የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
የተካደ ትውልድ

የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፤ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ የማይገላግለው
የተካደ ትውልድ ፤
አብዝቶ የጾመ፤ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፤ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ ፤ የተወለደ’ ለት አምባሩ ካቴና፤ ማተቡ ሠንሠለት፡፡ ምቾትን የማያውቅ ፤ ረፍት የተቀማ አልጋው ያጋም እሾህ፤ ምኝታው የሣማ
የተካደ ትውልድ፤
ሞቶ እንኳ ሬሳው፤ አይላላለት ቀንበር በዘብ እጅ ተገድሎ፤ በሹም የሚቀበር ከጡት አስጥል በላይ፤ ኑሮ የመረረው እንዳይሄድ፤ ጎዳናው፤ የተደናገረው ድል ያልሰመረለት ፤ ትግል ሳይቸግረው
የተካደ ትውልድ በሥጋ በነፍሱ በቀልቡ በገላው ኧረ ምንድን ይሆን ፤ ምንድን ይሆን መላው?