top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

አቶ በቀለ አየለ መኩሪያ ማናቸው?



ዘር ለገበሬው ክልል ለአርብቶ ኣደሩ ሀገር ለሀገሬው!!! ጀግኖቻችንንና ታላላቅ ሰዎቻችን ለማድነቅ ከዚህ አለም እስኪያልፉ መጠበቁ ብልህነት አይደለም። እስኪ የቀድሞው የቡታጅራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ በቀል አየለ መኩሪያ ለቡታጅራ ከተማና ነዋሪዎችዋ ታላቅ ባለውለታነታቸው የምትስማሙ ፍቅራችንን እንግለፅላቸው። የእኔና ኣስተያየት ከተጠይቅሁኝ አጋነንከው አትበሉኝና ከጋሽ በቀለ በላይ ለዛች ከተማ ላቡን ያንጠፈጠፈ አል ብዬ አላምንም። ለከተማዋ እድገት ህዝቡን በማስተባበር ካበረከቱት በጥቂቱ ለአብነት ልጥቀስ። 1. የቡታጅራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጫካ ኣስመንጥሮ ማሰራት 2. እርሳቸው ዳሬክተር በነበሩበት ጊዜ የቡታጅራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በትምህርት ኣሰጣጥ ጥራት እና በተማሪዎች ዉጤት ለሰባት ተከታታይ አመታት ከሸዋ ክፍለ ሃገር ኣንደኛና በሃገር ኣቀፍም ደርጃ ከፍተኛ ዉጤትን ማስመዝገብ 3. ደርግ ሲወድቅ ከተማው ሌቦችና ወንጀለኞች እንዳይዘርፉት ህዝቡን በማስተባበር አረጋግተው ያለምንም ጥፋት የሽግር ሂደቱን ማፋጠን። 4. የቡታጅራ ስታዲዮም ህዝቡን አስተባብሮ ጫካ ኣስመንጥሮ ማሰራት። 5. የቡታጅራ ሆስፒታል የቡታጅራ ህዝቡን አስተባብሮ ጫካ ኣስመንጥሮ ማሰራት። 6.ከስዊድን መንግስት የእርዳታ ድርጅት ጋር ትብብር በመፍጠር ድኩማን የአይን ሬፈራል ሆስፒታል ማሰራት 7. መርሲ ሆስፒታል እንዲሰራ ፕሮጄክቱን በመምራት ገንዘብ ከፍለው መታከም ለማይችሉ ኣቅመ ደካሞች በከፊል ነጻ ህክምና እንዲያገኙ መርዳት። 8. በቅርቡ ደግሞ በኣለም ሶስት ሃገሮች ብቻ የሚገኘውን የአይጥ እርባታ ቡታጅራ ከተማ ዉስጥ እንዲከፈት በማድረግ ከተማዋ ዉስጥ ኣስራሁለተኛ ክፍል ኣጠናቀው ወደ ዩኒቨርዚቲዎችና ኮሌጆች ላልገቡ የስራ እድል በመፍጠር ወዘተ... ጋሽ በቄ እና ባለቤቱ ጎንደር ቢወለዱም ሁሉንም ልጆቹንም ሆነ ፕሮጄችቶቹን የወለዳቸው በሚወዳት ቡታጅራ ከተማ ዉስጥ ነው። ስለዚህ ኢትዮዽያችን የቀናችው በሃገር ወዳድ ኢትዮዽያውያን ልጆችዋ እንጂ በዘርና በጎጥ በሚያንስቡ መንደርተኞች አለመሆኑ ከምንወደው የቀለምና የልማት አባታችን ጋሽ በቄ መረዳት ይቻላል። እስኪ እኔ ይህን ያህል ስለ ጋሽ በቀለ ዉለታዉን ባየሁትና በሰማሁት ማለት ከቻልኩ ለሎቹስ የቡታጅራና ኣካባቢዋ ተወላጆችና ነዋሪዎች ምን ይላሉ? አብድልማሊክ ሁሴን


19 views0 comments
bottom of page