top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"መልካም ቃል እና ንግግር"



"መልካም ቃል እና ንግግር"

‘ጥሩ ንግግር (ቃል) ለተናገረ 400 ዲናር እሰጣለሁ’ የሚለውን ዜና ንጉሱ ለህዝቡ እንዲደርስ አደረገ።

ከእለታት አንድ ቀን ንጉሱ ከአገልጋዮቹ ጋር ከተማውን እየጎበኘ ሳለ በእድሜው የገፋ አዛውንት የፍራፍሬ ዛፍ እየተከለ አስተዋለ። ንጉሱም በመገረም “ለምን ትደክማለህ? ይች የፍራፍሬ ዛፍ አድጋ እንድታፈራ ከሀያ አመት በላይ ትፈልጋለች። አንተ ደግሞ እንደምናይህ አርጅተሀል። ፍሬዋን ለመብላት የምትታደል አይመስለኝም” በማለት ተናገረ። አዛውንቱም “ከኛ በፊት የነበሩት ዘሩ፤ እኛም አጭደን ተጠቀምን… እኛ ደግሞ በተራችን እንዘራለን፤ መጭዎች አጭደው ይጠቀማሉ” በማለት ለንጉሱ መለሰለት …

ንጉሱም በንግግሩ በመደሰት “መልካም ንግግር! 400 ዲናር ስጡት” ሲል አዘዘ… አዛውንቱም ሽልማቱን ተቀብሎ ፈገግ አለ…

ንጉሱ፦ “ለምንን ፈገግ አልክ?” አዛውንቱ፦ “ይች የተከልኳት ዛፍ ከሃያ አመት በኋላ ነው የምታፈራው። ነገር ግን የቃላቶቼ ዛፍ አሁን አፈራች…” ንጉሱ፦ “መልካም ንግግር! 400 ዲናር ስጡት!” አዛውንቱ ሽልማቱን ተቀብሎ እየተመለከተ በድጋሚ ፈገግ አለ…

ንጉሱ፦ “ደግሞ አሁን ለምን ይሆን ፈገግታህ ግርምትህ?!” አዛውንቱ፦ ይች ዛፍ መፍራት ስትጀምር በአመት አንድ ግዜ ነው የምታፈራው ነገር ግን የቃላቶቼ (የመልካም ንግግሬ) ዛፍ አሁን ሁለት ጊዜ አፈራች። ንጉሱ፦ “መልካም ንግግር! አሁንም 400 ዲናር ስጡት” ብሎ ካዘዘ በኃላ አዛውንቱን ሳያይ በፍጥነት አዛውንቱ ካለበት አካባቢ ራቀ…

የአገልጋዩቹ አለቃ “ጌታዬ ለምን በፍጥነት መራቅ ፈለግክ?!” ሲል ጠየቀው … ንጉሱ፦ “እዚህ ሰውዬ ጋር ከቆየን የእሱ መልካም ንግግሮች ሳያልቁ የእኔ ዲናሮች ያልቃሉ ብዬ ስለሰጋሁ ነው” ብሎ መለሰለት…

🎯 «የመልካም ቃል ዛፍ ፍሬዋ ብዙ ነው።» 👑


89 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page