top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ላልተጣመረው እና ላልተዋሃደው ጉራጌ መጠሪያው ምን ይሰራለታል? (ኢዱና አህመድ)


ላልተጣመረው እና ላልተዋሃደው ጉራጌ መጠሪያው ምን ይሰራለታል? (ኢዱና አህመድ)

በሃገራችን የጉራጌ ህዝብን በተመለከተ ይህ ነው የሚባል የተጻፈ ታሪክ ባይኖርም የጉራጌ ህዝብ ከቀድሞው የሃገራችን የሰሜኑ ክፍል በተለይዩ ምክንያቶች እና ጊዜያቶች በመምጣት አሁን ላይ የጉራጌ ዞን ቦታዎች ላይ ሰፍሮ የሚገኝ ህዝብ ነው። ከየትኘው የቀድሞው ሃገራችን የሰሜን ክፍል የሚለው የሚነሳ ቢሆን እንኳን ሆድ እንዲፈጀው ይሁንና የተነሳሁበት አላማ ቀደም ብሎ እና አሁን ላይ ጉራጌ በሚል ስያሜ የተጠቃለሉት ህዝቦች ስላላቸው እና ስለ ሌላቸው ማህበራዊ ትስሰር ለማጉላት ብቻ ነው። ታሪክን ለታሪክ ጸሃፊዎችና አዋቂዎች እንተውላቸው። እነርሱ በእነርሱኛው እንደሚሉት ይበሉ።

ጉራጌ ዞን “ጉራጌ” በሚል ስያሜ የተጣመሩ፣ የተለያየ እና በተወሰነ መልኩ ተቀራራቢ የሆኑ ቋንቋዎቹን የሚናገሩ ነገር ግን በምዕራብ ጉራጌ ዞን የሚገኙት ጉራጌዎች ከምስራቁ ዞን ውስጥ ከሚገኙት ጋር ምንም አይነት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር የሌላቸው ከመሆኑ ባሻገር የምዕራቡ ዝርያ ያላቸው ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ቀን ከሌት የምስራቁን አካባቢና ተወላጆች መልካም የሆነውን ሁሉ ለማበላሸት ኮሚቴ ሰይመው እና በጀት በጅተው የሚንቀሳቀሱ ሆነው ቆይተዋል።

ጉራጌ በሚል ስያሜ የተጣመሩት ህዝቦች እንደሚከተሉት ይሆናሉ።

1. ሰባት ቤት ጉራጌ

2. መስቃን

3. ሶዶ ክስታኔ


ትንተና በግርድፉ

  1. ሰባት ቤት ጉራጌ በጉራጌ ዞን የምዕራቡ ክፍል የሚገኝ ማህበረሰብ ሲሆን ሰባት ቤት ጉራጌ ወይም ሰባቱ የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ጎሳዎች ነገር ግን ሰባት ቤት ጉራጌ በሚል ስያሜ የሚጠሩ ናቸው። ከምን አንጻር ሰባት ቤት እንደተባሉ፣ ሰባት እና ቤት የሚለውም እንዴት እና ለምን ከስያሜው ጋር እንደተካተተ እሰከ ዛሬ ግልጽ አይደለም። በተጨማሪም ሰባቱ ጎሳዎች በመጣመር እራሳቸውን ሰባት ቤት ጉራጌ በሚል መሰየማቸው ጉራጌ የሆኑት ሰባቱ ብቻ ናቸውን? በማለት እንድንጠይቅ ያስገድደናል። ህዝቡ እንደ ህዝብ እጅግ ታታሪ እና ሰላማዊ ነው። ህዝብን መፈረጁ ቢከብድም የእነርሱን ክፉዎችን እምቢኝ በማለት ከምስራቅ ጉራጌው ጋር የተሻለ ማህበራዊ ግንኙነት ማስረጽ አለመቻላቸው በራሱ ብቻ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።

  2. የመስቃን ህዝብ መስቃንኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ እና በአሁኑ በምስራቁ የጎራጌ ዞን ወይም በድሮው ሐይቆችና ቡታጅራ አውራጃ ሰፍረው የሚገኙ ህዝቦች ናቸው። የመስቃን ማህበረሰብ ከ62 በላይ የራሱ የሆኑ ጎሳዎችን ያቀፈ ሲሆን በሃገራችን የብሄር መስፈርቱ ግልጽ ባይሆንም ጉራጌ በሚል ስያሜ ተጨፍልቆ ይገኛል። የመስቃን ህዝብ በመስቃን ወረዳዎች ዙሪያው ከሚገኙት ብሔረሰቦች (ስልጤ፣ ማረቆ፣ ሶዶ ክስታኔ እና ወለኔ) ለዘመናት እጅግ እና ጥልቅ የሆነ ማህበራዊ ትስስር ኖሮት በጋብቻ ተሳስሮ የሚኖር ህዝብ ሲሆን በምእራብ ጉራጌ ዞን ካድሬዎች ጠንሳሽነት በተወሰነ መልኩ ከማረቆ ማህበረሰብ ጋር ግጭቶች ቢከሰቱም አብሮ የመኖር እሴቱ ጠብቆ እየኖረ የሚገኝ ታታሪ፣ የዋህ እና አትንኩኝ ባይ የሆነ ፍጹም ሰላማዊ ህዝብ ነው።

  3. የሶዶ ክስታኔ ህዝብ የሶዶ ክስታኔኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ በአሁኑ በምስራቁ የጎራጌ ዞን ወይም በድሮው ሐይቆችና ቡታጅራ አውራጃ ሰፍረው የሚገኙ ህዝቦች ናቸው። አጎራባች ከሆኑ ህዝቦች ከኦሮሞ ፣ ወለኔ፣ መስቃን እና ማረቆ ጋር ጥልቅ የሆነ ማህበራዊ ትስስር ኖሮት እና በጋብቻ ተሳስሮ የሚኖር ህዝብ ነው። ሶዶ ብልህ እና ታታሪ ህዝብ ነው። ሶዶ በአቋሙ የጸና ለእምነቱና ለአካባቢው ታማኝ የሆነ ህዝብ ነው። ሶዶ ክስታኔ ሌላውን አይነካም። የራሱንም አሳልፎ አይሰጥም።


ከስያሜው በቀር ማህበራዊ በሆኑ ጉዳዮች ሁሉ ላልተጣመረ እና ላልተዋሃደ ማህበረሰብ ጉራጌነቱ ወይም መጠሪያው ምን ይሰራለታል?


በነገራቸን ላይ በዳይን በተመለከተ ጊዜያችንን ስናባክን ያ… በዳይ ጡንቻው ፈርጥሞ እና በአቅሙ ገዝፎን ሌላው ደግሞ አቅመ ደካማ ሆኖ አይደለም። በዘር ፖለቲካ የእኔ የሚላቸውን በየቦታው ሰግስጎ በማሽቃበጥ መፈናፈኛ ስላሳጠ እንጂ።

ከማእከላዊ መንግሰት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የደቡብ ሸዋ ክልልላዊ መንግሰት ምስረታ እውን ይሆን ዘንድ ምኞቴ የገዘፈ ነው!!


ይቀጥላል…

ኢዱና አህመድ ኡስማን

65 views0 comments
bottom of page