የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች (ክፍል - 02)

7. መናውን ፈሰርነው አንተ ሳትናገር
ድቤውም ዋሽንቱም መሰንቆው ጭራ አይቀር
ጠጅና ጉማሬ ጫት ስንቅም እንደምር
ጀባ ብለንሃል በዟሂር መነጸር
ሐሲድ የሚመታ አንድ እንኩዋን ሹም ሳይቀር::
8. አላህ ካደረገን የኸልቁ ወዳጅ
በድቤና በጫት ልጀምር በጠጅ::
መሰንቆ እየመታሁ ልወዝወዘው እንጅ
በጭራ በዋሽንት ሰው ባልነካው እጅ
አውሊያ እምጠራበት ሶላት ሳልሰለች::
9. ጫት ባፋችን ይዘን ጠጅ እየጠጣን
ጥቁር ጭራ ይዘን ድቤ እየመታን
ሐሲድ እንዳይነካን አውሊያ እየጠራን
አምስት አውቃት ሶላት እየሰጋገድን
ሰው ያልነካው እቃ ጀሊሉ ሰጠን::
10. መጪውን አየነው ጉድ አጃኢበት
ዓለም ስትስቅብኝ እኔ ሳቅኩባት
ለአዳም መህሉቃት ከወንድም ከሴት
ካለቁት በስተቀር ያሉት በሐያት
ተከትቦ አየዋለሁ ስሙን ወደፊት::
11. ስሙን ይነግረኛል ዋሪዳው ሳይስት
ገና በእናቱ ሆድ ሳኸለቅ ፊት
ለወልይ ለንጉሥ፣ ለራስ መሳፍንት
ምን አስለፈለፈኝ ሊታይ ወደፊት
እኔም በል ብሎኝ ነው የምወሸክት::
12. ሃምሳ ዓመት ስናገር ሰምተው ጉድ እያሉ
እንደ ፍልፈል አፈር ሰው ሲፈለፍሉ
(ሰምተው እንዳልሰሙ አላየንም አሉ
እንደ ፍልፈል አፈር ሰው ሲፈለፍሉ)
እኛም ሰደድናቸው ከአፈር እንዲተሉ
ቀሩ እንደፈራነው ውሸታም እንዳይሉ::