top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ማዳመጥ ትልቅ የዕውቀት ምንጭና መከበሪያ ነው!ማዳመጥ ትልቅ የዕውቀት ምንጭ ነው፡፡ ማዳመጥ ያስከብራል! አንድ ግለሰብ ሲያዳምጥ እንጂ እሱ ብቻ ሲያወራ አዲስ ዕውቀት ሊገበይ አይችልም፡፡ ምክንያቱም ግለሰቡ ሲያወራ እሱ ብቻ የሚያውቀውን ሲሆን ካዳመጠ ግን የበለጠ ሊያውቅ ይችላል፡፡ ሌላው ነጥብ ደግሞ ለሚናገረውም ግለሰብ ክብር ለማሳየት ነው፡፡ ብዙወቻችን ኢትዮጵያዊያን ይህንን የትምህርት ምንጭ የዘነጋን ይመስላል፡፡ በተለያዩ ጥቃቅን ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሰባስበን ስናወራ የሚናገር እንጂ የሚያዳምጥ ጥቂት መሆኑ በጣም ያሳስባል፡፡ ጥቂትም ሆነ ብዙ ሆነን ተሰባስበን ስንወያይ ወይም ስናወራ ብዙወቻችን ከየአቅጣጫው በቅጡ ሳንደማመጥ እናወራለን፡፡ አንዱ መናገር ጀምሮ ሳይጨርስ ሌላው ያቋርጠዋል ወይም ይነፍገዋል፡፡ ማዳመጥና መፅሃፍ ማንበብ ስለማናዘወትር የብዙወቻችን አጠቃላይ እውቀት የተወሰነ ስለሚሆን ተሰባስበን በምናወራ ጊዜ የምናወራበት አርዕስት ውስን ነው፡፡ በትርፍ ጊዜ የምናደርጋቸው ዝንባሌዎችን ካዳብርንና ካለን ግን ውይይታችን ሰፋ እንዲል ያደርገዋል፡፡ ይህም በመሆን ጊዜ ስለሌሎች ማውራትና ማማት እንድንቀንስ ይረዳናል፡፡ የሚያዳምጥ ሰው በየጊዜው ዕውቀት ይቀስማል፡፡

አንዲት ጥቂት ነገር ካወቅን ደግሞ ብዙ የምናውቅ እየመሰለን ማጋነን ደግሞ አይጠቅምም፡፡ ታዲያ እኔ እንደዚህ አደረግሁ፥ እኔ እንደዚህ ፈጠርኩ፥ እኔ እንደዚህ ነበርኩ ማለትን እናዘወትራለን፡፡ ሳያስፈልግ ዝናና ክብር እንፈልጋለን፡፡ ተጠይቀንም ሆነ ሳንጠየቅ ጉዳዩን ባናውቀውም ሃሳብ እንሰጣለን፡፡ የማናውቀውን ስንጠየቅ ይህን እኔ አላውቅም ብለን ደፍረን ከመመለስ ይልቅ የተሳሳተ ትንተና ውስጥ እንገባለን፡፡ ያ በራሱ አዳማጩ መልሱን የማያውቅ ከሆነ ማሳሳት ሲሆን፤ አዳማጩ ደግሞ ጉዳዩን የሚያውቀው ከሆነ በራስ ግምት ውስጥ መግባት ነው፡፡ ይህም ሁኔታ በባዶ ያዎቁ ከመምሰል አልፎ ውርደት ውስጥ ይከታል፡፡ ይህ እራሱ ለኢትዮጵያ ችግር ትልቅና ዋነኛ ምሳሌ ነው፡፡ ስለ አንድ ጉዳይ በምክንያትና በተጨባጭ ተነግሮን ልክ መሆኑን ብናውቅም መጀመሪያ በግላችን ካሰብነውና ከምናውቀው የተለየ ከሆነ ለመቀበል ይከብደናል፡፡

ከእኛ የተለየ ወይም የተሻለ ሃሳብ በቀረበ ጊዜ በግላችን የተጠቃን ይመስለናል፡፡ በምክንያታዊ ሆኖ ጉዳዩን አበጥሮ በመተንተን የሚያስረዳንን ደግሞ በግል ከምናውቀው የተለየ ከሆነ ተንታኙን እንደ ስሜተኛ መቁጠር አልፎ አልፎ የተለመደ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜም ይህንን ተንታኝ “ይኸማ የኔን ብቻ ስሙኝ” ባይ ነው ተብሎ ስም ይወጣለታል፡፡ እና እውነት የሚናገሩ ሰዎች ይህንን ስም በመፍራት ጸጥ ይላሉ፡፡ ግን ብልሆች ናቸው፡፡ እነዚህ ብልሆች ጸጥ ማለታቸው ግን ሁላችንንም ይጎዳናል፡፡ እንደነዚህ ያሉ ግለሰቦችን መተባበርና ሞራል መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ ከእኛ የተለየ ወይም የተሻለ ሃሳብ በቀረበ ጊዜ ልምድ መውሰድ እንጂ በግላችን እንደተጠቃን መቆጠር የለበትም፡፡

ማዳመጥ፤ የማዳመጥ ጥቅሙ!

አንድ ሰው መከበርና ዝነኛ መሆን ከፈለገ፤ ለመከበር ሌሎችን ማክበርና የሚያስከብሩ ድርጊቶችን ማሳየት አለበት፡፡ ዝነኛ ለመሆን ደግሞ ችሎታውንና ደንታውን በተግባር ማሳየት አለበት፡፡

አንዳንድ ሰዎች ታዲያ ክብርና ዝንናን በራሳቸው ማስተዋወቅ ሲሙክሩ አያምርም፡፡ ይህንን ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የማዳመጥ ትዕግስት ሊኖረን ይገባል፡፡ ካዳመጥን ደግሞ አዲስ ዕውቀት እንደምናገኝ ካመንን የማዳመጥ ትዕግስታችን ይጨምራል፡፡ ዝናና ክብር በከፊል በራስ የሚፈጠሩ ቢሆኑም ሙሉ በሙሉ መጽደቅ ያለባቸው ግን ከሌሎች እይታ ነው፡፡ አዲስ ዕውቀት ባገኘን ጊዜ አስተሳሰባችን ይሰፋል፡፡ አስተሳሰባችን በሰፋ ቁጥር በተለያዩ ጉዳዮችና ሁኔታወች ላይ ምክንያታዊ የሆነ አመለካከት ይኖረናል፡፡ በሌሎችም ዘንድ እንከበራለን፡፡ ዝናና ክብር በከፊል በራስ የሚፈጠሩ ቢሆኑም ሙሉ በሙሉ መጽደቅ ያለባቸው ግን ከሌሎች እይታ ነው፡፡

ዝናና ክብር በከፊል በራስ የሚፈጠሩ ቢሆኑም ሙሉ በሙሉ መጽደቅ ያለባቸው ግን ከሌሎች እይታ ነው፡፡

ለዚህ መገልገያ መሳሪያ የሚሆነው ማዳመጥና መደማመጥ ሲቻል ነው። የግል ህይዎታችንም ይሻሻላል፡፡ ደንታ ያለው ኢትዮጵያውያን ትውልድም እናመርታለን፡፡ ለኢትዮጵያ እድገትም ጥሩና እርግጠኛ መሰረት እንጥላለን፡፡

source - tatariw


20 views0 comments
bottom of page