top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

እራስን መሆን/ እኔ ማን ነኝ? BY ZELALEM TESFAYE


ዘላለም ተስፋዬ

ኮሌጅ እያለሁ አንዱ ፕሮፌሰር ሁላችንን እንዲህ ሲል ጠየቀ ” ከእናነንተ ውስጥ ቶሎ ወይ በቀላሉ የሚናደድ ማን ነው?” ክፍል ውስጥ ከነበርነው 25 የምንሆን ተማሪዎች ውስጥ ከስምንት እስከ አስር የሚያክሉ ተማሪዎ እጃቸውን አወጡ። ፕሮፌሰሩም መልሶ ጠየቀ ” እስቲ ማን ይነግርኛል ለምን በቀላሉ እንደሚናደድ?” የዛን ጊዜ ተማሪው ሁሉ ጸጥ አለ። ከዛን ፕሮፌሰሩ ያለው አይረሳኝም። “እዚህ ውስጥ እድሜው ከ20 በታች ያለ ተማሪ ያለ አይመስለኝም፥ ታዲያ ቢያንስ ሃያ አመት ያህል ከራሳችሁ ጋር ኖራችሁ ስለራሳችሁ በደነብ እንዴት ነው የማታውቁት? በቀላሉ ስትናደዱ ለምንድን ነው በቀላሉ ምናደደው ብላችሁ እንኳን እንዴት አትጠይቁም” አለ። ይህ ለብዙዋችን እውነት ነው፥ከእራሳችን ጋር ይህን አመት ስንኖር የምናደርገውን ነገር ለምን ብለን አንጠይቅም።ስለ እራሳችን ምን ያህል እናውቃለን? እኛ ስለራሳችን ካላወቅን ሌሎች ስለኛ ሚሉትን ብቻ አሜን ብለን እንቀበላለን።

እራሳችን ማን እንደሆንን ሳናውቅ እንዴት እራሳችንንስ እንሆናለን? እራስን ማወቅ ማለት ምን ማለት ነው? ከልጅነታችን ጀምሮ የተለያዩ ነግሮች ከቤተስብ፥ ከትምህርት ቤት፥ ከጓደኞች እና ባጠቃላይ ከህብረተሰብ ስለራሳችን ስንሰማ ነው ያደግነው። ባካባቢያችን ያሉ ሰዎች በዘራችን፥ በቆዳ ቀለማችን፥ በትምህርትደረጃችን፥ በቤተሰቦቻችን የንብረት መጠን ብቻ በተለያዩ ነግሮች ተነስተው ማንንታችንን ይነግሩናል። እኛም የሰማነውን ተቅብለን ያ ያሉኝ ነኝ ብለን እንኖራልን። በእርግጥ ልጅ እያለን የሚነገረንን ሁሉ ከመቀበል ውጪ ነገሮችን አመዛዝኖ እና አጣርቶ የመቀበሉ ጥበቡ አልነበረንም፥ ነገር ግን ካደግን በኃላ ግን እራሳችንን ማወቅ የሚገባን ከሰው ከሰማነው ብቻ ከሆነ እራሳችንን ሳይሆን ሌላ ሰውን እየኖርን ነው። እኛ ማን እንደሆንን ሳናውቅ ስንቀር ሰው የጠንን ማንነት ተሸክመን እኖራለን። ሴት ስለሆንሽ ይሄን ማድርግ አትቺይም፥ ወይ ወንድ ስለሆንክ ይህን ማድረግ የለብህም፥ የመጀመሪያ ልጅ ስለሆንክ ይህን ወይ ያን ማድረግ አለብህ፥ ዘርህ ይህ ስለሆነ እንዲህ እና ያን ማሰብ አለብህ፥ ብር ስለሌለህ ይህን ወይ ያን አታቅድ አታስብ •••

ሰዎች ማን እንደሆንን ሊነግሩን አይገባም ሲባል ባጠቃላይ የሰውን ምክር ወይም ሰው የተናገረውን አንሰማም ወይም አናደምጥም ማለት አይድለም። ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን በህይወታችን እንዲመሩን፥ መልካሙን መንገድ እንዲያሳዩን፥ ከእነርሱ ህይወት እንድንማር ስላስቀመጣቸው ሰዎች በርካታዎች ናቸው። ” ሞኝ ከራሱ ውድቀት ጠቢብ ግን ከሌላው ይማራል” ምክርን እና የህይወት ምሳሌን እየተማርን ህይወታችንን ማሻሻል ይኖርብናል። ነገር ግን የሰው ሃሳብ እና ቃል የኛን ማንነት መወስን የለበትም። ማን ነኝ ወይ ምን ማድረግ እፍልጋልሁ ብለን ስንጠይቅ የምናስበው ስዎች ምን እንዳሉን ወይም ከኛ ምን እንደሚጠብቁ ከሆነ ያኔ ስተናል።

ታዲያ እራስን ማወቅ እንዴት ይቻላል?

እራስን ማግኘት ወይ እራስን ማወቅ ማለት ከምንሰማው፥ ከምናየው እና ከምናነበው እንዴት ሊያልፍ ይችላል። እነዚህ ነጥቦች እራሳችንን እንድናውቅ ይረዱናል።


1. ውስጣችንን መስማት

ፈጣሪያችን ሲፈጥረን ህሊናችን ከሱ ሃሳብ ጋር እንዲስማማ አድርጎ ነው። የተሳሳተ ነገር ስናደርግ ብዙ ጊዜ ህሊናችን ይወቅስናል፥ ውስጣችን ደስ አይለውም። አንድ ነገር ስናደርግ ውስጣችንን መጠየቅ ፥ ውስጤ ምንድን ነው ሚስማኝ? ምንድን ነው ፈጣሪ ለውስጤ የሚናገረው ብለን መጠየቅ እናም ከዛ ከሚሰማን ነገር ወይ የውስጥ ድምጽ ጋር መስማማት። ያልሆነውን ስናስመስል ውስጣችን ምቾት አይሰማውም፥ ምክንያቱም ውስጣችን ያለው ድምፅ ፋጣሪ የእርሱን ባህሪ እንድንወርስ ከማንነታችን ጋር ያያዘው ስለሆነ ነው። ስለዚህ ለራስ ታማኝ መሆን፥ አባቴ ወይ ጎረቤቴ ምን ያላል ወይ ከኔ ይጠብቃል ከማለታችን ይልቅ ፈጣሪ የሰጠኝ ህሊናዬ የውስጥ ድምጼ ምን ይላል ብለን መጠየቅ። አንድ አንዴ ውስጣችን የሚለንን ስምቶ ለዛ መታዘዝ ይከብደናል ምክንያቱም እድሜ ልካችንን የኖርነው የውጭ ድምጽ በመስማት ስለነበር። ከራሳችን ጋር እንስማማ።


2. የራስን ዋጋ ማወቅ

ስንፈጠር እኛን የመስለ ሌላ አልተፈጠረም። ፈጣሪ እያንዳንዳችን ልዩ ሆነን ነው የፈጠረን። የአንድ ስው ዋጋ በምንም በማንም አይለካም። የኛ ዋጋ የፈለግነው ነገር ሲሳካ አይጨምርም ወይ ስንደክም ወይ ስንወድቅ አይቀንስም። ሃብት፥ ውበት፥ ትምህርት ደረጃ፥ የትውልድ ስፍራ እና የዘር ሃረጋችን ዋጋችንን አይጨምረውም። ወይም አይቅንሰውም። የሰው ሁሉ ዋጋ እኩል ነው ግን አንድዩ ሌላውን በፍጹም አይተካውም። ስለዚህ እኔ ይሄ ስለሌለኝ ወይ ስላለኝ መደሰት፥ መከበር ወይ በሰላም መኖር አይገባኝም አንበል። ሰው ለኛ የሚሰጠን ዋጋ ሳይሆን እኛ ለራሳችን የምንሰጠው ዋጋ ነው ወሳኝ ነገር። አብዛኛው ጊዜ ሌላው ሰው የሚሰጠን ዋጋ እኛ ለራሳችን ከሰጠነው ዋጋ ጋር አንድ ነው። በፈጣሪ ፊት የፕሬዝዳንት ኦባማ ዋጋ እና መንገድ ላይ የሚተኛው ወንድማችን ዋጋ እኩልና አንድ ነው። ነገር ግን በሰሩት መልካም ስራ መጠን ከፍርዱ በዃላ ደረጃቸውና ቦታቸው ሊለያይ ይችላል።


3. አዕምሮን ማደስ

ከልጅነታችን ጀምሮ ስለኛ ብዙ ተነግሮናል። ያንን እንደ እውነታ ወስደን ሳናስብው ማንንታችን እድርገናቸዋል። አሁን ግን ቆም ብለን ስለኛ የምናስባችው ነገሮች ከየት እንደመጡ እንመርምር እና ለኛ የማይጥቅሙን ነግሮች ሁሉ እናስወግድ። አንተ እኮ ፈሪ ነህ፥ ትምህርት አይገባህም፥ ጸባይህ ለሰው አይገባም፥ አትረባም፥ መልክህ አያምርም፥ መናገር አትችልም ዝም በል፥ ካንተ ያ… ወይ ይኸኛው ይሻላል፥ አይሳካላልህም፥ የተለያዩ መጥፎ እና ማንነታችንን በመጥፎ ሊቅይሩ የመጡ ንግግሮችን ሁሉ ከአይምሮአችን አጥቦ ማውጣት ያስፈልጋል። ትዝ ይለኛል የተውስኑ ልጆች ጋር ቁጭ ብለን ስናወራ ስለራሳችሁ መጥፎ የምታስቡት ነገር ከየት እንደመጣ አስቡ እስቲ ስላችው ሁሉም ልጅ እያሉ አንድ ሰው የተናገራቸው ነገሮች ነበሩ። እኛ ግን ሳናስተውል እራሳችንን በእነርሱ ቃሎች ወስነነዋል። ወይም ሰዎች ባይሉን ደግሞ አንድ አንዴ እኛ እራሳችን ካለፍንባቸው የድሮ ድካሞች ዛሬያችንን ወስነነዋል። ስለዚህ ቆም ብለን እንዚህን ሃሳቦች በመልካም ሃሳቦች ልንተካቸው ይገባል።


4. ነገሮችን እና እራስን መለየት

በአካባቢያችን የሚሆኑ ነግሮች የራሳቸው ማንነት አላቸው የነሱን ማንነት ከእኛ ጋር ማያያዝ አያሻም። ለምሳሌ ትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት ሳናመጣ ስንቀር ያንን ወስደን እኔ ማለት ሰነፍ ነኝ ወይ እንዲህ… ነኝ ከማለት በፊት ትምህርቱን ጥሩ ውጤት ላመጣ የሔድኩበት መንገድ ጥሩ አልነበርም ስለዚህ በሚቅጥለው በየትኛው መንገድ ልሂድ ብሎ ማሰቡ የግድ ይላል። ባጠቃላይ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ ከመደምደም በፊት እንዴት ያንን ነገር ልስራው ወይ ላሻሽለው ብሎ ማሰብ ይገባል። በተጨማሪም ከሰው ጋር ያለን ግንኙነት ምክንያታዊና ምክናታዊ ባልሆኑ ጉዳዮችና ክስተቶች መልካም ካልሆነ እኔ ጥሩ ጓደኛ አልሆንም ወይም ጓደና አይወጣልኝም ከማለት በፊት ነገሩን ከራስ ማንነት ወጣ አድርጎ በምን መንገድ መግባባት እንችላለን፥ ምን ብናደርግ ይሄ ይስትካከላል ማለት አለብን።


5.እራስን ከሌላው ጋር አለማወዳደር

እላይ ነጥቦች ውስጥ እንደተጠቀሰው ሁላችን ስንፈጠር ልዩ እና በጣም ልዩ ሆነን ነው። የሌላው ህይወት ለመማሪያ ምሳሌ ሊሆነን ይገባል እንጂ ማወዳደሪያ መስፈርት መሆን የለብትም። ሰው ሁሉ በየራሱ የሚሄድበት መንገድ አለው ፥ ያንተ መንገድ ከሌላው ይለያል፥ የሰው መንገድ ላይ መግባት አንተ መድረስ የሚገባህ ቦታ አያደርስህም። አንተ ማድርግ በምትችለው እና ፈጣሪ በሰጠህ ነገር መዝነው ። በተቀደሱት መጽሃፎች ውስት እንደተጠቀሰው ፈጣሪአችን ለሰው ልጅ በሙሉ የተለያየ ችሎታ ወይም ተሰጥኦ እንደሰጠ ግን እያንዳንዱ የሚጠየቀው በተሰጠው ልክ ምን ተግባራትን እንደፈጠመ ነው። የሌላውን ሰው ስጦታ ትተን ለእኛ የተሰጠን ላይ ማተኮሩ የተሻለ ነው።

6. መልካምን ማሰብ

ጥሩ ጥሩ ንገሮችን ማሰብን አይምሮአችንን ማስለመዱ መልካም ነው። ብዙ ጊዜ ለሰው የምንለውን እንጠነቀቃለን በቃላችን እንዳንጎዳቸው ቃላት እንመርጣለን ስለራሳችን ግን ያን ያህል አንጠነቀቅም። ስለ ራሳችን የምናስበው እና ምንናገረው ነገር መልካም ንገር እንዲሆን መጠንቀቅ አለብን። የተቀደሱት መጽሃፎቹ “በምላስ ላይ ሞት እና ህይወት አለ” ይላሉ። ለምን? ምክንያቱም በምንናገርው የሰውን መንፈስ ልንገድል ወይ ልናቀና ስለምንችል ነው። ስለራሳችን እንዲሁ በውስጣችን እንናገራለን እናስባለን ያ ሃሳብ መልካም መሆን አለበት። እራሳችንን መሆን ይከብደናል ስለራሳችን ያለን ሃሳብ መጥፎ ከሆነ። እራሳችንን ማበረታታት፥ መልካም ይሆንልሃል ፥ በፈጣሪ የተወደድክ ነህ እያልን ብዙ ብዙ መልካም ነገሮችን መናገር መተግበር አለብን።


7. እራሳችንን በስዎች አይምሮ ውስጥ አለማየት ብዙ ጊዜ እራሳችንን እንዳንሆን የሚያረገን እራሳችንን በሰው ውስጥ ሆነን ማየቱ። ማለትም ስናወራ ያ የሚስማን ሰው ስለኛ ምን እንደሚያስብ በሱ ውስጥ ሆነን እራሳችንን ማየት እንጀምራልን። ከዛን መናገር የምንፈልገውን ሳይሆን መስማት የሚፍልገውን ማውራት እንጀምራለን። ይህ በአነጋገራችን ብቻ ሳይሆን፥ ባለባበሳችን፥ ባረማመዳችን፥ በሁሉ ነገራችን በሌላ ሰው ውስጥ ያለው እይታ እንዲስተካከል እያልን እራሳችንን እንቀያይራለን። ይህ እንዳይሆን ስናወራ ወይ ስንኖር ውስጣችን እንደሚለው መሆን አልበት። ብዙ ጊዜ ውስጣችን የሚለውን መስማት ሲባል በመጀመሪያ ውስጣችን ከፈጣሪ ትዕዛዛት ጋር መስማማቱን ማረጋገጥ አለብን።

309 views0 comments
bottom of page