top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የማህተመ ጋንዲ ምርጥ አባባሎች



  • እንደሰው ልጅ ትልቅነታችን ያለው የአቶሚክ ዘመን ተረት ተረት እንደሚነግረን ዓለምን እንደገና ለመስራት በመቻላችን ላይ ሳይሆን ራሳችንን ዳግም ለመስራት ያለን ችሎታ ላይ ነው።

  • ማንም ሰው እኔ ሳልፈቅድለት ጉዳት ሊያደርስብኝ አይቻለውም።

  • የወደፊቱን ጊዜ አስቀድሜ ማየት አልሻም። የሚያሳስበኝ የአሁኑን ጊዜ መንከባከብ ነው። ቀጥሎ ስላለው ቅጽበት አምላክ ምንም ዓይነት ቁጥጥር አልሰጠኝም።

  • በራስ ጥበብ በጣም እርግጠኛ መሆን መልካም አይደለም። ጠንካሮች ሁሉ እንደሚደክሙ እና ጠቢባንም እንደሚሳሳቱ ማስተዋል ይጠቅማል።

  • በመጀመሪያ እነሱ ቸል ይሉሃል። ከዚያ ይስቁብሃል። ከዚያ ይፋለሙሃል። ከዚያ አንተ ታሸንፋለህ።

  • ደካሞች ይቅር ማለት አይቻላቸውም። ይቅር ባይነት የጠንካሮች ብቻ ባህሪይ ነው።

  • ከኩንታል ሙሉ ሰበካ ይልቅ አንዲት ኪሎ ድርጊት ትበልጣለች።

  • የሰዎችን መልካም ገጽታ ብቻ ነው የምመለከተው። እኔ ራሴ እንከን የለሽ ስላልሆንኩ የሌሎችን እንከን የምቆጥርበት ምክንያት የለኝም።

  • ደስታ ማለት የምታስበው፣ የምትናገረው እና የምታደርገው ሲስማሙ ማለት ነው።

  • የማያቋርጥ እድገት የተፈጥሮ ሕግ ነው።


111 views0 comments
bottom of page