top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

“መስማት በሌለብህ ሰዐት ደንቆሮ ሁን”


“መስማት በሌለብህ ሰዐት ደንቆሮ ሁን”
“መስማት በሌለብህ ሰዐት ደንቆሮ ሁን”

አንድጊዜ የእንቁራሪቶች ቡድን በጫካ ውስጥ እየተጓዘ እያለ ሁለቱ እንቁራሪቶች ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ ፡፡ ሌሎቹ እንቁራሪቶች በጉድጓዱ ዙሪያ ተሰብስበው ምን ያህል ጥልቀት እንዳለው ባዩ ጊዜ ምንም የመውጣት ተስፋ እንደሌላቸዎ ለሁለቱ እንቁራሪቶች ነገሯቸው ፡፡

ነገርግን ሁለቱ እንቁራሪቶች የሌሎችን እንቁራሪቶች ጩኸትና አጉል ጫጫታ ችላ በማለት ከጥልቁ ጉድጓድ የሚወጡበትን መፍትሄ ማፈላለግ ጀመሩ ፡፡

አሁንም ከጥልቁ ጉድጓዱ አናት ላይ ያሉ የእንቁራሪቶች ቡድን ሁለቱን እንቁራሪቶች ምንም ተስፋ የላችሁም የጉድጓዱ ጥልቀት በጣም ከፍተኛ ስለሆነ ምንም የመውጣት ተስፋ እንዳታደርጉ እያሉ መጮኻቸውን ቀጥለዋል፡፡ በጭራሽም ለመዝለል እንዳትሞክሩ የሚሉምነበሩ፡፡

በመጨረሻም አንደኛው እንቁራሪት ሌሎቹ የሚናገሩት እውነታቸውን ነው ከዚህ ጥልቅ ከሆነ ጉድጓድ ለመውጣት መሞከርከሞኝነትም ጅልነት ነው በማለት ምንምአይነት የመውጣትም ተስፋ እንደሌለው ራሱን አሳምኖ ሞቱን መጠባበቅ ጀመረ፡፡ ሌላኛው እንቁራሪት ግን የቻለውን ያህል መዝለሉን ቀጠለ ፡፡ አሁንም ዘለለ። ከጫፍ ያሉት እንቁራሪቶች ጩኸት ግን ቀጥሏል ወዳጃችን አጉልየሆነ ህመም ለምን ትጭምራለህ እንደፈረደብህ እዛው አርፈህ ሙት በማለት በከፍተኛ ጩኸት ተናገሩ፡፡እንቁራሪቱ ግን የመጨረሻ ያለውን እንጥፍጣፊ ሀይል በመጠቀም ከፍ ብሎ በመዝለል ጥልቅ ከሆነው ጉድጓድ ለመውጣት ቻለ፡፡ እንቁራሪቱ ጥልቅ ከሆነው ጉድጓድሲወጣ ሌሎቹ እንቁራሪቶቹ በመገረም ጥልቅ ከሆነው ጉድጓድ ትወጣለህ ብለን አልጠበቅንም ነበር አሉት። እንቁራሪቱ የሚሉትን ስላልተረዳ መስማት የተሳነው ወይም ደንቆሮ መሆኑንከነገራቸው በዃላ ፡፡ እናንተ ከላይ ሆናችሁ አፋችሁን ስትከፍቱ እና ስተወራጩ እያበረታታችሁኝ ስለመሰለኝ ያለ የሌለ ሃይሌን በመጠቀም ከጉድጓዱ ለመውጣት ቻልኩኝ አላቸው፡፡

ከዚህ… ታሪክ የምንማረው ትልቅ ነገር አለ። የሰዎች ጫጫታናአጉል ጩኸት በእርስዎ ህይወት ላይ በተወሰነ መልኩ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በየትኛውም መሰፈርት ቢሆን ከጉዟችን ሊገታን አይገባም።መስማት በሌለብህ እና በሌለበሽ ወይም በሌለባችሁ ሰዐት ደንቆሮ ሁኑ ወይም መስሚያችሁ ጥጥ ይሁን። ወደ አሰባችሁት አላማና ግብ ለመድረስ መሰናክል የሚሆን ገንቢ እና መልካም ያልሆነን ነገር አትስሙ። ያላችሁን እንጥፍጣፊ ሀይል ዘዴን በመጠቀም ልክ መስማት እንደተሳነው እንቁራሪት ከስኬታችሁ ጫፍ መድረስ ትችላላችሁ ።


ከፌስ ቡክ መንደር የተገኘ


59 views0 comments
bottom of page