top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ኢንተርፕርነር ሺፕ ማለት ምን ማለት ነው?ኢንተርፕርነር ሺፕ /የስራ ፈጠራ / ፅንሰ ሀሳብ የተጀመረው ለ 18ኛው ክፍለ ዘመን (1700 ዎቹ ) ሲሆን ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ቢዝነስ አስተሳሰብ ሲቀነቀን እስከ አሁን እስካለንበት የ21ኛው ክ/ዘመን ደርሷል፡፡ ብዙዎች ይህንን ፅንሰ ሃሳብ ከግል ስራ ፈጠራ (በግል ስራ መጀመር) ጋር የሚያያይዙት ሲሆን የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ደግሞ ከዚህ ባለፈ ተጨማሪ ትርጉም እና ትንታኔ ይሠጡታል፡፡

  • አንድ አንድ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ኢንተርፕርነር (ስራ ፈጣሪ) ማለት ከዚህ በፊት ያልተጀመሩ / ያተሞከሩ/ ትርፋማ ስራዎች ለመጀመር የሚደፍር እና ሊከተሉ ለሚችሉ ኪሳራዎች ሃላፊነት ለመውሰድ የሚደፍር ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ልዩ ልዩ የፈጠራ ስራዎች ወደ ገበያ የሚቀርብን ሰው ስራ ፈጣሪ /ኢንተርፕረነር) በማለት ይበይናሉ ፡፡ አንድ አንድ ግለሰብ ኢንተርፕረነር ነው የሚያስብለው አዳዲስ ምርቶች እና ምርት ሂደቶችን በማስተዋወቅ ሰፊ የገበያ ድርሻን ለማግኘት የሚሞክር ነው ሲሉ በርካታ የመስኩ ምሁራን ይገልፃሉ፡፡

  • ይህ በእንዲህ እያለ በርካታ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በመሰረታዊነት በአንድ ነገር ላይ ይስማማሉ፤ አንድ ሀገር ምጣኔ ሃብት ለማሳደግ እንዲሁም በርካታ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ሁነኛው መንገድ የስራ ፈጠራ (ኢንተርፕርነርሺፕ) መሆኑን። ከእንደኛ ዓይነት ሀገራት ( እያደጉ ባሉ ሀገራት) አዳዲስ እና ጀማሪ የስራ ዘርፎች በስራ እድል ፈጠራ፣ በገቢ እድገት እንዲሁም በድህነት ቅነሳ በኩል ለሃገሪቱ የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ በእነዚህ ሀገራት ያሉ መንግስታት ለእነዚህ አዳዲስ የስራ ዘርች ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል፡፡

አንዳንድ ግለሰብ ስራ ፈጣሪ የሚያሰኙት መሰረታዊ ባህሪያት

በአለማችን ላይ የሚገኙ ስራ ፈጣሪዎች ከተለያየ ይህ ህብረተሰብ ክፍል የተገኙ፣ የተለያዩ ዘር፣ እምነት፣ሃይማኖት፣ ፆታ እና የእድሜ ክልል ቢኖራቸውም እነዚህን መሰረታዊ ባህሪያት ግን ይጋሯቸዋል፡፡

  1. የፈጠራ ችሎታ

አዳዲስ ምርቶችን አገልግሎቶች እና የአሰራር ስልቶችን ማስተዋወቅን የሚያካትት ሲሆን የፈጠራ ችሎታ በስራ ላይ ለሚገኙ ምርቶች እና አገልግሎቶች መሻሻል አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ባህሪ በመጠየቅ፣ በመማር እና ምርምር ከማድረግ ማዳበር ይቻላል፡፡

  1. ቁርጠኝነት፡-

ይህ የስራ ፈጣሪዎች ባህሪ በተለየ ሁኔታ እንዲሰሩ የሚያደርጋቸው ባህሪ ነው፡፡ ስራ ፈጣሪዎች ከሌላው በበለጠ ጠንካራ ሰራተኞች ናቸው ሃሳቦቻቸው እና የአሰራር እቅዳቸው ከተግባር ጋር ሲጣመር ቁርጠኝነት ይባላል፡፡

  1. ፅናት፡-

ጠንካራ ፍላጎትና አላማን ይዞ እስከ ስኬት መዝለቅ የፅኑ ሰዎች መለያ ነው፡፡ ይህም ሲባል በጥንካሬ ያለማቋረጥ ላስቀመጡት ዓላማ በትጋት መስራት እና ለአስቸጋሪ ሁኔታዎች እጅ አለመስጠት ማለት ነው፡፡ በርካታ ሙከራዎች ባይሳኩ እንኳን እስኪሳካ መማርና ለስኬት መድረስ የስራ ፈጣሪዎች ዋነኛ መገለጫ ባህሪ ነው፡፡

  1. ለለውጥ ዝግጁነት

ገበያው በሚፈልገው መልኩ አካሄድን በማድረግ እና ለአዳዲስ ሃሳቦች አዕምሮን ክፍት ማድረግ ማለት ነው፡፡

የገበያውን እውነታዎች በመረዳት ተለዋዋጭ የገበያ እቅዶችን ማዘጋጀት ተገቢ ነው፡፡ ይህም ለአንድ አዲስ የስራ ፈጣሪ ወሳኝ ባህሪ ነው፡፡

  1. መሪነት

ተገዢ የሚሆኑበት ሕግ በማዘጋጀትና እና ግልጽ የሆነ ግብን በማስቀመጥ ወደ ስኬት የሚያደርስ ልዩ ክህሎት ነው፡፡

  1. ጠንካራ ፍላጎት፡-

ይህ ባህሪ የአንድን ስራ ፈጣሪ እስከ መጨረሻው እንዲፀና የሚደርገው ሲሆን ሌሎችንም በስራው ለማሳመን የሚረዳ ነው፡፡

  1. በራስ መተማመን ፡-

ይህ የእርግጠኝነት ባህሪ ሲሆን ጥርጣሬን ከሕሊና በማስወገድ አንድ ፈጣሪ ሙሉ አቅሙን ስራው ላይ ብቻ እንዲያው ያስችለዋል፡፡ በራስ መተማመን የሌሎች ሠዎችን ትችት እና አስተያየት ያለምንም የአቋም ለውጥ ለመቀበል ያስችላል፡፡

ምንጭ - studentethiopia


420 views0 comments
bottom of page