top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

"ከነኛ ሴረኞች ይልቅ የኛዎቹ ተባባሪ የታሪክ አተላዎች ያሳፍሩኛል" (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)


"ከነኛ ሴረኞች ይልቅ የኛዎቹ ተባባሪ የታሪክ አተላዎች ያሳፍሩኛል" (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)

ዛሬም ትችቴ ስለ ጉራጌ ህዝብ ሳይሆን ስለጉራጌ ፖለቲከኞች ሴራ እንደሆነ ታሳቢ ተደርጎ ይነበበ!


ላላፉት 30ዓመታት በዚህ ቀጠና ላይ ፖለቲከኛ ተከራካሪ አለመኖሩ ከዛ ይልቅ የግፍ ተባባሪ በየግዜዉ መፈጠሩ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም እንደተባለዉ ወይ እርግማን አለ ወይ እርግማኑን የሚሰብር ጀግና የለም ላላፉት 30ዓመታት የቡታጅራ ልጆች ፖለቲካ አያዉቁም። ወይም ደግሞ ፖለቲካን ሳይማሩ ቀርተው ይሁን? በምን ምክንያት እንደሆነ ባይገባኝም ከነበርንበት ዘቅጠን ዛሬም በሌሎች የምንጎተት በሌሎች የምንወከል እራሳችንን የማንመራ አጃቢና ንጉሱን ጠባቂ ጃንደረባ ብቻ ሆነን ቀርቸናል። ለዛም ነው ባለቤት አልባ ማህበረሰቦች በመሆናችን በህዝባችን ላይ የሚደርሰዉን ግድያ እስር መፈናቀል ቃጠሎና ዉድመትን የሚፈታና ህዝቡን አንድ አድርጎ የሚመክር የኛ ሰዉ ያልተፈጠረዉ። ለዚህ... ደግሞ ዋንኛዉ ምክንያት የራሳችን ልጆችን ድመት ሆነን እየበላን የሌሎቹን የምናሳድግ ጥቂት ሾተላዮች በየግዜዉ እየፈጠርን የምንሄድበት ነገር መቆሚያ ሊበጅለት ይገባል። ዛሬም እንደ ጥንቱ እራሳችን በየሰፈሩ ተጎልተን ቀስታችንንና ጦራችንን ስለን ጨቋኞቻችንና እና በዳዮቻንንን ከመዉጋት ይልቅ እነሱኑ ለመጠበቅ የራሳችንን ልጆች ለመዉጋት ከፊት እንሰለፋለን። ለዛም ነዉ ዛሬም እከሌ የሚባል ያንተ ፖለቲከኛ ተሟጋች እና ታጋይ ወይም በተቃዋሚ ወገን ወይ በመንግስት ወገን የሌለህ መቼም ትምህርት ቤትና የተማሩ ሰዎች ጠፍተዉ አይመስለኝ። ፖለቲካን የጀመሩና ለሃገር የሚሆኑ ልጆችህ በየመንገዱ እንዲጨነግፉ ሲደረግ ለምን ከማለት ይልቅ ለ1 አመት ወይም 6 ወር ስልጣንህ ጨቋኞችን በማገዝ የታሪክ አተላ ትሆናለህ። ነፍሳቸዉን ይማረዉና አምባሳደር ድንበሩ አለሙ በ1992 በያኔዎቹ ሰባሪዎች ሰለባ ሆነዉ ሲገፉ እና ለፓርላማ እንዳይወከሉ ሲደረግ በግል ትግላቸዉ በሳምንት ዉስጥ 10ሺ ፊርማ በማሰባሰብ በግል ለመወዳደር ሲመጡ ተለምነዉ ወደ ድርጅቱን ወክለው ለፓርላማ የገቡት እና በታሪክም ቢሆን የሚጠቀሱ የአካባቢዉ ሰዉና አምባሳድር የሆኑት። ከዛ በተረፈ የኛ ፖለቲከኞ ከዞን አልፈፈዉ ሄደዉ አያዉቁም። ታዲያ... ለሃገር እና ለአካቢዉ መከታ አይሁኑ እንጂ ለራሳቸዉ ኑሮ አንሰዉም አያዉቁም። እኔም አንተ ከምታስበዉ በላይ መኖር የምችል ፕሮፋል አለኝ ለኔ በምርጫ ከመወዳደርና 5 አመት ስራ ፈት ከመሆን ይልቅ ትንሽዬ የመንደር NGO ዉስጥ ብገባ ለራሴና ለቤተሰቤ የተሻለ ገቢን አገኛለሁ። አረ እንደዉ የሰፈር ደላላ ብሆን እንኳ ከተወካዮች ምክር ቤት የተሻለ ገቢ ማግኘት እችላለሁ። ለራሱ አስቦ ነዉ ብለህ አትጨነቅ::

ላላፉት 30 ዓመታት ጉራጌ ዞን ዉስጥ አመራር ከነበሩት ዉስጥ የአካባቢዉ ልጆች ለሚስትርነት ወይም ሚኒስትር ዴኤታነት ይቅርና የክልል ቢሮ ወይ ምክትል ቢሮ ሃላፊነትስ የደረሱ አሉ እንዴ? የት ናቸዉ? እነ በድሩ ደድገባ፣ ትንታጉና የፖለቲካ አዋቂዉ በድሩ ሃሰን፣ ሁሴን ዳሪ፣ ሁሴን ቡክሎ፣ መሃመድኑር ሳሊ፣ ረዉዳ ጀማል፣ ጀሚል አህመድ፣ ሲቲ አህመድ፣ ሟቹ ይላሉ ጀማል እና ዶ/ር ሽመልስ ኬራላ 2000 ዓ/ም ላይ በስያሜ ሰበብ የጠፉትን ብርቅዬ የአካባቢዉ ልጆች ጠቅሴ አልጨርሰዉም። ዛሬ በሰፈር ስልጣን ተታለህ ከተማ አስተዳድር ቁጭ ብለህ ለጨቋኞች ድጋፍ ምትጽፈዉ ሰዉዬ እራስህ እኮ በትግልህ ዋጋ የከፈልክ የወቅቱ ጀግና ነበርክ ሌላኛዉ ደግሞ ቤተሰቦቹን ሰብስቦ በፊክ አካዉንት ሰዎችን በማጠልሸት ተራ ስልጣን ሚፈልገዉ ሰዉዬም አትጨነቅ እኔ ስልጣን ሳገኝ ላንተና ለቤተሰቦችህ የሚሆን እሰጥሃለዉ በልሉኝ::

ለመረጃ ያህል የሩቁን ልተዉና እኔ ማዉቀዉን በቅርብ ዞን በነበሩት አቶ ጌቱ አርጋዉ ለክልል ገቢዎች ባለስልጣን ታጭቶ ከዞን እንዲልኩት ሲጠየቅ አይቻልም ብሎ በቅጣት ድሬደዋ እንዴት እንደተላከና ቅጣቱ ሽልማት ሆኖለት ፈንቅሎ በመዉጣቱ ነዉ ዛሬ ትንሽም ቢሆን እከሌ አለ ልትል ያስቻለህ። ካዛ በተረፈ ሰብስቤ ተካ ምን ስለፈጠረ ነዉ አዋርደዉ አቃጥለዉ ንብረቱን በየመንገዱ በትነዉ ከግድያ እራሱን አድኖ ወደ ቻይና ለትምህርት ሄዶ ሲመለስ ከሱ ጋር የነበሩት የተሻለ ቦታ ሲመደቡ እርሱ ዛሬም ሃዋሳ ላይ ይባክናል። እኔን ያለፍላጎቴ ወደ ዞን አልመጣም አስከፋችኋለዉ እያልኩ ነዉ ለምነዉ ወስደዉ ሃቅ ሃቋን ስዘረግፍ ለማስወጠት የሞከሩት። ታጁ ነስሩን ማነዉ ሰው በተሰበሰበበት አዳራሽ በሽጉጥ ግንባርህን ነዉ ምለው ብሎ አስፈራርቶ በንዴት ትምህርት እንዲገባ ያደረገው አሁን የተቀመጡ ለነሱ ሚመቻቸዉን ባንዳና ሙቅ አፍ ሰብስበዉ ያስቀመጡት ያንተ ልጆች ጎሰኛ የህዝብ ድጋፍ የሌላቸዉ ተደርገዉ በየመንገዱ ሲጣሉ የነሱን ሰንሰልና ብሳና ዥማር ነዉ ለሚኒስትር የሚበቃ ባለምጡቅ አዕምሮ ይላሉ። ዶክተር ካሱ ኢላላን የሃገር ገዳይ አርገዉ መኩሪያ ሃይሌን የጉራጌ አድባር አድርገዉ ከሚስሉ ሰዎች ጋር ተማምነህ መኖር የሚቻለዉ በይቅርታና በመደመር ካልሆነ በስተቀር ግፉን ረስተህ ከሄድክ ግን ግፉ እራሱ ዋጋህን ይሰጥሃል። እናም ሳጠቃልለዉ ከጨቋኞች ጋር በመሰለፍ የታሪክ አተላ ከመሆን ተቆጠብ ማህበረሰቡም እንዲህ አይነቶቹን ተልካሾች ቢያስተምራቸዉ መልካም ነዉ እላለሁ። ትንሽ ጹሁፌ ስሜታዊነት ስለተላበሰ ቅርታ እጠይቃለሁኝ እኔ ግን ግፍን ደግፎ ማንም ቢከፋ ትግሌን ከማድረግ አልቆጠብም::

ቆይቼ ከጉራጌ በአዲስ አበባና እና በዞኑ ላይ ብልጽግና ላይ የተወከሉ ሰዎች ተመጣጣኝነት ላይ ሃሳብ አሰጣለሁኝ!

ለአሁኑ አበቃሁ አመሰግናለሁኝ::


ታዬ ተስፋዬ ስሜ

54 views0 comments
bottom of page