top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ከማህፀን በላይ/ ዉጪ እርግዝና/ Ectopic pregnancy



ከማህፀን በላይ/ ዉጪ እርግዝና/ Ectopic pregnancy

ከማህፀን በላይ እርግዝና የሚከሰተዉ የወንዱ ዘር ፈሳሽ የተደባለቀባት የሴት እንቁላል / fertilized egg/ ከማህፀን ግድግዳ ዉጪ በየትኛዉም ቦታ በምታድግበት ወቅት ነዉ፡፡ በአብዛኛዉ ጊዜ ከማህፀን በላይ እርግዝና የሚከሰተዉ እንቁላልን ከእንቁሉጤ ወደ ማህፀን በሚወስደዉ የሴት ዘር መተላለፊ ቱቦ ዉስጥ (ፋሎፒያን ቲዩብ/ fallopian tubes/) ዉስጥ ነዉ፡፡ የዚህ አይነቱ ከማህፀን በላይ እርግዝና ቲዩባል ፕሪግናንሲ ይባላል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ከማህፀን ዉጪ እርግዝና በሆድ ዉስጥ፣ በእንቁልጤና በማህፀን አንገት ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡

ምልክቶች የማህፀን በላይ እርግዝና በትክክለኛ መንገድ መቀጠል አይችልም፡፡ እያደገ ያለዉ ሽል ያለቦታዉ ስለሚያድግና የእናትየዋን አካል ስለሚጎዳ ለረጅም ጊዜ መቆየት አይችልም፡፡ ስለሆነም በጊዜዉ ህክምና ካልተወሰደ ለህይወት አስጊ የሆነ የደም መፍሰስ እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡ በመሆኑም በወቅቱ ህክምና ከተወሰደ ለወደፊቱ ሊኖር የሚችለዉን ጤናማ እረግዝና ዕድል እንዲሰፋ ያደርጋል፡፡ በመጀመሪያዉ የእርግዝና ጊዜያት በመደበኛዉ/ትክከለኛ አርግዝና ወቅት ከሚታየዉ የእርግዝና ምልክቶች በስተቀር( የወር አበባ መቅረት፣የጡት ህመም፣ ማቅለሽለሽ እንዲሁም በምርመራ እርግዝና መኖሩ መታወቅ በስተቀር) ምንም የተለየ ሌላ ምልክት የለዉም፡፡ እየቆየ ሲመጣ ግን አርግዝናዉ መቀጠል ስለማይችል እንደ ከብልት ደም መድማት፣ የዳሌ ዉስጥ ህመም ወይም የሆድ ቁርጠት ያሉ የመጀመሪያዎቹ የችግሩ ምልክቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡ በተጨማሪም እንቁላልን ከእንቁልጤ ወደ ማህፀን የሚያጓጉዘዉ ቱቦ /የሴዘር መተላለፊ ቱቦ ስለሚፈነዳ በጣም ብዙ ደም ሆድዎ ዉስጥ ይገባል/ ይጠራቀማል፡፡ ይህ ለራስ ምታት፣ መዝለፍለፍና እራስን እስከ መሳት ደረጃ ሊያደርስ ይችላል፡፡

ተጋላጭነትዎን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮች ከእንዳንዱ 1,000 እርግዝናዎች ዉስጥ 20ቹ ከማህፀን ዉጪ እርግዝና ሊያጋጥማቸዉ ይችላል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከማህፀን በላይ እርግዝና ጋር ተያያዥ ካላቸዉ ነገሮች ዉስጥ፡- • ከዚህ በፊት መሳል ችግር አጋጥሞት ከነበረ • በዘር መተላለፊያ ቱቦዉ ላይ መቆጥቆጥ/ ኢንፌክሽን ከተከሰተ • የዘር ቱቦዉ ላይ ችግር መኖር/ Structural concerns ፡- የዘር መተላለፊ ቱቦዉ ያልተለመደ ቅርፅ ካለዉ ወይም በሌሎች ነገሮች ምክንያት ጉዳት ደርሶበት ከሆነ( ለምሳሌ ቀዶ ጥገና) • የወሊድ መከላከያ፡- ምንም እንኳ ሉፕ/ IUD እየተጠቀሙ እርግዝና የመከሰት እድሉ በጣም አነስተኛ ቢሆንም ሉፕ በማህፀንዎ እያለ እርግዝና ከተፈጠረ ግን እርግዝናዉ ከማህፀን በላይ የመሆን እድሉ ሰፊ ነዉ፡፡ ሌለኛዉ የዘር መተላለፊ ቱቦዉ ከተቋጠረ በኃላ እርግዝና ቢከሰት እርግዝናዉ ከማህፀን በላይ እርግዝና የመሆን እድሉ በጣም ከፍተኛ ነዉ፡፤ • ማጨስ፡- ከእርግዝናዎ በፊት ጀምሮ ሲጋራ እያጨሱ ከነበረ ከማህፀን በላይ እርግዝና የመከሰቱ እድል እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡

ከማህፀን በላይ እርግዝናን መከላከል ከማህፀን በላይ እርግዝናን መከላከል ባይቻልም የተወሰኑ ለችግሩ መከሰት የሚያጋልጡ ነገሮችን መቀነስ ግን ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነትን በመገደብና አንድ ለአንድ በመፅናት የአባለዘር በሽታ ችግርን ለመከላከል ይቻላል፡፡ ይህ የዳሌ ዉስጥ ህመምንን ስለሚቀንስ ከማህፀን ዉጪ እርግዝናን መቀነስ ይችላል፡፡ ሌላኛዉ ሲጋራ ማጨስን ማቆም ነዉ፡፡


133 views0 comments
bottom of page