የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
የሼህ ሁሴን ጅብሪል - ትንቢታዊ ግጥሞች ( ክፍል-09 )

53.መምጣቴን ሰምተው ልደር ካሉ ቄሱ ሐለቴን ያውቃሉ ጣይቱን ያስታውሱ አዱርስ ጨሰ ብለው እንዳይወሰውሱ ጫት በአፋችን ከያዝን ጠጅን እንዳቀምሱ ዋሪዳው ይማታል አይወድም መጅሊሱ::
54. የነብስ አባትዎ ከሆኑ እኚህ ቄስ ቁጭ ብለው ይደሩ ከእኛ ጋር መጅሊስ መውደድስ አትወዱም ጳጳስና ቄስ ግን ለአጼ ምኒልክ እንዲላቸው ደስ ሰው ዝም ብሎ ያድራል እንኳን ሊደግስ::
55. አርባ ጊዜ መጣሁ የልብህ ይድረስ ፊትም ዱአ አርገናል አንተ እንድትነግ፣ ቀልብህ ደኅና ቢሆን ብትወድ መጅሊስ ገርፈህ ባትሰቅል እንደ ዮሐንስ ስንቱ እስላም ወደደህ ሁሉን አለው ደስ::
56. ጎጃም ተክለ ሃይማኖት ጎንደር እራስ ተሰማ (ትግራይ እነ ራስ አሉላ አባ ጅፋር ጅማ ሐረር ራስ መኮንን ዘራቸው የገማ እኔ ተናገርኩኝ ያልሰማህም ስማ ከጉግሣ ዘር በቀር የለም የሚለማ::
57. መች ባንተ ይሆናል ምኒልክ ንጉሡ አንተ አስበህ ነበር ልትሰጥ ለእያሱ እንኳን ሊነግሥና ይያዛል ለራሱ በራስ መኮንን እጅ ትጠፋለች ነብሱ ከጌታ ተፈርዷል አርደውት ሊነግሥ::
58. ከገረድ ተወልዶ እደግ ብንለው ጥንብ አቀረበልን እዩት ይህን ሰው ከሸዋረጋ ፊት አሁን ላዋርደው ልልክበት ነበር ዳግሚያ እንዳይለምደው አይለምደውም ነበር ቄስ ወርቁን ቢያየው።
59. ወይ መሐመድ አሊ ምን ሆኗል ይኸ ሰው በድየው እንደሆን ልጠየቅ በሰው በዮሐንስ ጠበል ዲኑን ሲያረክሰው ጥፋት በእሱ ሆኖ ተገኘበት ይህ ሰው ኋላ ብትሞት ማነው የሚዋሰው? 60. ጠጅና ሥጋህን ከፊቴ ላይ አንሣ እኔ በበሬ ሽንጥ ሰውነቴ አይሳሳ በአንድ ቀን ተርቤ ሰውነቴ አይከሳ አላህ የጠላውን አልበላም ነጃሳ ወንዝ ለወንዝ ሄጀ እበላለሁ ዓሣ::
61. አንተ ብታፈቅረኝ እኔ ብወድህ አትቆጣም ብዬ እኔም አንተ አልኩህ እንዳይደነግጡ የነብስ አባትህ ከመጅሊስ ካልሆነ እኔም አልደፍርህ አንተስ ምን ትስተው እኔ ባልነግርህ?