top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ግጥሎት



ቀጥሎ የምታነቡት ነገር በግጥምና በፀሎት ማሃል ያለ ነገር ነው። ግጥሎት ብየዋለሁትናንት በእንቅልፍና በንቃት ማሃል ሆኘ የመጣልኝ ነው። ወፍ እንዳገሩዋ ትጮሃለች! ነፍስ እንደዘመኑዋ ትፀልያለች! የፅሁፌ አላማ ራሴን እና ብጤዎቼን ለማዝናናት ብቻ እንደሆነ ይታወቅ!

አባት ሆይ ! እንሆ ዛሬ ተወለድሁ! ካለመኖር ወደ መኖር ተሰደድሁ። ፋኖቼን በመልካም እድል -ፋኖዎቼን በካራ ባርክልኝ ከእድሜየ ጨመር ከርጅናየ ቀነስ በተከዘች ልቤ ላይ ትንሽ ደስታ ነስነስ- አርግልኝ

አባትሆይ የናቶቼ አምላክ Wish me good luck የእለት እንጀራየ ደርሶኛል አሁን ደሞ ወጡን ላክ።

በጨለማ የጠፋሁ ልጅህን -በጄኔረተር ታግዘህ ፈልገኝ!! አህያ የነዳሁ ልጅህ- የግል ጄት ስነዳ ልገኝ። የመንፈቅ ኮቴን -ያመት ቦይኮቴን አትንፈገኝ!

አባት ሆይ በስተጎኔ ግራና ቀኝ ጣምራ ክንፎች ግጠምብኝ ወይም ለጄት በቂ በጄት ልቀቅብኝ።

ጌታሆይ እረኛየ ነው በለመለመ መስክ ያሳድረኛል። እኔ ግን በግ አይደለሁም ካንጋሮ ፍራሽ ያምረኛል።

አባት ሆይ !

ከፀጋየ ባጋራ የማውቀውን ባካፍል ከስድ ዘመን ተቃራኒ ቅኔና ወግ ብፈለፍል እንዴት ያቅራራብኛል ማንም አንደኛ ክፍል ጌታሆይ ጠላቴን አርበድብደው! ስንቁ እንደ ጥጥ ሸክም ይቅለል-ቆለጡ እንዳለሎ ይክበደው! አባት ሆይ ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ! ጨለምተኝነቴም አለቀ! በነገራችን ላይ በላይ ዘለቀ አማራ ነው ኦሮሞ አሁን ይህን ከዚህ ፀሎት ጋር ምን አገናኘው ደሞ?

አባት ሆይ ተመስገን! ተመስገን ተመስገን ደሳለኝ! እኔስ ያላንተ ማን አለኝ?!

እበላለሁ እሰባለሁ እወጣለሁ እገባለሁ እገባለሁ እወጣለሁ! ግን ከጭቆና መች አመልጣለሁ? እንኩዋስ በምድረ ጦቢያ እዚህ አመሪካ አገር የማርቲን ሉተር ሀውልት እንደ ማለዳ እንትን ቢገተር black lives don’t matter.

14 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page