፈጸምያ – አድርጎ ያኖረ ይልቅ ከንቱ አንድከም – የትም አያደርሰን -ይህ ሁል ፍልስፍና እንተወው ግዴለም! ድሃ በራብ ይሙት! ሀብታምም በብስና ለበዳይ ይፈረድ! ተበዳይም ይካስ ! ይቀጣ እንደገና ! መቸም ያለም ሥራት- እብድ እንዳደራው ድር -ውትብትብ ነውና።

የትኛው ሀሳብ ወደ ሀቁ ይቀርባል? ፍርድዎን ከምክንያቱ ጋር እንዲሰጡ ጋብዤዎታለሁ።


14 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page