የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
አቅም እያለህ ዝለል! / jump when you have the power!

ውሃ በተሞላ ድስት አንዲት እንቁራሪት ብንጨምርና ከዛም ውሃውን ማፍላት ብንጀምር ፤ ውሃው እየፈላ በሄደ ቁጥር እንቁራሪቷም የሰውነት ሙቀቷን ማስተካከል ትጀምራለች፡፡
የውሃው ሙቀት ከፍተኛ እየሆነ ሲሄድ እሷም የሰውነቷን ሙቀት በዛው ልክ ማስተካከሉን ትቀጥላለች፡፡ የውሃው ሙቀት ጨምሮ የመፍላት ነጥብ (boiling point) ላይ ሲደርስ ግን ማስተካከል የማትችልበት ደረጃ ስለደረስ እሯሷን ለማዳን ከድስቱ ዘላ ለመውጣት ትፈልጋለች ትሞክራለች፤ ግን ዘላ መውጣት አቅም አይኖራትም አትችልም፡፡ ምክንያቱም ያላትን አቅም ሁሉ ሙቀቷን በማስተካከል የውሃውን ቃጠሎ ለመከላከልና ለመላመድ ባደረገችው ተጋድሎ ጨርሳዋለችና፤ ወድያው ትሞታለች፡፡
እንቁራሪቷን ምን ገደላት? / What killed the frog? *** አብዛኞቻቸችን የፈላ ውሃ እንል ይሆናል፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም :: እንቁራሪቷን የገደላት የፈላው ውሃ ሳይሆን መች መዝለል እንዳለባት የመወሰን እቅም ማጣቷ ነው፡፡ አብዛኞቻችን ከሰዎችም ይሁን ከነገሮች ጋር ያለንን ነገር ለማስተካከልና ለመላመድ እንሞክር ይሆናል፤ ግን እስከመች ማስተካከል እንዳለብንና መች መወሰን እንዳለብን ማውቅ ይሳነናል፡፡
አንዳንዴ ነገሮችን የለመድናቸውና ለኛ የማይጎዱ መስለው ይታየናል፤ በመጨረሻው ቅፅበት ግን እንዳለመድናቸው ቢገባንም ማመልጥና መውጣት የማይቻለን ሰዓት ይሆናል፡፡ በጥፋት/ወንጀል መንገድ ውስጥም ስንሆን እንዲሁ ነው ፤ ትንሹን ወንጀል እንለምደዋለን የሚጎዳን አይመስለንም ፤ ደስታ ውስጥ ያለን ይመስለናል ፤ ደስታው ሙቀት ይፈጥርልናል፡፡ ሙቀቱ ወደ እሳት የተቀየረ ጊዜ ግን. . . . . . . .ጉድ ነው፡፡
ሙሉ አቅም ባለን ጊዜ እንዝለል !!! / Let us decide when to jump!
Let's jump while we still have the strength.
ምንጭ-ጉግል