• የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር!

Updated: Jun 26, 2019

“ደግነት አይለይህ!”

ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው፤ “ያስከፍላል” ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ።

እናም ዘወትር ደግ ሁን፤ ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም፤ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸውና ሰላማቸው ልክ የለውም።

“ደስታህንና ሰላምህን ካንተ ዘንድ አኑራቸው!”

ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ!” ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው።

በራስህ በአፈጣጠርህ→ደስ ይበልህ፤ ውለህ በመግባትህ→ደስ ይበልህ፤ በአለህ ትንሽ ነገር→ደስ ይበልህ።

“ፍቅርን ፈልጋት!”

ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም።

“ዘመንህን ከርኩሰት ጠብቀው!”

እድሜህን በተመለከተ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው።

ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳየኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።

“መኖርህ ማንንም ካልጠቀመ መሞትህ ማንንም አይጎዳም” የሚለውን አባባል አስታውስ!”

የኖሩበት እድሜ ትንሹም ቢሆን በቂ ነው ይባላል። የማቱሳላ እድሜው እንጅ የሰራው ስራ አይታወቅም፤ “ኖሮ ሞተ” ብቻ ከመባል ፈጣሪ አምላክ ይጠብቅህ፤

መኖርህ ሰዎችን ካልጠቀመ መሞትህ ላይጎዳቸው ይችላል፤ መኖር ማለት መጥቀም መጠቃቀም ነው።

“ከማማረር ማመስገንን ልመድ!”

የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ረስተን፣ ያልጎደለን ነገር ላይ “ጎደለን” ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው፤ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል።

በማማረር መባረክ የለም። ሰላምና ጤና፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለይ።

ለውጥ ከራስ ይጀመራል! እናም አሁኑኑ መለወጥን ጀምር።


ከጌጡ ተመስገን ድረ ገጽ የተወሰደ

33 views0 comments

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean