የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
የአፍንጫ አለርጂ(አለርጂክ ሪሄናይትስ/ሄይ ፊቨር)

ዛሬ በአፍንጫ አለርጂ ህመም ላይ ምክሮች እንሰጥዎታለን፡፡ ስለአፍንጫ አለርጂ ህመምም ይሁን ስለሌላ የጤና ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 8896 ሃሎ ዶክተር ላይ በመደወል በቂ ልምድና ሙያ ያላቸዉን ሀኪሞቻችንን ያማክሩ፡፡ እርስዎን ለማማከር ሁሌም ዝግጁ ናቸዉ፡፡
የአፍንጫ አለርጂ/ አለርጂክ ሪሄናይትስ እንደ የንፍጥ መዝረክረክ፣ የአይን መብላት/ማሳከክ፣ የአፍንጫ ማፈን/መጠቅጠቅ ማስነጠስንና የሳይነስ ቦታዎች ላይ መክበድ የመሰሳሉትን ጉንፋን መሰል ምልክቶች የሚያመጣ የህመም አይነት ነዉ፡፡ ይህ ህመም እንደ ጉንፋን በቫይረስ ምክንያቶች የሚመጣ ሳይሆን ለተለያዩ አለርጂን ሊያመጡ በሚችሉ በቤት ዉስጥና ከቤት ዉጪ ያሉ እንደ ፖለን፣ አቧራ፣ ቡናኝና የቤት ውስጥ እንስሳት አይነምድር ላሉ ነገሮች በምንጋለጥበት ወቅት ሰዉነታችን የሚያሳያዉ ያልተገባ ምላሽ/ሬስፖንስ ( allergic response) በሚኖርበት ወቅት ነዉ፡፡ የአፍንጫ አለርጂ ደስተኛ እንደይሆኑ ያደርጋል፣ ስራዎትን፣ ትምህርትዎንም ይሁን እረፍትዎን ያዉካል፡፡
የህመሙ ምልክቶች የአፍንጫ አለርጂ የህመም ምልክቶች አለርጂን ሊያስነሱ ለሚችሉ ነገሮች ሲጋለጡ ወዲያዉኑ የሚመጡ ሲሆን የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡- • የንፍጥ/የአፍንጫ ፈሳሽ መዝረክረክና የአፍንጫ መዘጋት/መጠቅጠቅ መኖር • የአይን ማልቀስ ወይም መብላት/ማሳከክ መኖር • ማስነጠስ • ሳል • የአፍንጫ ማሳከክ፣ የጉሮሮ ወይም ላንቃ መብላት መኖር • የሳይነስ ቦታዎች መወጠርና ህመም መኖር • ከአይን ስር ያለዉ ቦታ ማበጥና ቀለም መቀየር( Swollen, blue-colored skin under the eyes) • የጣዕምና ሽታ ማሽተት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
የአመቱ ወቅትና አለርጂ የአፍንጫ አለርጂ የሚነሳበት/የሚባባስበት ወቅት በአመት ዉስጥ የሚለያይ ሲሆን በተለይ ዛፎች፣ ሳርና የተለያዩ አበቦች በሚያብቡት ወቅት ይብሳል፡፡ በቤትዎ ዉስጥ ያሉና አለርጂን ሊያስነሱ የሚችሉ እንደ የምንጣፍም ይሁን ከሌላ ነገሮች የሚነሱ አቧራና ቡናኝ፣ በረሮ፣ ሻጋት፣ የቤት እንስሳት አይነምድር ሁሌ ካለ አመቱን በሙሉ የህመሙ ምልክቶች ላይጠፋ ይችለል/ሊኖሮት ይችላል፡፡ብዙ ሰዎች የአለርጂ ምልክቶቹ አመቱን በሙሉ ያላቸዉ ቢሆንም በተወሰኑ የአመቱ ወቅቶች ግን ሊባባሱ ይችላሉ፡፡
ዕድሜና አለርጂ የአፍንጫ አለርጂ በየትኛዉም የዕድሜ ክልል የሚከሰት ቢሆንም ብዙዉን ጊዜ ግን በህፃንነትና በወጣትነት ወቅት ይከሰታል፡፡የአፍንጫ አለርጂ ዕድሜዎ በሚጨምርበት ወቅት ምልክቶቹ እቀነሱ ይመጣሉ፡፡
የህክምና ባለሙያዎን ማማከር ያለብዎ መቼ ነዉ • የህመሙ ምልክቶች ቀጣይነት ያለዉ ከሆነና የሚያሳስቦት ከሆነ • የአለርጂ መድሃኒትዎ እየሰራ ካልሆነ • መድሃኒቶቹ እየሰራ ቢሆንም የጎንዮሽ ጉዳቱ ካስቸገረዎ • አለርጂዉን ሊያባብሱ የሚችሉ እንደ አስም፣የአፍንጫ ዉስጥ ዕጢዎች(ናዛል ፖሊፕ)፣ተደጋጋሚ የሳይነስ ኢንፌክሽን የመሳሰሉት ሲከሰቱ
የአፍንጫ አለርጂ ምክንያቶች ወቅታዊ የአፍንጫ አለርጂን የሚቀሰቅሱ ነገሮች • የዛፍ ሽታዎች/ፖለን • የሳር ሽታ/ፖለን • የአበባ/አረም ሽታዎች/ፖለን • በሞቃታማ ወቅት የአፍንጫ አለርጂን የሚያባብሱ ከሻጋታና ከፈንገስ የሚነሱ ፖለኖች አመቱን በሙሉ ሊከሰቱ የሚችሉ አለርጂ ምክንያቶች • አቧራ፣ተዋሲያን( mites)፣ወይም በረሮዎች • የቤት ዉስጥ እንስሳትና አእዋፋት አይነምድር(የዉሻ፣ድመት፣ወፍ) • በቤትና ከቤት ዉጪ ከፈንገስና ሻጋታ የሚነሱ ቡናኞች(ስፖርስ) ናቸዉ፡፡
ለአፍንጫ አለርጂ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች( Risk factors) • አስም ወይም ሌላ የአለርጂ ህመም ካለዎ • በቤተሰብዎ ዉስጥ መሰል ህመም ካለ(አስም ወይም ሌላ የአለርጂ ህመም ካለ) • የሚሰሩበት ወይም የሚኖሩበት አካባቢ ብዙዉን ጊዜ ለአለርጂኖች (አለርጂን ሊያስነሱ ለሚችሉ ነገሮች) የሚያጋልጥዎ ከሆነ
የአፍንጫ አለርጂ የጎንዮሽ ጉዳቶች • ለአስም መባባስ ምክንያት ይሆናል • የተስተካከለ/ጥራት ያለዉ አኗኗር እንዳይኖሮት ሊያደርጎት ይችላል • ለሳይነስ ኢንፌክሽን መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል • በልጆች ላይ ለጆሮ ኢንፌክሽን መከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ለአፍንጫ አለርጂ ሊደረግ የሚችል ህክምና ለአፍንጫ አለርጂ ሊደረግ ከሚችሉ ህክምናዎች ዋናዉ ለአለርጂ ሊያጋልጦት ከሚችሉ ነገሮች እራስን መከላከል መቻል ነዉ፡፡ነገር ግን ሁልጊዜ እራስን ተከላክሎ መቆየት ስለማይቻል መድሃኒቶች በተጨማሪ ሊያስፈልጎት ይችላሉ፡፡ የአፍንጫ አለርጂዎ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ካልሆነ ያለሃኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱና ህመምዎን ሊያቃልሉ የሚችሉ መድሃኒቶችን መጠቀም ይችላሉ፡፡
መድሃኒቶች • ናዛል ኮርቲኮስቴሮይድ፡-ይህ በሚነፋ መልክ ያለ መድሃኒት ሲሆን የአፍንጫ ዉስጥ መቆጣትን፣ማሳከክንና መዝረከረክን ይቀንሳል፡፡ይህ መድሃኒት ለረጅም ጊዜ ሊሰጥ የሚችልና ለብዙ ሰዎች ህመሙን ለማሻሻል የሚረዳ ነዉ፡፡ • አንታይ-ሂስታሚን፡-.አንታይ ሂስታሚኖች በአብዛኛዉ በሚዋጥ መልክ ያለ ሲሆን በሚነፋና በጠብታ መልክም አሉ፡፡አንታይሂስታሚን ማስነጠስን፣ማሳከክን ፣የአፍንጫ መዝረክረክን ያሻሽላል፡፡በዚህ ምድብ ከሚመደቡት ውስጥ ዳይፌንሃይድራሚን፣ሎራቲዲን፣ሲትሪዝን የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡ • ዲኮንጀስታንት፡- እነዚህም ፌኒልኤፍሪንና ኦክሲይሜታዞሊን የመሳሰሉትን የያዘ ሲሆን በሚነፋ መልኩ ያሉ ናቸዉ፡፡ • ክሮሞልይን ሶድየም፡- ይህ በሚነፋና በአይን ጠብታ መልክ ያለ መድሃኒት ሲሆን በቀን ዉስጥ በተደጋጋሚ ሊወሰድ የሚችልና የህመም ምልክቶችን ሊቀንስ የሚችል መድሃኒት ነዉ፡፡ • በሚዋጥ መልኩ ያሉ ኮርቲኮስቴሮይዶች፡- ለአጭር ጊዜ ቢወሰዱ ከፍ ያለ የአፍንጫ አለርጂን ሊያስታግሱ ይችላሉ፡፡
ሌሎች ህክምናዎች • አለርጂ ሾት(ኢሚኖቴራፒ)፡- የሚወስዱት መድሃኒቶች ህመሙን ሊያስታግስልዎ ካልቻሉ የህክምና ባለሙያዎ ለአለርጂኖች ቢጋለጡም እንኳ ተጋላጭነትዎን ለመቀነስ አለርጂ ሾት እንዲወስዱ ሊያዝሎት ይችላል፡፡ • አፍንጫን ማፅዳት/ማጠብ( Rinsing your sinuses)፡- አፍንጫዎን ፈልቶ በቀዘቀዘ ዉሃ ወይም በተጣራ ዉሃ ዉስጡን ማጠብ የአፍንጫ መጠቅጠቅን/ማፈንን ይቀንሳል፡፡ ማጠብ ንፍጥንና አለርጂኖቹን ያጥባቸዋል፡፡ከፋርማሲ ስክዊዝ ቦትል የሚባልና ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ትንሽዬ የፕላስቲክ እቃ በመግዛት መጠቀም ይችላሉ፡፡
የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥና የቤት ዉስጥ ህክምና የአፍንጫ አለርጂን ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮችን ሙሉ በሙሉ መከላከል ባይቻልም ተጋላጭነትዎን በመቀነስ የህመም ምልክቶቹን መቀነስ ይቻላል፡፡ለእርስዎ የትኞቹ ነገሮች ሊያስነሳብዎ/ሊያባብስብዎ እንደሚችል/ሉና እነሱን እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ለማወቅ ይረዳዎታል፡፡ ፖለኖችንና ሻጋታዎች( Pollen or molds) ለመከላከል • በአበባ ወቅት በርንና መስኮትን መዝጋት • የታጠቡ ልብሶችን ከቤት ዉጪ ያለማስጣት፡- ፖለኖች ታጥቦ በተሰጣዉ ልብስ ላይ በመጣበቅ ልብሱ በሚለበስበት ወቅት አለርጂ ሊያመጡ ይችላሉና • የሚቻል ከሆነ የአየር መፅጃ በመኪናዎ ዉስጥ መጠቀም( air conditioning) • ጠዋት/ማለዳ አለርጂን የሚቀሰቅሱ ፖለኖች በብዛት በሚገኙበት ወቅት ስለሆነ ከቤት ዉጪ ስራ ያለመስራት/ ከቤት ያለመዉጣት • በጣም ነፋሻና ደረቅ አየር በሚበዛበት ሰዓት ከቤት ያለመዉጣት • በአትክልት/ጋርደን አካባቢ ስራ የሚሰሩ ከሆነ የአፍንጫ ማስክ መጠቀም(አፍንጫን መሸፈን) ቡናኝን ለመከላከል • የመተኛ ፍራሽንና ትራስን አለርጂኖችን በሚከላከል ነገር መሸፈን (Use allergy-proof covers) • ብርድልብስንና አንሶላን በ54 ዲግሪ ሴንቲግራድ ወይም 131 ዲግሪ ፋራናይት የሞቀ ዉሃ ዉስጥ ማጠብ • በሳምንት አንዴ ምንጣፎችን በቫኪዩም ክሊነር ማፅዳት በረሮዎች • በረሮዎች ሊገቡበትና ሊራቡበት የሚችሉ ቀዳዳዎችን መድፈን • የሚያንጠባጥቡ/የሚያፈሱ ቧንቧዎችን መጠገን • የወዳደቁ የምግብ ተርፍራፊዎችን ከዕቃና ከወለል ላይ ማፅዳት • ምግቦችን በሚከደን እቃ ዉስጥ ማስቀመጥ • የበረሮ ማጥፊያ መድሃኒቶችን መጠቀም የቤት እንስሳትና አይነምድራቸዉ • ከተቻለ የቤት እንስሳት በቤት ዉስጥ እንዳይኖሩ ማድረግ • የቤት እንስሳትን በሳምንት አንዴ ማጠብ • የቤት ዉስጥ እንስሳትን(ድመት፣ዉሻ) መኝታ ቤት ዉስጥ እንዳይገቡ ማድረግ
የአፍንጫ አለርጂን እንዴት መከላከል ይቻላል? የአፍንጫ አለርጂን ለመከላከል ይህ ነዉ የሚባል የተረጋገጠ የመከላከያ ዘዴ ባይኖርም ሊደረጉ የሚችሉ ጥንቃቄዎች አሉ፡፡ እነዚህም ለአፍንጫ አለርጂን ሊያስነሳብዎ/ሊያባብስብዎ ለሚችሉ ነገሮች ተጋላጭነትዎን መቀነስና ለአለርጂኖች እንደሚጋለጡ የሚያዉቁ ከሆነ ከመጋለጥዎ በፊት የአለርጂ መድሃኒቶችን አስቀድሞ መዉሰድ ይገባል።
ምንጭ - የጤና ማህደር ድረ ገ