top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ላንዲት ማስቲካ ሻጭ ህጻን



በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ ኣንጋጠሽ ወደ ላይ ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው:: ኣፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ መስኩ ከነጎርፉ ሰማይ ከነዶፉ ለጌቶች ተሽጦ ኣተር ነው እያሉ፤ ኣፈር ዘግኖ መፍጨት ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት ይህንን ማን ሰጦሽ ገና በልጅነት፤ ልጅነት ኣምልጦሽ፡፡ በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ በክራር ተማግሮ በቆመ ከተማ እምባሽ ቅኝት የለው ፤ለሰው ኣይሰማ፡ ጠዋት የፎከረ ፤ቀትር ላይ ሲረታ ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ትናንት የበረታ ኑሮን ያህል ሸክም፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡ ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡


37 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page