top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የልብ በሽታን ለመከላከል (ቅድመ መከላከል)



  • በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ

እንደ ስንዴ፣ሲሪያል፣ ፍራፍሬ፣አትክልት እና አጃን መመገብ ከኮሌስትሮል ወደ ሰውነታችን እንዳይወስድ ማድረግ አቅም አለው

  • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

እንቅስቃሴን ማድረግ ለድንገተኛ የልብ ሕመም ተጋላጭነትን ይቀንሳል በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ እንቅስቃሴ ያድርጉ

  • ለሰውንት ተስማሚ የሆኑ የስብ ዓይነቶችን ምግቦች መመገብ

ይህም ማለት ከስጋ እና ጮማ ከበዛባቸው ምግቦች ይልቅ እንደ አሳ፣ኦቾሎኒ፣እና አቮካዶ የመሳሰሉትን መመገብ

  • ሲጋራ ማጤስን ማቆም

ሲጋራን በመደበኛ ሁኔታ የሚያጨሱ ከሆነ እራስዎን ለድንገተኛ የልብ ሕመም በከፍተኛ ሁኔታ ይዳርጋል

  • የሚወስዱትን የጨው መጠን መቀነስ

ጨውን መመገብ የሚያዘወትሩ ከሆነ የደም ግፊትዎን እንዲጨምር ያደርጋሉ፡፡ስለዚህ የሚመገቡትን የጨው መጠን ይቆጣጠሩ፣

ጭንቀትን መቀነስ

ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት ካለብዎ ራስዎን ለአደጋ እየጣሉ ስለሆነ ለመቀነስ ይሞክሩ

  • የስኳር መጠንዎን መቆጣጠር

የስኳር ሕመም ለልብ ሕመም በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጋልጥ ስለሆነ በሚገባ ይቆጣጠሩ

  • የደም ግፊት መጠንዎን በሚገባ መቆጣጠር

የደም ግፊት ለልብ ሕመም ተጋላጭነትን ስለሚጨምር በሚገባ መቆጣጠር ይኖርብዎታል፡፡ መድኃኒት የሚወስዱም ከሆነ በሐኪምዎ ትዕዛዝ መሠረት ይተግበሩ

  • የአልኮል መጠጥ ማዘውተር

አልኮልን በአብዛኛው የሚጠጡ ከሆነ እራስዎን ለደም ግፊት መጨመር ያጋልጣሉ ይህም በተዘዋዋሪ ለልብ ሕመም ይዳርግዎታል

እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ!

ጤና ይስጥልኝ

(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር)


20 views0 comments
bottom of page