top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ግጥሞች (ክፍል - 20)


181. አረብ አገራችን ሳይለምድም አይቀር

ወልደው ይከብዳሉ ያደርጋሉ አገር

ግን ልጁ ሸይጣን ነው አንድ የለውም ኸይር

ሶላትም አይሰግድ እንደ ዱር ሲቀር

መልከ ቆንጆ አይመርጡም ብትሆን ባሪያ ኩፍር::

181. ሀብታም ወራሽ መንግሥት ተሹሞ ሲመጣ

ሙክት የዚያን ጊዜ ይሆናሉ ቋንጣ

ሁሉም ይጎዳዋል ፀሐይ እስኪወጣ

ታስሮ ከመገደል ምናልባት ቢወጣ

የአላህ በል የዚያን ቀን እንዲህ ያል ሲመጣ::

182. ዘመን ተለውጦ ጥቅምት ሲደርስ

በአሥመራ ከተማ ይነፍሳል ነፋስ

የዚያን ቀን ሐበሻ ይላል ፈረስረስ

ሃምሳ ቀን ይቆያል ሴት ወንዱ ሲያለቅስ

ወንፊት ጉድ እስኪወልድ እስኪሆን አራስ::

183. መንግሥታቶች አሥራ አምስት ሲቀሩ

ከድንጋጤ በቀር ይርቃል ኸይሩ

በረካም አይገኝ እስኪ ቁርዓን ቅሩ

መድፈርም አይበቃ ደብዳቤ መቅበሩ

ለሰው ግን ጥሩ ነው በአማን ማደሩ::

184. በመካ አንድ ንጉሥ በገርብ ሦስት ሲቀር

ድርቡሽ የዚያን ጊዜ ያስባሉ ሸር

የዚያን ቀን ያየ ሰው ሲጫጫር

በሰበቡ አሥመራ ትሆናለች አር::

185. እኛ አፈር በገባን በስድሳ አምስት

ንጉሥ የተባለ የለውም ሐያት

እጁ እየተያዘ ይገባል እሳት

ዘሩ እየታደነ እንደ አውሬ እንደ እሳት

ከእኛም ሳይመጣ አይቀር ኋላ ወደፊት::

186. አጼ ኢያሱ ነግሦ በሸዋ መሬት

ጥቅልል አርጎ ይዞ የአያቱን ግዛት

በኋላ እንደገና አላህ ሽቶበት

ዘኒ ሆነ ብለው በቀን በሌሊት

አይቶ እማይለቅ ሆኖ የምታምር ሴት

እንኳን ሌላይቱን እህቱን ጣላት

በሏ በሌለበት እሱ አስረገዛት

ከአልጋው ያወርዱታል በሥራው ክፋት::

187. ለጥቃ ተሾመች ዘውዲቱ የሚሏት

ሦስት ዓመት ገዛች ይች ቆንጆ ሴት

የራስ መኮንን ልጅ ተፈሪ የሚሉት

መቃ ሠራ በሷ ገድሎ ቀበራት

እቤት ውስጥ ቀብሮ መደብ ሠራባት

በመቃ ይሎታል መች ሲቀርለት::

188. ታ(ተ)ጥቆ ተሾመ ተፈሪ አባ መላ

ሃምሳ ዓመት ይገዛል ሐበሻን በሞላ

የሚገዛበት ነው በብልሃት በመላ

ባይሆን ቀኑ ሲደርስ ሃምሳ ዓመት ሲሞላ

የገዛ አሽከሮቹ ያዝ አርገው በመላ

ከአልጋው ያወርዱታል በችግር ሊቆላ፣

ከዚያ ያበሉታል ቸኮሌ ባቄላ

ችግረን ቅመሰው ጮማህን ሳትበላ::

189. ሕዝብን ስትቀጠቅጥ ለድሃ አታዝን

ክብር ስታሳዳግ አርገርህ የልቡን

በመሥሪያ ቤቱ ዘመዶችህን

እስኪ ይድረሱልህ እንዲህ ስትሆን::

190. ከአልጋው አምዘግዝገው ምድር ይጥሉታል

ወዲያው የፊጥኝ እጆቹን ያስሩታል

በፊት መቃ መሥራት እንዲህ ያንገላታል

ከሞላው አሟሟት በእሱ ይበረታል

ሳያስበው ድንገት ከአልጋው ያወርዱታል::

34 views0 comments
bottom of page