top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶችየጡት ካንሰር በዓለማችን በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በወጣት ሴቶች ላይም የመከሰት እድል አለው፡፡ የጡት ካንሰር መነሻ መንስኤዎች በእርግጠኝነት የሚታወቁ ባይሆንም የተካሄዱ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ ለህመሙ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎችን በከፊል እንደሚከተሉት ቀርበዋል፡፡ 1. እድሜ በጡት ካንሰር የመጠቃት እድል በእያንዳንዱ 10 ዓመት የህይወት ዘመን በእጥፍ የሚጨምር ሲሆን በአብዛኛው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ ይከሰታል፡፡ 2. በዘር ይህ የካንሰር አይነት በዘር የመተላለፍ ባህሪ ያለው ሲሆን በካንስር ህመሙ የተጠቃው የቤተሰብ አባል እናት ፣ እህት ወይንም ሴት አያት ከሆኑ የመተላለፍ እድሉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ 3. ከዚህ ቀደም የጡት ካንሰር ህመም የነበረባቸው 4. ልጅ ያልወለዱ ሴቶች ወይም የመጀመሪያ ልጃቸውን እድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ ከሆኑ በኋላ የወለዱ ሴቶች 5. ጡት ያለማጥባት 6. ደረታቸው ለብዙ ግዜ ለጨረር የተጋለጡ ሴቶች 7. ከፍተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች ማዘውተር 8. ሲጋራ ማጨስ ** የጡት ካንሰር ህመም ምልክቶች** 1. በጡት ላይ እና በጡት አካባቢ የሚወጣ እባጭ አብዘኛውን ግዜ የጡት ካንሰር ህመም ምልክት የሚሆነው ህመም የለሽ የሆነ እባጭ ነው፡፡ ይህ እባጭ አብዛኛውን ግዜ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የካንሰር አይነት ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ 2. የጡት መጠን እና ቅርጽ መለያየት አንዱን ጡት ከሌላኛው ጋር በማነጻጸር የቅርጽ እና የመጠን ልዩነት ካስተዋሉ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ 3. በተወሰነ የጡት ቆዳ ላይ የመጠንከር ስሜት መከሰት 4.የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ይህ አይነት የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መገልበጥ ከልጅነት (ቀድሞ የነበረ) ወይም ተፈጥሮአዊ የሆነውን የጡት ጫፍ መገልበጥ አያካትትም 5. የህመም ስሜት አልፎ አልፎ በጡት አካባቢ የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል ፡፡ ነገር ግን የጡት አካባቢ ህመም በአብዛኛው የካንሰር ህመም ቀዳሚ መገለጫ ወይም ምልክት ላይሆን ይችላል፡፡ የጡት ካንሰር ህመም የሚሰራጭባቸው ቦታዎችን የሚከተል የህመም ምልክት ሊኖረው ይችላል፡፡ ቀድሞ የሚሰራጨው ወደ ብብታችን ስር በሚገኘው( Lymph node ) በተላበው አካባቢ ሲሆን ይህም የብብት ስር እብጠትን ሊስከትል ይችላል፡፡ የጡት ካንስር ቅድሚያ ካልተደረሰበት እና ህክምና ካላገኘ ወደ ጉበታችን እንዲሁም ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመሰራጨት እስከ ሞት ሊያደርስ የሚችል የህመም አይነት ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያም እየተበራከተ ያለ የህመም አይት ነው፡፡ በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ማናኛውም አይነት የህመሙ ምልክቶች የታዩት ሠው ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ በቶሎ መፍትሄ ማግኘት ይኖርበታል፡፡

በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም ቱፈር ጤና ይስጥልኝ


65 views0 comments
bottom of page