top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ምርጫህን አስተካክል በመረጃና በምክንያት ወስን ዘመኑን ለማይመጥን ባህላዊ የምርጫ ቅስቀሳ ቦታ አትስጥ!


ቅጽ አንድ

በዚህ ሰነድ ዞናዊ አንድነታችንን የሚፈታተኑ ኢፍትሃዊነቶች በፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ይዳሰሳሉ

ያለንበት ሁኔታ በጨረፍታ

የጉራጌ ዞን ፖለቲካ ሁኔታ እጅጉን በሴራ የተሞላ ሲሆን የምስራቁ ቀጠና አንድ ሆኖ መብቶቹን እንዳይጠይቅ በየጊዜዉ የተለያዩ አጀንዳዎችን በመፈብረክ እርስ በርሱ ሲያጋጩት ቆይተዋል:: ብቻም አይደል ለዘመናት በጉራጌ ስም የሚጠየቁ ልማቶችን በፍትሃዊነት እንዳንጠቀም በመደረጋችን ወጣቶች ተመርቀዉ ስራ አጥ ሆነዋል:: የትምህርት አድል በአቅራቢዉ ባለመኖሩ በርካቶች ትምህርታቸዉን ማሻሻል ሳይችሉ ከጓደኞቻቸዉ በታች ሆነዋል፤ የንግዱ ማህበረሰብ ተጨማሪ ትላልቅ የመንግሰት ኢንቭትመንቶች በአካባቢዉ ባለመኖሩ ነግዶ ማትረፍ ተስኖታል፤ ስራ ፍለጋ የተደራጁ በርካታ ማህበራት ስራ የሚፈጥርላቸዉ የመንግስትና የግል ትላልቅ ኢንቭትመንቶች በአካባቢዉ ባለመኖራቸዉ እርስ በርስ ሽሚያና ግጭት ዉስጥ ገብተዋል::

በአጠቃላይ ባለፉት ግዜያት አካባቢችን በፖለቲካዉ በኢኮኖሚዉና በማህበራዊ እና ባህላዊ እሴቶቹና አቅሞቹ ልክ ጎልቶ እንዳይወጣ በማድረግ በፌድራልና በክልል መንግስት የሚገነቡ የህዝባችንን ልማት ፍላጎቶች የሚያሟሉ ተቋማት ሰፊዉን የቡታጅራና አካባቢዉ ህዝብ እየዘለሉ ባለስልጣን ያለበት ሰፈር ላይ ሲገነቡ ቆይተዋል:: ህዝባችን ግን በተፈጥሮ ልማትን ከየትኛዉም አካበቢ በላይ የሚወድ ቅን ለስራና ለለዉጥ ደፈ ቀና የሚል በመሆኑ ማንም በሚመሰክርለት ደረጃ እራሱን በራሱ በማሳደግና በመለወጥ አሁን ለደረሰበት ደረጃ በቅቷል:: ታዲያ እንደሌሎች አካበቢዎች ከፌድራልና ከክልል መንግስታት ትላልቅ የልማት አድሎች ተጨምሮለት ቢሆን በከፍተኛ ደረጃ የህዝባችን ተጠቃሚነት ይኖር ነበር፡፡ ይህ እንዳይሆን ግን ላለፉት 30 ዓመታት በጥቂት ሴረኛ የጉራጌ ካድሬዎች ምክንያት የህዝቡ ጥያቄ ሲደፈቅ ቆይቷል፡፤ የቡታጅራና አካባቢዉ ህዝብ የትኛዉም አካባቢ ያልሰራዉን የመንግስትን እጅ ሳይጠብቁ በራሳቸዉ ሃብትና ጉልበት የገነቡትን በስልጤና በጉራጌ ዞን ደረጃ የመጀመሪያ የነበረዉን የቡታጅራ ሆስፒታል ወደ ሪፈራልና ሰፔሻላዝድ ማሳደግ ሳይቻል ከሱ በኋላ አዲስ የመጡት እንዲያድጉ ተደርጓል፡፡ ሌላዉ ደግሞ በ1989 የተገነባዉንና ለስልጤና ለጉራጌ ህዝብ ጭምር አንድ ለናቱ የነበረዉ የመጀመሪያዉ የቡታጅራ ቴክኒክና ሙያ ተቋም ሳይሻሻል ለረጅም ግዜ ባለበት እንዲቆይ ተደርጎ ከሱ በዋላ በየገጠር ወረዳዉ የተገነቡና የተሰሩት ኮሌጅና ፖሊ ቴክኒክ ሆነዉ አድገዉ ወጥተዋል በብዙ ክርክርም ባለፈዉ አመት ፖሊ ቴክኒክ እንዲሆን ተደርጓል ያም ሆኖ የተሟላ የበጀት የመሳሪያ አቅም ስለሌለዉ የድግሪ ፕሮግራም መስጠት አልቻለም፡፡

አጭር አሳቢ ሆነን እንጂ ለቡታጅራ የመጣዉ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እኛጋ ካልተገነባ ቡታጅራ አይሰራም በማለታቸዉ ወደ ሆሳዕና ሲሄድ በተመሳሳይ ሁኔታ የመምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅም ወደ ቦንጋ እንዲሄድ የተደረገበት መንገድ የማንረሳዉ ትዉስታችን ነዉ፡፤ በዚህ አመትም ከ45 በላይ ከተሞችና ወረዳዎችን እንዲያስተባብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቡታጅራ ቅርንጫፍ ወደ ሆሳዕና ሲዛወር የጉራጌ ካድሬዎች የከተማዉን አመራር ከማገዝ ይልቅ አዉቀዉ ተኝተዋል ፡፤ አሁን ደግሞ በክልልና በዞን ደረጃ ያሉ ሴረኛ የጉራጌ አመራሮች ለቀጣዩ ምርጫም በዚህ ቀጠና ላይ ህዝብ የሚፈልጋቸዉን ግለሰቦች ብልጽግናን ወክለዉ እንዳይመጡ በር በመዝጋት በተቃራኒዉ በሌሎቹ የጉራጌ አካባቢዎች ማለትም በእዣ በእነሞርናኤነር ቁ1 በእነሞርና ኤነርቁ2 በእንደጋኝ በጌታ በቸሃ በሙህር አክሊል በፌድራልና በክልል ደረጃ ያሉ ሚኒስቴሮች ሚኒስቴር ዲአታዎች ኮሚሽነሮች የዩንቭርሰቲ ፕሬዝዳንቶችና ዶክተሮች እና ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ለብልጽግና ፓርቲ እጩ አድርገዉ ሲያቀርቡ ለመስቃንና ቡታጅራ ምርጫ ክልል ግን ተመጣጣኝ የሆኑ በትምህርትና በስራ ልምዳቸዉ የተሻሉ ዶክተሮች ታዋቂ ግለሰቦችንና ለቀጠናዉ ሞጋች የሆኑ እጩዎችን ከመያዝ ይልቅ ሴራ የተሞላበት የእጩ አቀራረብ ሁኔታዎች መፈጠሩ ህዝቡ በተለይም ወጣቱ አዉቆ በተደጋጋሚ እጩ ይቀየርልን ብሎ በአግባቡ ጠይቋል:: እነሱ ግን ቅሬታ ያቀረበዉን ወጣቱንና የመንግስት ሰራተኞችን ምንም አታመጡም በማለት የሄዱበት መንገድ ይህን ህዝብ ለተጨማሪ በደልና ኢፍትሃዊነት እንዳዘጋጁት ልንረዳ ይገባል፡፤ በአጠቃላይ እኛ የምንፈልገዉ ሰዉ በብልጽግና ፓርቲ እጩ ሆኖ መቅረብ በጥቂት የጉራጌ ካድሬዎች እጅ ሆኗል:: ስለዚህ ያለን አማራጭ የግል እጩን መርጠን በቀጠናዉ ላይ የተቆለፉ የሴራ ፖለቲካዎችን በማጋለጥ የህዝቡ የፍትህ የእኩልነት እና የልማት የዘመናት ጥያቄዎችን የለዉጡ መሪ ፊት ሳይታፈኑ በቀጥታ እንዲቀርቡ በማድረግ ሰዉ ወለድና መዋቅር ወለድ ጭቆና በከፊልም ቢሆን ለመቀነስና ባለፉት አመታት በፌድራልና ክልል መንግስት ተወካይ በማጣችን ምክንያት የተረሳዉን ማህበረሰብ ተወካይ እንዲኖረዉ እናደርጋለን ማለት ነዉ::

አንዳንዱ ያልገባዉና ለአጭር ግዜ በሚቆየዉ ለመንደር ስልጣኑ ሲል የሴረኞች ተባባሪ ሆኖ ህዝባችንን ፓርቲ ምረጡ ጭምብል ሴራዉን ለማስቀጠል ሲፍጨረጨር ይታያል:: እኛ ግን አንሸወድም ላለፉት 25 አመታት ኢህአዴግ መንግስት እንዲሆን በፓርቲዉን ምረጡ እንጂ የቀረበዉን እጩ አትዩ በሚል ሽፋን የህዝባችን እንደራሴና ተወካይ ሳይሆን ባዶ ወንበር መርጠን ልከናል፡፤ ዘንድሮ ግን ለዘመናት የተጫነብንና ከአቅማችን በታች እንድንለማ ያደረገንን ሰዉ ወለድና መዋቅር ወለድ ጭቆና ለማስወገድ እዉነተኛና ሞጋች ተወካይ ታዬ ተስፋዬን በመምረጥ የዘመናት የልማትና የእኩልነት ጥያቄዎቻችን በሴረኞች ሳይታፈኑ በቀጥታ ለመንግስት እንዲቀርቡ ማድረግ ይኖርብናል በፓርቲ ስም ጠቅልለዉ የሰጡንን ሳይሆን በተግባር ያየነዉና ያወቅነዉ ብሎም እንዲወክለን የመረጥነዉን እጩ በካርዳችን መርጠን ማሳየት ይኖርብናል ::

ዞናዊ ኢፍትሃዊነቶች ምን ይመስላሉ

የፖለቲካ ተሳትፎ ኢፍትሃዊነት

የፖለቲካ ተሳትፎአችን ምን ይመስላል ለሚለዉ ለአብነት ያህል ከምስራቁ አካባቢ ያለዉን እንኳ ብንመለከት ያለፉት ዘመናት የተሰራዉ ግፍ ያሳዝናል ለዚህ ምክንቱ ደግሞ ለሃገር የሚሆኑ ልጆችህ በየመንገዱ እንዲጨነግፉ ስለሚደረግ ነዉ ይኸዉም ላለፉት 30 ዓመታት የዚህ አካባቢ ፖለቲከኞ ከዞንአልፈፈዉሄደዉአያዉቁምላላፉት 30 ዓመታትጉራጌዞን ዉስጥ አመራር ከነበሩት የአካባቢዉ ልጆችለሚስትርነትሚኒስትርዴኤታነትይቅርናየክልልቢሮ ወይ ምክትል ቢሮሃላፊነትስመድረስ ብርቅ ለመሆኑ ማሳያታሪካችንን ዞር ብሎ ማየት ይበቃናል፡፡

ሌላዉ ዞኑ የፖለቲካ አመራር ምደባ በተመለከተ ብቃትና በችሎታ ብቻ ሰዎች ለአመራርነት ማጨት የሚደግፈዉ ነዉ፡፤ ይሁን እንጂ አካባቢዎችን ማመጣጠን ተብሎ በጎሳ/በወረዳ ደረጃ አመራር ለዘመናት ሲመደብ ቆይቷል ይህም አሰራር ቢሆን ከህብረሰተብ ተሳትፎ አንጻር ሚኮነን አይደለም ግን ደግሞ እንደ አሰራር ከተወሰደ ዋና እና ሁለተኛና ጉራጌ አድርጎ ማሰባሰቡ ለምን ያስፈልጋል ለምን የዞኑ አስተዳዳሪ ብቃት ያለዉ ሰዉ ከተገኘ ከመስቃኑም ከሶደዉም ከማረቆዉም ቢሆን ችግር የለዉም የሚል ሀሳብ ከመያዝ ባልተጻፈ ህግ አስተዳዳሪ ከነዚህ መሆን አይችልም ተብሎ 30 አመት አለፈዉ ለምን፡፤

ሌላዉ አሁን ያለዉ የጉራጌ ዞን አጠቃላይ በሹመት ደረጃ ያለ አመራር ፑል 66 ነዉ ለ13 ወረዳዎች በአንድ ወረዳ ከ5-11 አመራር ሲሳተፍ ከምስራቁ አልተደረገመም ለምሳሌ ያህል የመስቃን ወረዳ 2 ሰዉ ብቻ እንዲሳተፍ ተደርጓል፡፡ ይህ አሰራር ምን ያህል የተዛባ እንደሆነና በብልጽግና ሁሉም ማህበረሰብ ተመጣጣኝ ዉክልና ያገኛል ከተባለ 13ቱም መዋቅር በህዝብ ቁጡሩ ልክ ተመጣጥኖ መሳተፍ ይኖርበታል ግን ደግሞ ችግሩን አምኖ ከማስተካከል ይልቅ ዛሬም እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡

የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ኢፍትሃዊነት

በዞናዊ የጋራ ሃብቶች አጠቃቀምና የስራ አድል ፈጠራ ኢፍትሀዊነት ያለበት ነዉ፡፤ለምሳሌ አሁን ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ማዕከል ላይ ብቻ 2536 የዞን የመንግስት ሰራተኞች ይገኛሉ ከዚህ ዉስጥ ከ34 ማይበልጡ ወይም 2 ፕርሰንት ብቻ የምራቁ አካባቢ አካባቢዋ ሰዎች ናቸዉ፡፡ በአንጻሩ ምስራቁ አካባቢ ባሉ ወረዳዎች ከፍተኛ ( በሺዎች የሚቆጠሩ) ተመራቂ ተማሪዎች 2 እና 3 ኣመት ስራ ፈትተዉ ሲቀመጡ ዞን ማዕከል ላይ ግን በርካታ የስራ ማስታወቂያ እየወጣ ቅጥር ይፈጻማል፡፡ ብቻም አይደል ከሴክተር ሴክተር ምቾት ፍለጋ የሚዘዋወር ሰራተኛ ቀላል አይደለም ስለሆነም ቡታጅራ ቡኢ እንሴኖና ቆሼ ተመርቀዉ ስራ አጥተዉ ለተቀመጡ ወጣቶች በልዩ ሁኔታ ስራ ሚያገኙበት ሁኔታ ዞኑ ማመቻቸት አለበት፤ በየአመቱ በዞኑ ምክር ቤት ለዞኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለስራ ማስኬጃ ለደሞዝና ለመሳሰሉት ከሚመደበዉ 300-460 ሚሊየን ብር በጀት ላይ ሁሉም የዞኑ ወጣቶች በመቀጠር ደረጃ የሚገኝ የስራ አድል ፈጠራ ፍትሃዊ ተጠቃሚ መሆን አለባቸዉ ።


እባክዎ ሌሎች እንዲያነቡት የቻሉትን ያህል ሼር ያድርጉ

ቅጽ 2 ይቀጥላል ተከታትለዉ ያንብቡት

የምርጫ ምልክቱእንሰት” ነዉ

እንሰትን ይምረጡ

ታዬ ተስፋዬ ስሜ


54 views0 comments
bottom of page