top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

አስም ምንድን ነው? እንዴት ነው የሚይዘን? ለምን ያህል ግዜ ይቆያል?



አስም ምንድን ነው? እንዴት ነው የሚይዘን? ለምን ያህል ግዜ ይቆያል?

አስም ሳንባችን እና የትንፋሽ ቧምቧችንን ለረጅም ግዜ አጥቅቶ የሚቆይ የበሽታ አይነት ሲሆን ከ100 ሰው አምስቱ በበሽታው ይያዛል።

የአስም ምልክቶች ትንፋሽ ማጠር፣ የደረት መጥበቅ፣ ሲተነፍሱ ማፏጨት እና ሳል ናቸው። እነዚህ ስሜቶች የሚመነጩት የመተንፈሻ ቧምቧችን ሲጠብ ወይም ሲቃጠል ነው። በአንዳንድ ሰዎች ላይ እነዚህ ስሜቶች በቋሚነት ሲከሰቱ ሌሎች ላይ ግን ህመሙ በሚነሳበት ወቅት ብቻ ያጋጥማሉ።

አስም እንዴት ነው የሚይዘን?

አስም በየትኛውም እድሜ ሊይዘን ይችላል። ለምን በአንዳንድ ሰዎች ላይ ተከስቶ ሌሎች ላይ እንደማይከሰት እስካሁን አይታወቅም። አስም ያለባቸው ሰዎች የትንፋሽ ቧምቧቸው ለህመሞች ተጋላጭ ነው።

  • ቤተሰብ ውስጥ አንድ ሰው አስም ካለው ሌሎች ላይ የመኖሩ እድል ከፍ ይላል

  • የአስም ህመም በቀዝቃዛ አየር፣ ከባድ የአካል እንቅስቃሴ እና በጭንቀት ሊነሳ ይችላል

  • አለርጅን ተብለው የተጠቃለሉ በአካባቢያችን የሚገኙ ኬሚካል ይዘት ያላቸው ንጥረ ነገሮች ህመሙ እንዲነሳብን ያደርጋሉ

  • የአበባ ዱቄት፣ የእንስሳ ጸጉር፣ አቧራ፣ አንዳንድ ምግቦች፣ ሽቶ፣ ሲጋራ ጭስ እና የመሳሰሉት ንጥረ ነገሮች አለርጅን ሊሆኑ ይችላሉ

  • እነዚህ አለርጅኖች የትንፋሽ ቧንቧችን እንዲያብጥ እና የቃጠሎ ስሜት እንዲሰማው ያደርጋሉ። የበለጠ አክታ እንድናመነጭ እና የትንፋሽ ቧንቧ ጡንቻዎች እንዲጠብ ምክንያት ይሆናል። አየር በቀላሉ ማስገባት እና ማስወጣት አንችልም

  • የደረት ኢንፌክሽን ያለባቸው ላይ ህመሙ ይጠናል

አስም ምን ያህል ሊያሳስበን ይገባል?

አስም በብዙ ጤና ባለሙያዎች እንደ ከባድ ህመም አይታይም። የህመሙ ስሜት ከባድ አለመሆን እና ህመሙን በቀላሉ መቆጣጠር የሚያስችሉ ህክምናዎች መብዛት ከባድ ህመም ተብሎ እንዳይፈረጅ ምክንያት ሆኗል። ቢሆንም ግን አስም በቂዉን ክትትል ካላገኘ ኑሮአችንን ያውካል። አብዛኛው ሰው የአስም በሽታን ተቆጣጥሮ መኖር ይችላል። ነገር ግን በጥቂት ሰዎች ላይ በሽታው ለህይወት የሚያሰጋ ሁኖ ይገኛል። በተለይ ደግሞ ህመሙ ሲነሳ ወድያው ክትትል ካላገኘ። ለነዚህ ሰዎች ህመሙ ሲነሳ ከመክበዱ የተነሳ ሞት ሊከተል ይችላል።

አስም ለምን ያህል ግዜ ይቆያል?

የአስም ህመም እየመጣ የሚሄድ አይነት ህመም ነው። የሚሰሙን ህመሞች ከግዜ ግዜ ይለያያሉ። ቡዙ ሰዎች ዘንድ ህመሙ አልፎ አልፎ የሚመጣ ነገር ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ግን በየቀኑ ይታመማሉ። የምናደርገው ህክምና የህመሙን ስሜት በማስታገስ አንድ የህመም ዙር ለተወሰኑ ሰአታት ወይም ደቂቃዎች ብቻ እንዲቆይ ማድረግ ይችላሉ። ያለህክምና ህመሙ ለቀናት የሚቆይበት ሁኔታ አለ። አንዳንድ ልጆች እድሜአቸው ሲጨምር ህመሙ ይለቃቸዋል። አንዳንድ ሰዎች ህመሙ የሚጀምራቸው በተወሰነ የአመት ወቅት ሲሆን ለረጅም አመታት ብቻ ወይም ሙሉ ህይወታችንን ሊዘልቅብን ይችላል።

ህመሙን እንዴት መቆጣጠር ይችላል?

አስምን የሚያድን መድሃኒት የለም። ነገር ግን በሽታውን ለመቆጣጠር የሚረዱ መድሃኒቶች አሉ። ህመሙ ሲከሰት ስሜቱን የሚያስታግሱ መድሃኒቶች እና በህመሙ ወቅት ለመተንፈስ የሚረዳ ኢንሄለር በመጠቀም የህመሙን ስሜት ማስታገስ እንችላለን።

ምንጭ - ጤነኛ ድረ ገጽ


55 views0 comments
bottom of page