የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
የሚዛናዊ መሪ ሃላፊነትና ሚና ከችሎታውና ትህትናው ጋር

የሚዛናዊ መሪ ሃላፊነትና ሚና ሰፊ ሆኖ ችሎታና ትህትናን ማጣመር ሲችል ነው፡፡ ሚዛናዊ ስል አንድ መሪ ከበቂ ችሎታ ባሻገር ጥሩ ራዕይና ትህትና ያለው ሆኖ ከሰዎች ጋር አብሮ ለመስራትና ህዝብ ለማገልገል ዝግጁ መሆን ሲችል ነው፡፡ የተለያዩ ሁኔታወችና ቦታዎች ላይ መሪዎች እንዳሉ የታወቀ ነው፡፡ ለምሳሌ የቤተሰብ፣ የክለብ፣ የሃይማኖት፣ የድርጅት፣ የተለያዩ ተቋማት፣ የሃገር ወዘተ መሪ ሊሆን ይችላል፡፡ መሪ መሆን ማለት ደግሞ ወሳኝ የሆነ ቁልፍ ቦታ ላይ ሃላፊነት መውሰድ ማለት ነው፡፡ ይህንን ሃላፊነት ለመወጣት ታዲያ መሪ ሚዛናዊ መሆን አለበት፡፡ ሚዛናዊ ስል አንድ መሪ ከበቂ ችሎታ ባሻገር ጥሩ ራዕይና ትህትና ያለው ሆኖ ከሰዎች ጋር አብሮ ለመስራትና ህዝብ ለማገልገል ዝግጁ መሆን ሲችል ነው፡፡ ሚዛናዊ ስል አንድ መሪ ከበቂ ችሎታ ባሻገር ጥሩ ራዕይና ትህትና ያለው ሆኖ ከሰዎች ጋር አብሮ ለመስራትና ህዝብ ለማገልገል ዝግጁ መሆን ሲችል ነው፡፡
ከሰዎች ጋር አብሮ መስራት ስል ሰዎች ችሎታቸውን ለሃገር ወይም ለተቋሙ እንዲጠቀሙበት ማመቻቸት መቻል ማለቴ ነው፡፡ በተለይ በተለይ ያለ እራዕይና ትህትና ሚዛናዊ መሪ መሆን ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም አንድ መሪ ራእይ ሲኖረው ጎበዝ ስለሆነ ሰዎች ደህንነት ስለሚሰማቸው ያምኑታል፡፡ ትህትና ሲያሳይ ደግሞ በተከታዮቹ ወይም በህዝብ ይከበራል፡፡ ይወደዳል፡፡
ራእይ ማለቴ ለምሳሌ መሪው ችሎታና ጥበብ ስላለው ለሚመራው ተቋም፣ ህዝብ ወይም ሃገር ምን አይነት ጠቃሚ ነገር እንደሚያስፈልግ ስልሚያስብና ስለሚያውቅ እቅድ ያወጣል፤ አዲስ ሃሳብም ያመነጫል፡፡ የስራ አጋሮቹንም አዲስ ሃሳብ እንዳላቸው ይጠይቃል፡፡ እንግዲህ ጥበብ ተጠቅሞ ራእይ ያለው መሪ ስል የማሻሻል አላማ ኖሮት ጥሩ አቅጣጫም የሚያሳይ ነው ለማለት ይሆናል፡፡
ትህትና ማለቴ ደግሞ ለምሳሌ መሪው የሚመራውን ተቋም ወይም ሃገር በቅን አስተሳሰብ ለማገልገልና ለመስራት ዝግጁ ሲሆን ነው፡፡ ለምሳሌ ህግ፣ ህዝብ፣ አገር፣ ወግና ባህል የሚያከብር ሲሆን ነው፡፡ የማይዋሽ ለማለት ነው፡፡ አቀራረቡ በስነስርአትና በአክብሮት የተላበሰ በሚሆን ጊዜ ደግሞ ሰወች መሪን ሁለገባዊ መሆኑን ስለሚረዱ ይወዱታል፡፡ ያከብሩታል፡፡ እንደማስበው ባጭሩ የሚዛናዊ መሪ ጥበብና ሚና ይህንን ይመስላል፡፡
በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደሰማሁት ብዙ ሰዎች መሪ መሆን ማለት ትእዛዝ ማስተላለፍ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ አባባል ሙሉ በሙሉ እውነት አይደለም፡፡ ሰወች መሪ ትእዛዝ ሰጪ ነው ብለው በሚያስቡ ጊዜ በውድም ሆነ በግድ ትእዛዝ ተቀባይ ብቻ ይሆናሉ፡፡ እንደዚህ የሚያስቡ ሰወች በራሳቸው ስለማይተማመኑ እራሱን የቻለ የራሳቸው አስተሳሰብና ሚዛናዊ እውቀት አንሷቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶችና ጥቅሞች ወይም በእውቀት ማነስ ምክንያት ትእዛዝ ፈጻሚዎች ወይም ተቀባዮች ብቻ ይሆናሉ፡፡
ለምሳሌ ማንኛችንም እድሜአችን ከ75 አመት በታች የሆን ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ ነጻ ሆነን የኖርንበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም እስካሁን ድረስ ራእይ፣ ጥበብና ትህትና ያለው መሪ ኖሮን አያውቅም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በቃ በማለት ፋንታ መጥፎ መሪዎችን እንዲቆዩ ስለምንፈቅድላቸው ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ነጻ ለመሆን ሁልጊዜ እንታገላለን፡፡ አንዳንዶች ለመጥፎ ነገር ተገዢና ታዛዥ ሆነው ሌላው እንዲበደል ተባባሪዎች ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ እንደማያገባቸው ዝም ይላሉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ገና ነጻ አልሆንም፡፡ ለእውነተኛ ነጻነት የሚታገለው ክፍል ለራሱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነጻ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነት እንዲሰፍን ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ ነጻነትን የምናገኘው ተገዢና ታዛዥ ሆነን ወይም ዝም ብለን ሳይሆን ሁላችንም ለሁላችን ስንተሳሰብና ኢትዮጵያ የእኩልነትና የነጻነት ሃገር እንዲትሆን አብረን ስንታገል ነው፡፡
ነነጻነትን የምናገኘው ተገዢና ታዛዥ ሆነን ወይም ዝም ብለን ሳይሆን ሁላችንም ለሁላችን ስንተሳሰብና ኢትዮጵያ የእኩልነትና የነጻነት ሃገር እንዲትሆን አብረን ስንታገል ነው፡፡ የዚህ ጽሁፍ አላማ ለመጥፎ ነገር ተገዢና ታዛዥ ከመሆን ወይም ዝም ከማለት ይልቅ ለነጻነት መታገል ይበልጣል ለማለት ነው፡፡ አስተያየትዎን ከታች ለማስፈር አይርሱ!!
ምንጭ - ታታሪ