top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ለምንድነው የምንስቀው? ስነ ልቦናዊ ምክኒያቶች – ዶ/ር ዮናስ ላቀው

ለምንድነው የምንስቀው?
ለምንድነው የምንስቀው?

አንድ ሰው በአማካይ በቀን ከስድስት እስከ አስር ጊዜ ይስቃል፡፡ ሳቅ ምንድነው? ለምንድነው የምንስቀው?

የምንስቀው በተለያዩ ስነ ልቦናዊ ምክኒያቶች ሲሆን ለዛሬ ዋነኛ የሆነውን ኩታ ገጠም አልተግባብቶ (Incongruent juxtaposition) እናያለን፡፡

ኩታ ገጠም አልተግባብቶ ሁለት የማይስማሙ ነገሮች አጠገብ ለአጠገብ ሲመጡ ማለት ነው፡፡ በቃላት ለምሳሌ የሰላም ዘመቻ፣ አባባ አቡሽ…ወዘተ፡፡

ወይም በገጽታ ለምሳሌ አጭሩ አቢሎ እና ረጅሙ አስራት አጠገብ ላጠገብ ስናያቸው የሚፈጥረው አልተግባብቶ እንድንስቅ ያደርገናል፡፡

አቢሎ መካከለኛ ቁመት ካለው ሰው አጠገብ ቢቆም ኩታ ገጠምነቱ አለ አልተግባብቶሙ ግን ዝቅተኛ ስለሆነ አያስቅም፡፡

(ለአዲሱ Generator ትውልድ ኩታ ገጠም ማለት አጠገብ ላጠገብ ማለት ነው፡፡)

አእምሯችን ሁለት የማይሆኑ/የማይግባቡ ሀሳቦች ሲገጥሙት ውጥረት ውስጥ ይገባል፡፡

በዚህ ጊዜ የመተንፈሻ አካላትን በማንቀሳቀስ በሳቅ ያረግበዋል፡፡ ሳቅ የደስታ ስሜት ይፈጥራል፡፡

ስለዚህ ሳቅ ለአካልም ሆነ ለአእምሯችን ጤንነት በጣም አስፈላጊ ነው

አልተግባብቶምን በሀሳብ ደረጃ የሚያሳዩ ሁለት ምሳሌዎች፦

ሁለት ሌቦች ተይዘው ፍ/ቤት ይቀርባሉ፡፡ ዳኛው የመጀመሪያውን ሌባ ኮስተር ብለው “አድራሻ?!” ይሉታል፡፡

ሌባውም “ክቡር ዳኛ ወንድ ልጅ ምን አድራሻ አለው፡፡ አድራሻዬ ሜዳው፣ ተራራው፣ ገደሉ፣ ሸለቆው ነው፡፡” ይላቸዋል፡፡

በጣም ተናደው ወደ ሁለተኛው ሌባ ዞረው “የአንተስ አድራሻ?!” ሲሉት ወደ ጓደኛው እየጠቆመ “የሱ ጎረቤት ነኝ፡፡”

አንዲት የከተማ ልጅ ከአባቷ ጋር ከከተማ ውጭ እየሄደች ነው፡፡

አባቷን “አባዬ ያቺ ላም ቀንድ የሌላት ለምንድነው?” ብላ ጠየቀችው፡፡

አባቷም “ልጄ ላሞች በተለያየ ምክኒያት ቀንድ ላይኖራቸው ይችላል፡፡

አንዳንዶቹ በተፈጥሮ ቀንድ የላቸውም፡፡ አንዳንዶቹ ሰዎች ቀንዳቸውን ይቆርጡባቸዋል፡፡ ይ

ቺኛዋ ግን ቀንድ የሌላት በቅሎ ስለሆነች ነው፡፡”

መሳቅ የምታቆመው ስላረጀህ አይደለም፡፡ የምታረጀው መሳቅ ስላቆምክ እንጂ፡፡


እንሳቅ

መልካም ጊዜ

ከጌጡ ተመስገን ድረ ገጽ የተወሰደ

33 views0 comments
bottom of page