top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ያለምክንያት ከሄድክ በምክንያት አትምጣ! – መሐመድ ሲራጅ

መሐመድ ሲራጅ

የኔ ምርጥ ምክሮች

በህይወት ሰልፍ ውስጥ ሳለህ ልብ ልትላቸው የሚገቡ

እነኚህን 10 ነጥቦች በአጽንኦት አንብባቸው

➊. ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፤ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፤ማማረር ነገህን በጎአያደርገውም።

➋.የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም! ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፤ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል፤ ለሁሉምጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና።

➌.መኪና ገዛ ብለህ እኔስ አትበል! ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ?እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው።

➍.ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን

►በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ!

►ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣

►በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣

►ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣

►ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣ ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም።

ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል።

➎.በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!

ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም። አንተንም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፤ በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን።

➏.መክሊትህን ፈልግ!

ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና።

አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው። በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት።

አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ ፈልገውና አውጣው። ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ነው? ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው?

ድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን) እየሰሩ መኖር ነው? ምንድነው?

እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው፣ ምን ይሻለኛል? እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ። በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።

➐.መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ

ከሰይጣን እንዳልሆነ አስተውል! ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀየር ብቃት አለው። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል።

መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው፤መጥፎነት ከአንተ ይራቅ፤ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም።

➑.ሰው የዘራውን ያጭዳል የሚለውን አባባል አስታውስ፤የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፤መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፤ መልካም ከሰራህምእንደዚያውይገጥምሃል።

ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ፤ራስህን አትሸውድ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ፤ ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ አንተም የዘራኸውን በእጥፍታጭዳለህ።

➒. ለራስህ ስትል መልካም ሁን፣ በጎውንም አስብ!ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም።

➓ በማንም ላይ አትፍረድ!

ፍርድ የፈጣሪ ነው። ፍጥረት ሁሉ እንከን አለበት። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል።

*ለውጥ ከራስ ይጀመራል! እናም አሁኑኑ መለወጥ ጀምር።

115 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page