top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ቀሳፊ ምርቃት



ሰማሁ ምርቃትሽን …. ከእናት አንጀትሽ ቁልቁል ሲዥጎደጎድ ታየኝ ምድረ መልዓክ … ብራና ዘርግቶ ቃልሽን ሊከትብ ትከሻሽ ላይ ሲያረግድ

በረካሁንልኝ …ከፍ ያርግህ በሰው ፊት … እድሜ ጥምቡን ይጣል ይቅና ማቱሳላ እርጅና እጁ ይዛል አካላትህ ይስላ ዝም !

እግርህን እንቅፋት ጎንህን ጋሬጣ ጤናህን ድቅስቃስ የመንደር ሽውታ አይንካብኝ ብለሽ የመረቅሽኝ ለታ

ዝም !

ዘርህ ዋርካ ይሁን ወንዝ ዳር ያበበ ታሪክህ ዘላለም ባደባባይ ይድመቅ እየተነበበ ደሆች ፊትክን አይተው በጥጋብ ይኑሩ ልጆጅህ በስምህ ለዘላለም ይኩሩ ብለሽ ስትመርቂኝ

ዝም !

ካ,ይንሽ የፍቅር እንባ ፊቴ እየረገፈ ለእልፍ ምርቃትሽ እንቢ አለኝ ልሳኔ ‹‹አሚንታን ›› ነጠፈ

ዝምታየ አይክፋሽ ክፉ ፍራቴ ነው ልሳኔን የዘጋው በምርቃትሽ ውስጥ የምርቃት መቅሰፍት ውስጤን እየወጋው

በክፉ የሚያይህን ጨለማ ያልብሰው ክፉ ተራማጁን እግሩን ያልመስምሰው ብለሽ አሚን ያልኩት ምርቃትሽ ያዘ በክፉ የሚያየኝ አይኑ ታወረና በጭፍን ሊፈጀኝ ጎራዴ መዘዘ የህሊና እግሮቹ የሰለሉ ጠላት ብረት ተመርኩዞ መንገዴ ላይ ቆመ አሚን ካለሽ አፌ ‹‹እግዚኦታ›› ተመመ !

ግዴለሽም እማ …

ጠላቴ አይኑ ይብራ ይግደለኝ እያየ ባቡሰጥ ብትሩ እኔን እየሳተ ወገን አሰቃየ ጥላቴ እግሩ ይስላ ይቅደመኝ ከሮጠ በለመሹ እግሮቹ መንገድ እየዘጋ ከዘመን ሩጫ ትውልድ ተቋረጠ !

ግዴለሽም እማ …..

ጥላቴን መርቂው አይኑ ፀሃይ ይሁን ቦግ ብሎ ይብራ ምናልባት ምናልባት እውነቱን ቢያሳየኝ ወይ እውነቴን አይቶ ለልጅሽ ቢራራ ጥላቴ ዓይኑ ይብራ … ያኔ ትሰሚያለሽ ድል ካረገ ልሳን የሃቅን ፉከራ !

እንጅ ባንድ ምድር ልጅ እየመረቁ ‹‹ጠላትን›› ቢገፉ ርግማን ያወረው በደፈናው ጠላት ለልጅሽ ነው ደፉ !

አሚን ?


20 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page