የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
የ27 አመታት ትሩፋቶች ልክፍት (ክፍል ሁለት)
Updated: Jun 9, 2019

ትዕዛዝ አክባሪው ሰይጣን
ሰይጣን ልክ እንደ ዘረ አዳምና ሄዋን እንዲሁም በምድርና በሰማይ እንደሚገኙት ፍጡራን ሁሉ ፍጡር ነው። እንደ ማንኛውም ምድራዊ ፍጡር ቤተሰብ መስርቶ እና ወልዶ ይስማል እንዲሁም ሰያጣነዊ ማህበራዊ ህይወት ይኖረዋል ብዬ ፈጽሞን አስቤውም የማላውቅና ሰይጣንን ከሰይጣንነቱ ውጪ ወይም የማይዳሰስ መሆኑን ብቻ ነው የማውቀው። ይሁንና ሰይጣን የተፈጠረበት አላማ አለው። የሰውም ልጅ እንደዛው ነው። ታዲያ ያ… ሰይጣን የተሰጠውን ትዛዝ ያለመታከትመና በትጋት ሲወጣው ነው የሚስተዋለው። ሰይጣን ከተሰመረለት መስመር ውጪ ፍንክች አይልም። ኦዎን… የሰይጣን ደግ፣ ሩህሩህ፣ አዛኝ እና ቸር እንዲሁም በምድር ውስጥ ለሚገኙ ፍጡራን ሁሉ መልካሙን የሚያስብ ፈጽሞውን አይገኝም። ሰይጣን የተመደበበት ስራ ከመስራት አንጻር በእጅጉ የተመሰገነ እና ትዕዛዝ አክባሪ ነው።
ትዕዛዛትን የሚጥሰው የሰው ልጅ
ፈጣሪ የሰውን ልጅን ሲፈጥረው ያለማጋራት ፈጣሪን እንዲገዛ፣ ፍጹም ለመልካም እና ደግ ብቻ ነው። ታዲያ… ይህ የሰው ልጅ ከተፈጠረ ጀምሮ በሰው ልጆች መካከል የደረሱትን መተላለቅና ጉዳቶች ሲቃኙ የሰው ልጅ በትእዛዝ አክባሪነቱ እና ተቀባይነቱ ከሰይጣን በእጅጉ የወረደ ነው። እንድየውም የሰው ልጅ ተብዬው ክፋት እና መጥፎ ተተግባር ከመበራከቱ የተነሳ “ሰው ሰይጣን ነውን ? ወይስ “ሰይጣን ሰው ነውን” ? የሚል ጥያቄ ያጭርብናል።
ዝርጠጣ
በክፍል አንዱ ጽሁፍ ከፌስቡክ መንደር ዘልቄ “ ስለ እሳት መቆሰቆና ሲቆሰቆስ መንደዱን ይጨምራል " የሚል ከተራ ጽሁፎች መሃል ሰፍሮ ማግኘቴን ተናግሬ ነበር። የዘመኑ ወጣትና ጎልማሳ የማንበብ ባህሉ ጠፍቶት ፌስቡክ ላይ መጣጅ ከጀመረ እንደ ሰነበተ… መቆየቱ ለማንም የተሸሸገ አይደለም። ሌላው ደግሞ ምንም የማንበብ ባህል ያልነበረው፣ የሌለው እና እንዲኖረውም ፍንጭ ያላሳየውም በርካታ እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ። በአለንበት የመረጃ ዘመን ጊዜን ሳንጠቀምበት እንዲያልፍ የምንፈልግበት ቦታም ቢኖር እዚሁ ፌስቡክ መንደር ነው። ለማለት የፈለግኩት የኢትዮጵያውና ማህበረሰብ በተመለከተ ብቻ ነው። ከኢትዮጵያውን ውስጥም ቢሆን ወደ ፌስ ቡክ እራሳቸውን ሲዶሉ መልካሙን ብቻ በመስበክ ቀናውን መንገድ በማሳየት ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ እንዳሉ የሚዘነጋ አይደለም። የሆነው ሆኖ በእኔኛው አመለካከት በፌስ ቡኩ መንደር ውሎ ቅኝት በ27 ዓመቱ አገዛዝ ምን ያህል ሃገራችን ሃገር ተረካቢውን ትውልድን እንዳጣች ትልቅ ምስክር ነው። “አንዳንዱ አለማወቁን የማያውቀው የእኔ ቢጤው ትልቁ የእቀውቀት እና የስልጣኔ ደረጃ መኪና መንዳትና Smart phone መጠቀም ይመስለዋል”።
ወደ ጉዳዩ ስመለስ ስለ እሳት መቆሰቆና ሲቆሰቆስ መንደድ መጨመሩን የሚያራምዱት ግለሰብ ሰለ ተዳፈነ እሳት አደገኛነት የተገነዘቡ አይመስለም። ጸሃፊው ኦህህ… ይቅርታ ጸሃፊ የሚለው ትልቅ ስያሜ ስለሆነ የFB “ተሳታፊ” ተብለው ቢጠሩ ይመጥናቸዋል። ታዲያ እኚሁ ተሳታፊ በሰላም እና አንድነት የFB ሰበካቸው ለማያውቃቸው ነብያዊ ተግባር ለመፈጸም ወደ FB የተላኩ “ቀጣይ ነብይ” ያስመስልላቸዋል። እርሳቸውን በተመለከተ መሬት ላይ ያለው ጉዳይ ግን አያድርስ… ነው። ነገረ ተግባራቸው እንደ ትንሽ አይጥ አይነት ነው። ልክ ሰሞኑን እቤታችን ገብቶ ልናስወግደው ልጅ አዋቂው ቢረባረብ እና አሰሳውን ቢያካሄድም ደብዛው ጠፍቶ እንደቀረው ትንሽ አይጥ አይነት ናቸው። ያን… ትንሽ አይጥ እንዳንተወው አሳቻ ወቅት ጠብቆ ውር ውር እያለ ህፃናትን ማስበርገጉን ተያያዘው። ውልብ...ውልብልብ ሲል ታየ ተብለን ደግሞ ማሳደደዱን ብንያያዘውም ጣታችንን ብቻ ሊያስገባ ከሚችል ስርቻ ውስጥ ገብቶ ይሰወራል። እ… እርሱ ካለበት ዘንድ ለመድረስ እራሳችንን በእርሱው መጠን ማውረዱ እና በእርሱ መንገድ መሄዱን ግን አልፈለግነውም እንዲሁም ቤቱም... ሃገሩም በድምፅ አላጸደቀውም። አረረረ… እናንተዬ ፈጣሪ ከመውረድ ይጠብቃችሁ።
ታዲያ የአይጥ ጉዳይ ብርቅ ነው እንዴ ? በአይጥ ምክንያት ውድ የሆነው ጊዜ ማባከኑ አግባብ አይደለም ትሉ ይሆናል። ወደጆች ሆይ የእኛው ትልቁ ጥረታችን ይህ ሾላካ ወንድ አይጥ ሴቷን አይጥ ፈልጎ አምጥቶና ተራብቶ ቤቱ እና ሃገሩን አይጥ በአይጥ እንዳያደርገው ነው። “ለምን ትዘረጠጣለህ ሃገሩ አይጥ - በአይጥ ከሆነ የአይጥ አስወጋጅ መወቅርን በመዘርጋት ለተወሰኑት ሹመትን ለቡዙሃኑ ደግሞ የስራ እድልን ይፈጥራል” እንዳትሉኝ ደግሞ እሰጋለሁ።
ዘመኑ የነቀፌታ ዘመን በመሆ “አንተ ማን ነህና ? እንዳሻህ የምትዘረጥጠው እና የምትዘረጠጠው” የሚል ነቀፌታ የሚሰነዝር ከተከሰተ... እንካችሁ አዎን… እኔ በተዋከቡ፣ በእናውቅልሃለን አዕምሮአቸው የጦዘ እና በክፋት የሰኩሩ መሪዎች በፈጠሩት የተዋከበ ማህበረሰብ ውስጥ በፈጣሪ ፍቃድ የተከሰትኩ ነኝ።
ይቀጥላል…
(በኢዱና አህመድ)