top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

‘‘የሰው ዓመል ዘጠኝ ፣ አንዱን ለኔ ስጠኝ’’ እንደምናችሁ? ዘሬ እንድ ትልቅ ጥያቄ አለኝ፡፡ ሳታረቡ ትረባላችሁ እንዴ?

Updated: Jun 9, 2019



አንድ ጎረቤቴ እጅ አንስቶ ሰላምታ የማቅረብን ሚስጥር አስረዳኝ፡፡ አመስግኜዋለሁ፡፡ ለምሳሌ ያህል ጭንቄሶን እጄን አንስቼ ሰላም ብለው ፣ ‘‘ ጭንቄሶ ፣ እኔ ካንተ ጋር ሰላም ነኝ ፡፡ ጠብም ይሁን ችግር የለብኝም ’’ ፣ ማለት ነው ፡፡

ጠብ አለን እንዴ ፣ እስከዛሬ?

‘‘ሂድ እንግዲህ! ’’ ፣ ይላል -ጭንቄሶ፡፡

በየዕለቱ ስንቶቻችንን ነን እኔ ካንተ ጋር ጠብ የለኝም ሰላምታን የምንጠቀምበት ?

በስራ አጋጣሚ ወደ አርብቷደር መንደሮች ተመላልሻለሁ፡፡ አንድ ጊዜ የሀመር ተወላጅ ከሆነ ፣ ኦይታ ከሚባል አርብቷደር ጋር ተጨዋውተን ነበር ፡፡

ኦይታን እንዲህ ስል ጠየቅኩት ፡- ‘‘ ኦይታ ፣ ፍየሎችህ እጅግ ብዙ ናቸው ፡፡ ከብዛታቸው በላይ የቀለማቸው መለያየት ፡፡ ፍየሎችህን ውሃ ልታጠጣቸው ወንዝ ወረድክ እንበል ፡፡ ከሌላ መንጋ ጋር ቢቀላቀሉብህ ምን ታደርጋለህ?’’

‘‘ ለምሳሌ ያህል አንተ ለኔ ደብዳቤ ፃፍክልኝ ፡፡ አድርሱለት ብለህ ለሰው ሰጠህ ፡፡ ሰውየው ደብዳቤውን በሌላ ቀይሮ ሰጠኝ ፡፡ የሰጠኝን ደብዳቤ አንተን አግኝቼህ ባሳይህ ያንተ መሆን አለመሆኑን ለይተህ ለማወቅ ትቸገራለህ?’’

‘‘ በፍፁም! ’’ ፣ መለስኩለት፡፡

“ የኔም ፍየሎች ነገር እንደዚያው ነው ፡፡ ላንተ እይታይህ እንጂ እላያቸው ላይ የኔ አሻራ አርፎባቸዋል ፡፡ ምልክት አላቸው ” ፣ አለኝ፡፡

ይገርማል!

በነገራችን ላይ አርብቷደር መንደር ያሉ ህፃናትን የማየት ዕድል አጋጥሟችሁ ከሆነ፡፡ ድንቡሽ ያሉ ፡፡ ከውፍረት ጋር ሚንከባለሉ፡፡ እንደ ጡንቻ ከማሪ ስፖርተኛ ክምር ያሉ፡፡

‘‘ ሂድ እንግዲህ ይላል ’’ -ጭንቄሶ፡፡

ወተት ነው ቁርስ እራት ምሳቸው ፡፡ በርግጥ የኦሞ ወንዝ የቆሻሻ ድፍድፍ ነው ፡፡ ድፍድፉን የሚያጣራ ‘‘ጉሉፍ’’ ፣ የሚባል ተክል ስር አለ፡፡ በጉሉፍ ተጣርቶ ፣ የተጣራውን ውሃ ይጠጣሉ፡፡

አቤት ያጋር ውሃ ወሬ!! ‘‘ጉሉፍ’’ ችግር አለበት እያለች ማስወራት ጀምራለች አሉ፡፡

አንዳንድ ያገራችን ከተሞች ውስጥ ህፃናት በወተት ፋንታ ቤንዚን ይጠጣሉ፡፡ ጉድኮ ነው!! ህፃናቱ በወተት ፋንታ ቤንዚን የሚጠጡት እኮ ሳናረባ ተራብተን ነው፡፡ ስራ ሳንሰራ ውለን እየገባን በሚስቶቻችን ላይ ስራ እያበዛን ፡፡ ጉደኮ ነው!!

ሀያ ኮጁ የሚባል አንድ የዜን መምህር የሆነ ሰው ነበር ፡፡ አዛውንቱ መምህር እድሜው ስራን የሚፈቅድ አልነበረም፡፡ እርጅናውን ምክንያት አርገው ፣ ተማሪዎቹ ከርሱ ዞር ብለው ተመካከሩ፡፡

እንዲህ ብለው፡-

‘‘ መምህራችን በዚህ ዕድሜው የአትክልት ቦታዎችን ሲቆፍር መታየቱ ተገቢ አይደለም ፡፡ እርፍት ማድረግ አለበት ፡፡ ’’ ፣ አሉና የስራ መሳሪያዎቹን ደበቁበት ፡፡

ሀያ ኮጁ የስራ መሳሪዎቹን ሲያጣ ምግብ መብላት አቆመ፡፡ ሁለት ቀን ምንም ሳይቀምስ፡፡ ተማሪዎቹ ግራ ገባቸው ፡፡

‘‘ይሄ ሰውዬ ይሞትብናል ፡፡ ምግብ አልበላም ያለው ይስራ መሳሪያዎቹን ስለደበቅንበት ነው’’ ፣ አሉና መሳሪያዎቹን መለሱለት ፡፡

በማግስቱ ከጠዋት ጀምሮ በአትክልት መደቦቹ ላይ ከወትሮው በበለጠ ሲሰራ አመሸ፡፡

ማታ በዕራት ሰዓት ፣ በተማሪዎቹ እንደተከበበ ነበር ፡፡ ለርሱም ለተማሪዎቹም የተሰናዳው ዕራት ቀርቦ ፣ ተማሪዎቹ የሀያ ኮጁን ማዕዱን ባርኮ መጀመር እየተጠባበቁ ሳለ ፣ ሀያ ኮጁ ‘‘ሰራ የለም ፤ ምግብ የለም! ’’ ፣ አላቸውና ለሶስት ቀናት ያቆመውን ምግብ መመገብ ጀመረ፡፡

ትልቅ ሰው!!!- ሀያ ኮጁ፡፡

ስራ ሰርቶ ፣ አርብቶ ነው መውለድ!! መብላትም እንዲሁ፡፡ እኛ ግን ሳንሰራ እየረባን፣ በወተት ፋንታ ቤንዚን? እባካችሁ ሚስቶች ፣ ‘‘ ምግብ የለም፤ ዛሬ ማታ ስራ የለም ! ’’ ፣ በሉ እንጂ፡፡

‘‘ የሰው ዓመል ዘጠኝ ፣ አንዱን ለኔ ስጠኝ’’

ከወደዱት ሼር ያርጉት ፡፡


(በደራሲና ጋዜጠኛ ጌቱ ሻንቆ)

53 views0 comments
bottom of page