• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የ80 ዓመት አዛውንት እና ዶክተሩየ80 ዓመት አዛውንት እና ዶክተሩ

የ80 ዓመት አዛውንት ለጠቅላላ የጤና ምርመራ (Checkup) ሆስፒታል ይሄዱና ሃኪማቸው “እንዴት ነው ጤንነትዎ?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ ሽማግሌውም “በጣም ጤና ነኝ ---እንደውም የ18 ዓመት ኮረዳ አግብቼልህ አርግዛልኛለች----ልጅ ላገኝ ነው --- መታደል ነው አይደል?” ይሉታል ለሃኪሙ፡፡ ሀኪሙ ነገሩ አልተዋጠለትምና ትንሽ ሲያስብ ከቆየ በኋላ “አንድ ታሪክ አስታወሱኝ” በማለት ይነግራቸዋል፡፡ “አንድ እኔ የማውቀው አደን የሚወድ ሰውዬ ነበር፡፡ በቃ የአደን ነገር ጨርሶ አይሆንለትም፡፡ አንድ ቀን ለአደን ሲወጣ ታዲያ ጠብመንጃውን አነሳሁ ብሎ ዣንጥላውን ይዞ ይወጣል፡፡ ገና ጫካ ውስጥ እንደገባም ከየት መጣ ሳይባል አንድ የተበሳጨ ድብ ፊትለፊቱ ገጭ ይልበታል፡፡ ከመቀፅበት ዣንጥላውን እንደጠመንጃ አስተካክሎ ድቡ ላይ ያነጣጥርበትና እጀታውን ይጫነዋል----ድቡ ወዲያው መሬት ላይ ጠብ ይላል” አላቸው ሃኪሙ፡፡ ሽማግሌውም “ይሄማ ሊሆን አይችልም! ድቡ ላይ የተኮሰው ሌላ ሰው መሆን አለበት!” አሉ - ጮክ ብለው፡፡ ሀኪሙም “የእርስዎም ነገር እኮ እንደዚያ መስሎኝ ነው” አላቸው፡፡


32 views0 comments

Recent Posts

See All