top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ግጥሞች (ክፍል - 21)


የሼህ ሁሴን ጅብሪል ግጥሞች (ክፍል - 21)
የሼህ ሁሴን ጅብሪል ግጥሞች (ክፍል - 21)

190. ቸኮሌ እያበሉ እልፍኙ ያስሩታል

ሕዝቡን እንደቀጣ ችግር ያበሉታል

መስከረም አንድ ቀን ደንገት ይይዙታል

አሥራ አምስት ቀን ለዓመት ሲቀረው ይሞታል::

192. አንተ በእልፍኝህ ውስጥ በልተህ ጮማህን

ድሃው ቶሙን ውሎ ቀምሶ ጥሬውን

ትንሽ እዝነት የለህ ቅመሳት አሁን::

193. የገዛ አሽከሮቹ ያሳደጋቸው

በዙፋን ባልጋው ላይ ያሞናደላቸው

ከአልጋው ያወርዱታል አላህ ሠልጧቸው

እሑድ ቀን ሰንበቱ እንሂድ ብለው

ዘውዱን ከራሱ ላይ ሉሉን ቀምተው

አመድ ያቅሙታል ትዝ ሳይለው::

194. የዳግሚያ መኮንን የአልጋ ወራሽ አባት

የመነን አስፋው ባል፣ አጼ ኃይለ ሥላሴ ባለ ብዙ ብልሃት

ደርጎች ያወርዱታል ከእልፍኝ ከኩራት

በዘውዲቱ ጡር ውሎ መቃ በሠራበት

ጥቃቱን ይቀምሳል ኩስ እሬት ያለበት

በእሱ ጊዜ ያሉት ሹሞችም ባላባት፣

ከእዛ ያድኑታል ሁሉም በያሉበት

ዱአ አድራጊ ድሁ መቼም ምን የለበት፣

አደብ ካጣች በቀር ጌታችን ሽቶበት::

195. አጼ መባል ቀርቶ አሮጌው ይሉታል

እሬት ኮሶ ቀምሶ አመድ ያለብሱታል

ከአልጋው አውርደውት አልቅሶ ይሞታል

እራሱ ጡር ውሎ መቃ ፊቱ ታለ::

196. አንድ ሺህ ሦስት መቶ ዘጠና ዓመት

አራት መቶ ሳይሆን እዚህ መሃል ናት

ተፈሪ አባል መላ የሚወድምበት::

197. ኃይሌ መቃ ሠርቶ በዘውዲቱ ሬሳ

በሺች መደቡ ላይ ቢሞትባት እሳ

ጌታችን መቼ ነው ጀዛን የሚረሳ?

198. ከአዳም አንስቶ እነቢ ድረስ

ስድስት ሺህ ዓመት ስንት መቶ ምጉሥ

ከነቢ አንስቶ ቂያማ ድረስ

ሁለት ሺህ ዓመት ጌታ ቢለግስ::

199. አንድ ሺህ ሦስት መቶ ዘጠና ዓመት

ሒጅራው ሲሆነው ኸይረል በርየት

አለች ብርቱ ቀን አለች አቀበት::

200. እዝናት የሚጠፋባት ከወንድም ከሴት

ወዳጅም ዘመድም አባትም እናት፣

የወለዱትም ልጅ ውንድምም አኅት፣

እየጠና መሄድ ከአንዱ ዓመት አንዱ ዓመት

እስክትሾልክ ድረስ እርብ የሚሏት

እንዴት ያለች የመን እንዴት ያለች ወቅት?

የጠናች ወራት እህል በቆርቆሮ የመቀናበት

ቡና በችርቸራ የሚሆንበት

በሬ መቶ ሃያ የሚያወጣበት

በሬ አንደ ማሽላ የሚፈጅበት

ጭቃና ምስለኔ የሚሻርበት

ገበያ በሙሉ የሚጠፋበት::

201. እንኳን ሌላው ነገር ወስው ሐታ አድሩስ

ይጠፋል አወል ቡን ሲቀዳ እሚጤስ::

53 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page