top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

የትግል ሃሳቤ ምክንያቶች (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)

በበርካታ ምክንቶች በተለይም በዞናችን በምስራቁ ቀጠና ባለፉት 3 አመታት በተፈጠሩት ሁኔታዎች እጅጉን በማዘኔና በትንሽ እዉቀቴ ለማህበረሰቡ ከማስበዉና ከምመኝለት በተቃራኒ መንገድ በክልሉ ጥቂት ከፍተኛ አመራሮች የተመራና ያልተፈለጉ ሁኔታዎች በመፈጠራቸዉ በተወሰነ መልኩ ስሜታዊ ሆኜ ከፖለቲካም ይሁን ሌሎች ማህበራዊ ሁኔታዎች ጉዳዩ እስኪገባኝ እራሴን ለማራቅ ወስኜ ነበር ። ለዚህም ምክንያቱ ጥቂት በዞን እና በክልል ደረጃ ያሉ በአለቃና ምንዝር እሳቤ ደረጃ ያሉ ግለሰቦች የብልጽግና ካባ በመልበስ የቀደመዉን የደህዴን የበሰበሰ አሰራር የሚተገብሩ የህዝቡን ዘላቂ ችግር መፍቻ የሆነዉን እዉነታን በማዳፈን እራሳቸዉንና ህዝብን እየዋሹ አስከዛሬ ድረስ ቀጥለዋል። እኔ ደግሞ እንኳን ለዉጥ መጥቶ በዛ ከባድ ጊዜያትም አልፈራሁምና ባለፉት 2 አመታት በግልጽ በወሳኝ መድረክ ለአመንኩበትና የህዝቡን ችግር ይፈታል ብዬ አቋም በያዝኩባቸዉ አጀንዳዎች ላይ እንደ አብዛህኛዉ ባለስልጣን ይሄ ትግል ስራዬን/ስልጣኔን/ ያሳጣኛል ብዬ ቅንጣትም ሳልጨነቅ በአሉባልታና በወሬ ሳይሆን በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ ላይ ተመስርቼ ሞግቻለሁ። ነገር ግን አመራር በነበርኩባቸዉ ጥቂት ጊዜያት ለማነሳቸዉ ሃሳቦችና ለማቀርባቸዉ ሂሶች ተገቢዉን መልስና መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ እኔን ከድርጅት አሰራር ዉጪ ያለግምገማ ከትግል መድረክ ማራቅ ለጊዜዉም ቢሆን እራሳቸዉን እንደ ጀግና በመቁጠር መድረክ ላይ እፎይታን አግኝተዋል። እኔም በትግሌ ምክንያት የደረሰብኝ ጥቃት ረስቼ ብተወዉም እነሱ ግን ለነበረኝ የረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚመጥን ቦታዎች ላይ ምደባ እዳላገኝ ከማድረግ ጀምሮ በየትኛዉም መንገድ እንዳልከሰት እየተከታተሉ መንገዴን ለመዝጋት ተረባርበዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ችላ ብዬ በራሴ መንገድ ብጓዝም በአካባቢዉ ባሉ ጥቂት ተላላኪ አመራሮች ህዝቡን የማይመጥኑ ክብረነክ የሆኑ ሁኔታዎች በመፈጠሩ ከነሱ ተጽዕኖ ነጻ በሆነዉ ምርጫ ተሳትፌ በዉስጤ የያዝኳቸዉን በቀጠናዉ ላይ የተቆለፉ የሴራ ፖለቲካዎችን በማጋለጥ በማስታወሻዬ የመዘገብኳቸዉን የህዝቡ የፍትህና የእኩልነት እና የልማት የዘመናት ጥያቄዎችን የለዉጡ መሪና እንደራሴዎች ፊት ሳይታፈኑ ቀጥታ ባቀርብ በሚል ካልሆነ ምንም ሌላ እሳቤ የለኝም፡፡

ባለፋትጊዜያትም አብዛኛዉ ሰዉ በተለይም የገጠሩ ህዝብ አጠገቡ ሆኜ ከድህነት ለመዉጣት የሚያደርገዉ ትግል በነበረኝ እዉቀትና በቻልኩት አቅም ለመርዳት ሞክሬያለሁኝ ከዛ በተረፈ በአካል ሳታዉቁኝ በአቋሜ የምትደግፍኝ እንዲሁም የምትቃወሙ ትኖራላቹና እና በሃሳብ ትግል አምናለሁና እንተጋገዝ።

አስኪባለፋት ሁለት አመታት ያሳለፍኩበትን ሁኔታ ላስረዳ የክልል አመራር ተችተሃል አስጨንቀሃል ከሰሃል ወይም አጋልጠሃል ተብለዉ የተፈረጁ ጉዳዮችን በአጭሩ ልግለጸቸዉ ...

ይቀጥላል

የትግል ሃሳቤ ምክንያቶች (ታዬ ተስፋዬ ስሜ)

72 views0 comments
bottom of page