top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ቅጥ ያጣ የራስ ወዳድነት በሽታ የሚያጠቃቸው ሰዎች እና አይነቶቻቸው (Different types of Narcissists)



ቅጥ ያጣ የራስ ወዳድነት በሽታ የሚያጠቃቸው ሰዎች እና አይነቶቻቸው (Different types of Narcissists)

ናርሲሲስቶች (ራስ ወዳዶች) በጥቅሉ ለሁለት የተከፈሉ ናቸው፡-

1.ግልፅ ናርሲስት (Overt Narcissist)፡- ግልፁ ናርሲሲስት ስለማንነቱ፣ ስለስኬቱ፣ስለእውቀቱ፣ ስለሃብቱ እና ባጠቃላይ ያስከብረኛል ወይም ትኩረት ይስብልኛል ስላለው ነገር ሁሉ እያጋነነ በግልፅ ጉራውን ሲነዛ ይታያል፡፡ ግልፁ ናርሲሲስት እዚህ ግባ በማይባል ተቃራኒ አስተያየት የንዴት ጣሪያውን በግልፅ ሲያሳይ ይታያል፣ ንዴቱን ሲገልፅም ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ በመንጨርጨር ነው፡፡ 2.ድብቅ ናርሲሲስት(Covert Narcissist)፡- ድብቁ ናርሲሲስት እንደ ግልፁ ናርሲሲስት ከሌሎች በላይ እንደሆነ የሚያምን ቢሆንም ያንን ሌሎች እንዲያዩ በግልፅ ሲጣጣር አይታይም፡፡ ነገር ግን ላስተዋለው ሰው ችሎታውን እና ስኬቱን ለማሳየት በተዘዋዋሪ ነገር እያነሳ ሲጥል ወይም በሶስተኛ ወገን እንዲመሰከርለት ሁኔታዎችን ሲያመቻች ይታያል፡፡ ይሄኛው ናርሲሲስት ከቁጥጥር ውጭ ካልሆነበት በቀር ንዴቱን ባብዛኛው የሚገልፀው ያበሳጨውን ሰው ለረጅም ጊዜ ዝግት አድርጎ በመዝጋት ነው፡፡ ምንም እንኳን ሁሉም ናርሲሲስቶች (ግልፅ እና ድብቁን ጨምሮ) ራሳቸውን ከሌሎች በተለይ ከፍ አድርገው የሚያዩ፣ የማያቋርጥ ተደናቂነትን የማግኘት ፍላጎታቸው ያየለ እና ለሌሎች ስሜት ቅንጣት ታህል ደንታ የማይሰጣቸው ቢሆኑም ይህንኑ ባህሪያቸውን እንዳካተቱ ሆነው በተጨማሪ ከሚያሳዩዋአቸው ሌሎች ባህርያት በመነሳት ለአራት ተከፍለዋል፡- 1.መልኬ በቃኝ (Somatic Narcissist)

  • መልኬ በቃኝ ናርሲሲስቶች የሚያሳዩዋቸው ለየት ያሉ ባህሪዎች፡-

  • ከአንድ በላይ የፍቅር ጓደኞችን ደራርበው ይይዛሉ (ይህንን እንደስኬት ይቆጥሩታል)

  • ቶሎ ስለሚሰለቹ የፍቅር ጓደኞቻቸውን ባጭር ጊዜ ይቀያይራሉ

  • ከሩቅ ሲታዩ በጣም የሚስቡ እና የሚወደዱ አይነት ናቸው

  • ኑሮአቸውን እስኪያቃውስ ድረስ ገንዘባቸውን ውድ የሆኑ ቁሳቁሶችን በመግዛት መጨረስ (መኪና፣ ልብሶች፣ ሰአት፣ ወ.ዘ.ተ.). ይህን የሚያደርጉት የሰውን ትኩረት እንዲስብላቸው እና ስኬታማ መስሎ ለመታየት ነው፡፡

  • ለመልክና አቋማቸው የተለመደ ወይም ሊሆን ይገባዋል ከምንለው በላይ እንክብካቤ ያደርጋሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ጂምናዚየም ውስጥ በየቀኑ ለረጅም ሰአታት ጡንቻቸውን ለመገንባት ጎንበስ ቀና ሲሉ በብዛት ይታያሉ፣ ወንድ ሆነው ቅንድባቸውን ሲቀነደቡ ይታያሉ፡፡

  • የሚያደርጉት ነገር ሁሉ በሆሊዉድ የምናያቸውን ታዋቂ ሰዎች የአኗኗር ዘይቤ እንደመነሻነት የያዘ ይመስላል፡፡

ትኩረት ለመሳብ የሚያደርጉት ጥረት ላስተዋለው በግልፅ ወጣ ብሎ ይታያል፡፡ 2.አዋቂ ከእኔ ወዲያ (Cerebral Narcisists)

  • እነዚኛዎቹ ደግሞ በእውቀታቸው፣ ወሳኝ ከተባሉ ሰዎች ጋር ባላቸው ግንኑነት እና በስኬታቸው የሚመኩ ናቸው

  • እንደ መልኬ በቃኝ ናርሲሲስቶች እነዚኛዎቹ ሴት አውል አይደሉም (በተቃራኒው የፍቅር ወይም የትዳር ጓደኞቻቸው እንኳን በፍቅር ግንኑነት ማነስ ቅሬታ ያሰማሉ)

  • በልጅነት የነበረባቸውን እጥረት ለመሸፈን ይመስላል ከፍተኛ ስኬት ላይ ለመድረስ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡

  • ገንቢ አስተያየት ሲሰጣቸው የተሰደቡ ያህል ስለሚሰማቸው ያበሳጫቸዋል፡፡

  • የቅርባቸውን ሰዎች ስሜት በመጉዳት እና ተፅእኖ በማሳደር ሊቆጣጠሯቸው ይሞክራሉ

3.እውቀት ከመልክ ጋር (the Elitist Narcissist) የነዚኛዎቹ ባህሪ ከመልኬ በቃኞቹና አዋቂ ከእኔ ወዲያ የሚሉትን ናርሲሲስቶች ባህሪ ቀላቅሎ የያዘ ነው

  • በአይምሮአቸው እና በእውቀታቸው ይመካሉ፣ ሴት አውልም ናቸው፡፡

  • በስኬት ከላይ በመሆን ሌሎችን ከስራቸው ለማየት ይተጋሉ

  • ከማንኛውም ሰው በላይ የተሻሉ እንደሆኑ ያምናሉ (በስኬትም ሊሆን ይችላል ወይ ደግሞ ከአፈጣጠራቸው)

  • የይገባኛል ስሜታቸው በስራም ሆነ በግል ህይወታቸው ላይ ይንፀባረቃል

  • ራሳቸውን በመቆለል፣ ስለስኬታቸው ጉራ መንዛት እና ከሌሎች የተሻሉ መስለው መታየትን ያውቁበታል

4.ክፋተኛው ናርሲሲስት (Malignant Narcississt) እነዚህኛዎቹ ናርሲሲስቶች ከህብረተሰቡ የተለየ ባህሪ የማሳየት የስብእና ችግር (Antisocial Personality Disorder) ካለባቸው ሰዎች ጋር ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው

  • የሚያሳዩት ባህሪ ትክክለኛ ነው ወይም አይደለም ብለው አይጨነቁም

  • ለሚሰሩት ጥፋት መፀፀት አያውቁም

  • ጉረኛና ለራሳቸው ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጡ ናቸው

ሌሎችን በማታለል ወይም በመጉዳት ይደሰታሉ

source - yineger


40 views0 comments
bottom of page