top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ሐሳብ - ክፍል 5 (ኢዱና አህመድ)

Updated: Sep 30, 2023


ሐሳብ -ክፍል 5 (ኢዱና አህመድ)

ሃሳብን... በሃሳብ!

ሳስብ... ስብሰለሰል... በሃሳብ!

ያ… ሃሳብ መጣና “ እንደው የአህያ ባል ጉዳይ” አለኝ በሃሳብ

እኔም በሃሳቤ ብዬ አልኩት...

አወይ… አቅል ማጣት

አወይ… መንከራተት

ውሉ... በጠፋው ውጥንሽ

በድረሱልኝ ብቻ ጽናትሽ

ፍሬ ሳያፈራ አፈርሳታሽ

መና አጣና... በሬ ወለደሽ

በሰበቅ - ሰበቃው... ጤዛው ተነነ

ተረቱም… እውን ሆነ

የፈሩት... ደረሰ!

የጠሉትም… ወረሰ!

ያ… አህያው ባልሽ

ከጅብ አላስጣለሽ!

አየሽ… አለማስተዋልሽ

ባንጠለጠለ ብቻ መለካትሽ... መመዘንሽ

ስላንጠለጠለ… መኩራራትሽ

ቅንነት ባህላችን ነውና ምክርን ውሰጂ

አህያ መላ አያውቅም ልፋት ብቻ ቢሆን እንጂ!

አህያ መላ አያውቅም ልፋት ብቻ ቢሆን እንጂ!

እያልኩኝ ሃሳብን... በሃሳብ!

ሳስብ... ስብሰለሰል... በሃሳብ!

ያ... ሃሳበ መጣና በሃሳብ... መለሰኝ ከሃሳብ


ኢዱና አህመድ ኡስማን

ሪያድ ሳዑዲ አረቢያ

114 views0 comments
bottom of page