top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

አዎንታዊ ስነ ልቦና (Positive Psychology)



ህመምን ማከም እንደሚያስፈልገው ሁሉ የአእምሮ ጤናን ማጎልበት፣ የሰዎች ድክመት ላይ ከማተኮር ጥንካሬያቸው ላይ ማተኮር፣ ጥሩ ያልሆኑትን ለማቅናት የሚሞክረውን ያህል ምርጥ የሆኑትን አንዲያድጉ ማገዝ የአዎንታዊ ስነልቦና ትኩረቶች ናቸው፡፡ የሰው ልጆችን ኑሮ በተሟላ እና በተመጣጠነ መልኩ ለመረዳት ይሞክራል፡፡ "ሰዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መፍታት ይችላሉ?" ከሚለው መደበኛው የስነ ልቦና ሀሳብ በተቃራኒው የቆመ አይደለም፡፡ በአንጻሩ የተለመደውን ስነ ልቦና የሚያግዝና አድማሱን የሚያሰፋ ነው፡፡ ሰዎች ከውልደት እስከ ሞት የሚያልፉባቸውን ሂደቶች ያጠናል፡፡ ሰዎች መሆን የሚችሉትን 'ምርጡን እራሳቸውን' እንዲሆኑ እንዲሁም የሚያደርጓቸውን ነገሮች በተሻለ መንገድ ማድረግ እንዲችሉ ያግዛል፡፡

በህይወት ውስጥ ጥሩ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ በዛው ልክ መጥፎ ነገሮችም አሉ፡፡ የአዎንታዊ ስነ ልቦና ዋነኛ እሳቤው 'ጥሩ ህይወት' ውጣ ውረድን ከማለፍና ችግሮችን ከመቋቋም ከፍ ያለ መሆን አለበት የሚል ነው፡፡

ሰዎች በራሳቸው መንገድ ደስተኛ የሚያደርጋቸውንና በህይወታቸው የሚሰማቸውን እርካታ የሚወስኑ ነገሮችን ሲጠየቁ የሚሰጧቸው ምላሾች በሚያስገርም ሁኔታ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ከአሜሪካ ሚሊየነሮች እስከ የህንድ ጎዳና ተዳዳሪዎች የሰጧቸው ምላሾች ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቀጥለው የተዘረዘሩት ዘር ፆታ፣ የትምህርት ደረጃ ሳይለዩ ከደስታና ከአእምሮ ጤንነት ጋር ከፍተኛ ተያያዥነት አላቸው፡፡


** የጓደኞች መኖር

** ትዳር

** ተጫዋች መሆን

** አመስጋኝ መሆን

** ሀይማኖተኛ ሰው መሆን

** መዝናናት

** ስራ( የገቢዉ መጠን የጎላ ልዩነት አያመጣም)

በስራ ቦታ ምርጥ ጓደኛ መኖር( a best friend at work) ሰዎች በጣም ደስተኛ እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ በስራቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ያስችላል፡፡ ለማጠቃለል ደስተኛ በሆኑና በጣም ደስተኛ በሆኑ ሰዎች ያለው አንድ መሰረታዊ ልዩነት በጣም ደስተኛ የሆኑ ሰዎች የልብ ወዳጅና በጣም ጥሩ ማህበራዊ ህይወት አላቸው፡፡ (ከSynopsis of psychiatry, 11th edition የተተረጎመ)

ህይወት ውጣ-ዉረድን ከማለፍና ችግሮችን ከመቋቋም ከፍ ያለ መሆን አለበት!!!


ዶክተር ዮናስ ላቀው

48 views0 comments
bottom of page