top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የአንድነት ጥያቄ ከጉራጌ ልማት ማህበር ሪያድ



በሪያድ የመስቃን ልማት ማህበር ከጉራጌ ልማት ማህበር በደረሰው የአንድነት ጥሪ ወይም የጋራ በሆነ ጥቅም እና ጉዳይ አብሮ የመስራት ጥሪ መሰረት የመስቃን ልማት ማህበር ስራ አስፈፃሚው አካላት በጉዳዩ አጽንዎት ሰጥተው ተወያይተዋል። በውይይቱም ስራው አስፈጻሚው የጉራጌ ልማት ማህበር ያቀረበውን የአንድነት ጥሪን በመርህ ደረጃ እና በመስፈርት በጋራ ጉዳይ አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። ለዚሁም የመስቃን ልማት ማህበር ሪያድ ሳዑዲ አራቢያ ውስጥ ከሚገኙ የመስቃን ልማት ማህበር አባላት፣ የመስቃን ጥሌል የሽማግሌዎች ኮሚቴ ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ የባለድርሻ አካላት እና የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ለመወያየት መርሐ ግብር እንደነደፈ አስታውቋል። በመርሃ ግብሩ መሰረት ሳኡዱ አረቢያ ውስጥ ከሚገኙ ከሁሉም የሚመለከታቸው የመስቃን ቤተ ጉራጌ አካላት የሚደረገው ውይይት አዎንታዊ ምላሽ አግኝቶ ከተጠናቀቀ በተዋረድ ሃገር ከሚገኙት የቤተ-መስቃን አካላት፡- የመስቃን ልማት ማህበር ፣ የሐገር ሽማግሌዎች፣ የሚለከታቸው የመንግስትም አካላት እና ለመላው የመስቃን ቤተ ጉራጌ ማህበረሰብ እንደሚያሳውቅ እና የአንድነቱ መልካም ጥሪ ጭምር ይሳካ ዘንድ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርግ መስቃን ልማት ማህበር በአንክሮ አሳስቧል።

ምንጭ - መስቃን ልማት ማህበር (ሪያድ)


23 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page