top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

መስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት (Meskan Charity Organization)



የመስቃን በጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ መሰረት ምዝገባ አካሂዶ ከሰኔ 2011ዓ.ም ጀምሮ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ዓላማ በአካባቢያችንም ሆነ በሌሎች የአገራችን ክፍሎች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዙርያ የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ አገራችንን ከድህነትና ኋላ ቀርነት ማላቀቅ ነው።


በጎ አድራጎት ድርጅቱ እስካሁን ዋና ፅ/ ቤቱን በአዲስ አበባ እንዲሁም በቡታጅራና በሪያድ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን በመክፈትና በማደራጀት ረገድ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን የረመዳን ፆም ፍቺ/ ኢድ አልፈጥር ምክንያት በማድረግ ግንቦት 13 ቀን 2012 ዓ. ም 100 ባለ 10 ኪ.ግ የፍርኖ ዱቄት ምግብ የምስራቅ መስቃን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አህመዲን ደድገባ በተገኙበት በኢንሴኖ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የእርዳታ አስተባባሪ ግብረ ኃይል አስረክቦል። በዚህ አጋጣሚ ከበጎ አድራጎት ድርጅቱ ምስረታ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በምናደርገው እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋፅኦ እየደረጉ ላሉ የበጎ አድራጎት አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም በሪያድ ለሚገኘው ቅርንጫፍ ፅ/ቤታችን የላቀ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን ።


እንደሚታወቀው በ 2011 ዓ.ም በመስቃና ማረቆ ህዝቦች መካከል ፀረ ሰላም ኃይሎች በቀሰቀሱት ግጭት በርካታ ሰዎች ለሞት፣ ለአካል መጉደል እና መፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን እስካ አሁን ድረስ በጉራጌ ዞን፣ በምስራቅ መስቃን ወረዳ፣ በኢንሴኖ ከተማ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ 23, 500 ተፈናቃዮች በእለት ደራሽ እርዳታ ላይ ይገኛሉ። ስለሆነም ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ እነዚህ ወገኖቻችን በጊዚያዊነት ለመርዳትም ሆነ መልሶ እንዲቋቋሙ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ከመደገፍ አንፃር በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር (በሪያድ ፣በደቡብ አፍሪካ ፣በአውሮፓና በአሜሪካ እንዲሁም በመላው ዓለም) የምትገኙ የማህረሰቡ አባላትና ወገኖቻችን ለነዚህ ተፈናቃዮችና ተጎጂዎች የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።


ለበለጠ መረጃ

ስልክ ቁጥር + 251 983 754 146 ዋና ፅ/ ቤት: አዲስ አበባ

+ 251 913 444 368 ቅር ጫፍ ፅ/ ቤት: ቡታጅራ

48 views0 comments
bottom of page