• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ነጋ


የግዜር ስውር መዳፍ፣


ልክ እንደ ፓፒረስ፣እንደ ግብጦች መጣፍ ወይም እንደ ጥንቱ፤ ያባ ጅፋር ምንጣፍ ጨለማውን ስቦ፤ በወግ ሸበለለ ሰማይ፣የጠፈር ዓይን፤ ብርሃን ተኳለ ከዶሮ ጨኸት ውስጥ፤ አዲስ ጎህ ተወልዶ ፍጥረቱ በሞላ፤ ማርያም ማርያም አለ፤

ነጋ አልጋየን ሰብሬ አንሶላ ተርትሬ ባዲሱ ጉልበቴ በታደሰ አሞቴ ልኖር ተዘጋጀሁ እንደ ጣዝማ ቅንጣት፤ ከሚጣፍጥ ሞቴ ትንሳኤየን ዋጀሁ፡፡

ነጋ እንደ ምትሀተኛ፤ ተስፋ ሲያታልለኝ አዲሱ ማለዳ፤“ ዛሬን ሞክር ሲለኝ›› የዛሬው እጣየ ከትናንት ጣጣየ የሚለይ መሰለኝ፡፡


12 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean