top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ" - (በእሙ ኢሳን)


ተልባው ተንጫጭቶ

በጅብ ችኩል ስሜት ተገፋፍቶ

አለማወቁ እጅግ ከፍቶ

ምቀኝነቱ በሁለመናው ተንሰራፍቶ

በእኩይ ተግባሩ ተሰማርቶ

የሚተጋውን አንቋሾ - ተችቶ

ባልተዋለበት ስም አውጥቶ - ሰጥቶ

ንጹውን አቆሽሾ - አከርፍቶ

ታላቅ አዋቂውን ገፍቶ

እንዳዋቂ ሞግቶ

መሰሎቹን አፍርቶና አበርክቶ

ለያዥ ለጋባዠ እረፍትና እንቅልፍ ነስቶ

አረፋ እስኪደፍቅ ፎክሮና አቅራርቶ

በደቦ በየጥሻው ተሸጉጦና ተደራጅቶ

የከረመውን የነገር ዱቄት አሽቶና አብኩቶ

ለመጋገር እሳት ለኩሶና ተዘጋጅቶ

ለምን ይሆን ግን ተልባው መራኮቱ

መና ሊቀር ልፋቱ

ሊወቀጥ በሙቀጪቱ!


በእሙ ኢሳን

ሪያድ ሳኡዲ አረቢያ

64 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page