top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የዶቢ እና የማረቆ ያላቻ ጋብቻ (ክፍል አንድ)



  • ዶቢ ማነው ?

ዶቢ የቤተ መስቃን አንዱ ቤተሰብ ሲሆን ልክ እንደ ሌላው የመስቃን አካል ከሰሜን ኢትዮጵያ በ13ተኛ ክፍለ ዘመን በመፍለስ አሁን ያለበት አካባቢ ሰፍሮ ይገኛል። የዶቢ ቤተ መስቃን እንደ ሌላው የመስቃን ቤተሰቦች ዝርያው ባለመባዛቱ የዶቢ የልጅ ልጆች በሰሜን ምእራብ መስቃን ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ሁለት የገጠር ቀበሌዎች ብቻ ሰፍረው ይገኛሉ። በሁለቱ ቀበሌዎች ሰፍሮ የሚገኘው የዶቢ ማህበረሰብ ህዝብ ብዛት ከአምስት ሺ እንደማይበልጥ ቀደምው በተደረጉት የህዝብና ቤተ ቆጠራዎች ለማረጋገጥ ተችሏል።

እንደ አካባቢው ታሪክ ጠገብ ሽማግሌዎችና የታሪክ ምሁራኑ ገለጻ ከሆነ በዙሪያው ከሚገኙት ከሌሎች የመስቃን ቤተሰቦች ጋር ያልተዋለደ ፣ ከሶዶ ቤተ ጉራጌ እንዲሁም ከሰባት ጉራጌ ያለተዋለደ ወይም ጥንት የነበረውን የአባት ዶቢ ወይም እናት ዶቢ ማንነት ብቻ የያዙ የዶቢ አካላት ከአምስት መቶ እንደ ማይበልጡ ይናገራሉ። ዶቢ የቤተ መስቃን አካል ነው። ዶቢ ከሶዶ ቤተ ጉራጌ ጋር በሰፊው ተዋልዷል። ዶቢ ከሰባተ ቤት ጉራጌ ጋር ተወልዷል። ዶቢ መስቃን ነው። መስቃን ደግሞ ጉራጌ ነው።

  • ዶቢ ወረዳ ለመመስረት የሚያበቁት መስፈርቶችን ያሟላልን ?

ዶቢ እላይ እንደተጠቀሰው በሰሜን ምእራብ መስቃን ወረዳ ተራራማ አካባቢዎች በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ብቻ ሰፍሮ የሚገኝ ነው:፡ ወደ ዶቢ ሁለት ቀበሌዎች ለመድረስ የቡታጅራ ከተማ ሳይረገጥ የሚታሰብ አይደለም። ወይም ሌላ መግቢያ የለውም። ከአካባቢው ጥበትና ተራራማነት የተነሳ የዶቢ ልጅ ለአቅም ትምህርት ደርሶ ትምህቱን ከጀመረ በዃላ ማንበብ ሲጀምር እንዲሁም ቁጥር መለየት ሲጀምር ጅምር ትምህረቱን በማቋረጥ እና አካባቢውን በመተው በዋነኝነት በአዲስ አበባና በሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ቀደም ብለው አካባቢውን ለቀው በሄዱ ቤተ ዘመዶች አማካኝነት በንግድ ስራ(በጫማ ንግድ ስራ) ይሰማራሉ።

ታዲያ ያ…ጨቅላው የዶቢ የከተማን ህይወት ሀ- ብሎ ይጀምራል። አብዛኞቹ ተሰደው የሄዱት የዶቢ ልጆች በቤ-ዘመድ የንግድ ማእከል ወይም ያ…ቤተ-ዘመድ በቅጥር የሚሰራበት የንግድ ማእከል ውስጥ ስለሚሰሩ ከምግብ ፣ ከልብስና ከመጠለያ በቀር የተለየ ክፍያ አይኖራቸውም። የአብዛኞቹ ልጆች ህይወት ቅርብ የሆነ የቤተሰብ ንግድ ማእከል ውስጥ ከሚሰሩት በቀር አስከፊ ነው። ታዲያ…እነዚህ በአሰከፊ የህይወት ሂደት ውስጥ ያለፉት ጨቅላዎች ግን የዛሬዎቹ ጎልማሳዎችና መሃይማን ባለሃብቶች ሃብትና ንብረት ያፈሩት ወይም ንበረታቸው በሙሉ የሚገኘው ከጉራጌ ክልል ውጭ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ነው።

ወያኔዎቹ ባስታቀፉን የዘር ፖለቲካ በሐገራችን ውስጥ ለአመታት ሰፍኖ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት በተለያዩ የሐገራችን ክልሎች ውስጥ ይኖር የነበሩ የዶቢ ባለሃብቶች ንበረታቸውን በማሸሽ ሰላምን መረጋጋት ያለባቸው ክልሎች ውስጥ ሲሰፍሩ በጣት የሚቆጠሩት ግን ቡታጀራው ውስጥ የንግድ ማእከል አቋቁመዋል። እነዚህ በጣት የሚቆጠሩት ቡታጅራ ከተማ ውስጥ የንግድ ማእከል ከማቋቋማቸው በቀር ዶቢ የእራሱ የሆነ ከተማ የለውም ። ዶቢ የእራሱ ከተማ ካለመኖሩ ባሻገር እንደ ማህበረሰብ ወይም ስብስብ በሰሜን ምእራብ መስቃን ወረዳ ውስጥ በሚገኙት ሁለት የገጠር ቀበሌ ውስጥ ብቻ ነው ሰፍረው ነው የሚገኙት ።

  • የዶቢና ማረቆ ያለ አቻ ጋብቻ እና ሚስጥሩ ? በሚቀጥለው ክፍል ይጠብቁን

“የመስቃን ግብት” ነኝ - ከቡታጅራ


96 views0 comments
bottom of page