top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ለተጎዱት ወገኖቻችን እንድረስላቸው


በዉጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን በቡታጅራና ኣካባቢዋ በመፈናቀል ለተጎዱት ወገኖቻችን እንድረስላቸው !


ሁላችንም በሶሻል ሚዲያዉና ቤተሰቦቻችን ጋር ስንደዉል የምንሰማው ኣሳማሚና ኣሳዛኝ የወገኖቻችን መፈናቀል ዛሬ ለኛም ማህበረሰብ ዞሮ ስለደረሰውና ይህንንም በጋራ ኣንድ ወጥ የሆነ ሃገራዊ የርዳታ ማስተባበሪያ በቅርቡ ቀን ኮሚቴ ኣዋቅረን ለመጀመር ግብዐቶች ኣውጥተን ለመንቀሳቀስ ቅድመ ሁኔታዎችን እየጨረስን ነው። ስልዚህ በኣሜሪካም በካናዳም በኣውሮፓ በኣረብ ሃገራት በእስራኤል በደቡብ ኣፍሪካ እንደዚሁም በኣውስትራሊያ ለምትኖሩ ሁሉ በቅርቡ ቀን ወገኖቻችንን የምንረዳበት ቀላል መንገድ በሶሻል ሚዲያና በሰፊው በሚደመጡ የመገናገኛ ኣውታሮች እናሳዉቃችሁለን።

ሃምሳ ሎሚ ለኣንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ ነው የሚሉት የሃገራችንን ብልህ ኣባባል የተቸገሩና በቡታጅራ ስታዲየም ግጭትን ሸሽተው የተጠለሉትን ወግኖቻችን በመድረስ ተግባራዊ እናድርግ።

በመስቃንኛ፣

ዉድ በዉጪ ትነብሮ ኧተሞቸኛና ጎባቢተኛ መቸም በሶሻል ሚዲያም ኸነ ገኝ ትትዴዉሎ በመስቃንና በማረቆ ግብት የሰላዪ ኣለወግባባ በህዝበና ያሰላኒ ወፍናቀል ኣንሰማሁ ኤመስረነ። ስለኸነም በሩቄ ኸነም ከንፈረና ተወምጠጥ ብንችልኔ ብንረዳኔዮ ኧዃ ታኔብው በቡታጅራ ስታዲዮም ይቡወሮይ ይሰጦይ ብቻ ቴኸን ቤተህኖ የፈረሰቦ ስላኖ ዠበርነም የዋቋቁም ይችሎ ኸማ በቁናዬ

ንስላኔኖ። ዚም ለዋሳካ በዚዬ በኣሜሪካ ንነብርነ ኮሚቴ ኣቁዋቁዋምነም እንመና ያቅመና ኧጀና ንዘርጋነ።

በስልጥኛ

በዉጪ ሊትነብሮም የጉታጂራና ኣካባቢከ የባድወልድቻው፣ ኣኩ በቁርብ ኣያም በማርቆና በመስቃን ኡመት ጉት የትኬሰተይ ኣልቲግባቦት ያመጠይ ሚካት በሶሻል ሚድያሚ ሂንኩም ጌ ቲትዴዉሉ የሰማሙኩ ተስፋ ኣኛው። ኣኩ ሂንኩ ከንፈር ተምጠጦት ኣለፍናኒ ለትመካይ ሰብ ለጂጆት ኣቱም ኢድል ሊትረክቡ በቁርብ ኣያም በሶሻል ሚዲያ ፈንድሬይዝ ላሶት ዚጊጂት ትልፌጅነ በሶሻል ሚዲያ በቂሮት ኣቱም የድርሻሙ ኣሱ።

በሶዶኛ/ክስታኔኛ

በውጪ ትነብርም በቡታጅራና ኣካባቢ የመጣም ያገርባዮች መቼም በሶሻል ሚዲያም ሆነ ገየት ትትዴዉልም በመስቃንና በማረቆ ግብት ችግር የሰማህም ይመስለነ። ስለዚህም በቁናየን ሆነም በሶሻል ሚዲያ ጎፈንድሚ እርዳታ የዋሰባስብ ኮሚቴ ቂረስነም በዜና ተክታተልም።

ፈጣሪ ኢትዮዽያንና በሃገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ የሚኖሩ ህዝቦችዋን ኣብዝቶ ይባርክ!

We Shall Overcome! The Best Days of Ethiopia is Yet to Come!


34 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page