top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ምላሴ – አፌ ላይ አለ – (ዶ/ር ዮናስ ላቀው)


ባለፈው የሄድንበት ቦታ የት ነበር? …እ .እ ምላሴ ላይ አለ፡፡ ከስሙ በስተቀር ሌሎች ዝርዝሮችን ልናስታውስ እንችላለን፡፡ ይህ በሳምንት አንዴ አብዛኛው ሰው ላይ የሚያጋጥም ነገር ነው፡፡ በስነ ልቦና የሚታወቅ ክስተት ሲሆን ሌቶሎጂካ (lethologica) ይባላል፡፡ እድሜ ሲጨምር እየተደጋገመ ይመጣል፡፡ በጊዜያዊነት አንድን ነገር መርሳታችንን ተከትሎ ለጥቂት ደቂቃዎችም ቢሆን በቃላት ለመግለፅ የሚያስቸግር የጭንቀት ስሜት ይፈጥራል፡፡

“ምላሴ/አፌ ላይ ነው።” ግን ምንድነው? ሌቶሎጃካ አለማቀፋዊና በሁሉም ቋንቋዎች የሚከሰት መረጃን ሸራርፎ ማስታወስ ነው፡፡

ቋንቋ ምንም ያህል የተወሳሰበ ሂደት ቢሆንም አእምሯችን ሀሳቦችን ወደ ቃላት በከፍተኛ ቅልጥፍና ስለሚለውጣቸው እንደስራ አንወስደውም(በብዛት)። ቃሉ ምላሳችን ላይ ሲሆን እንደምናውቀው እናውቃለን፣ የሰማንበት ቦታ ወይም የመጀመሪያዐው ፊደል ትዝ ይለናል፡፡ ግን ቃሉ የለም፡፡ ምክኒያቱ አእምሯችን የአንድን ቃል ድምፀቱን አንድ ቦታ፣ ፊደሉን ሌላ ቦታ፣ የሚወክለውን ሀሳብ ሌላ ቦታ ሴቭ ስለሚያደርግ ነው፡፡ በድንገት ይመጣልንንና ወይም ሰው ሲያስታውሰን ‘እፎይ’ እንላለን፡፡ ይህ ክስተት በሳይንሳዊ ስያሜው ሌቶሎጂካ ቢባልም በአማርኛ “ምላሴ/አፌ ላይ ነው፡፡” በትግርኛ “ኣብዛ ኣፈይ እያ ዘላ” በኦሮምኛ “arraba koo irra jira” ይባላል፡፡ በፈረንሳይኛም በኮርያኛም በሁሉም ቋንቋ ተመሳሳይ ምላሴ ወይም አፌ ላይ ነው የሚል ትርጉም ነው ያለው፡፡


አስተማሪ፡ H2SO4 የምን ፎርሙላ ነው?

ተማሪ፡ ምላሴ ላይ አለ፡፡

አስተማሪ፡ ሰልፈሪክ አሲድ ነው ያቃጥልኸል ትፋው፡፡


መልካም ጊዜ!


ምንጭ - ከገጡ ተመስገን ድረ ገጽ

29 views0 comments
bottom of page