top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ዲፕረሽን ወንዶች ላይ : DEPRESSION IN MEN – ዶ/ር ዮናስ ላቀው


ዲፕረሽን ወንዶች ላይ : DEPRESSION IN MEN – ዶ/ር ዮናስ ላቀው

የዲፕረሽን ምልክቶች በሴቶችም በወንዶችም ላይ ተመሳሳይ ይሁኑ እንጂ መገለጫዎቹ ይለያያሉ፡፡

የልዩነቱ መንስኤ አስዳደግ ላይ “ወንድ አይደለህ ቆፍጠን በል!” የመሳሰሉት አባባሎች ስነ ልቦና ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ ወይም ተፈጥሯዊ ልዩነት ሊሆን ይችላል፡፡

በዚህ ምክኒያት ዲፕረሽን ወንዶች ላይ ሲከሰት በቀላሉ ለመለየት ከማስቸገሩም በላይ የሀፍረት ስሜት ተከትሎት ከመጣ ጥሩ ያልሆኑ ውጤቶች ያስከትላል፡፡

በዲፕረሽን ላይ ሀፍረት ተጨምሮ ሲመጣ ከሰዎች መገለል፣ ስሜትን አውጥቶ ለመናገር አለመቻል (ለቅርብ ሰዎች እንኳ) እንዲሁም የህክምና እርዳታ አለማግኘትን ያስከትላል፡፡

እንዲሁም በዲፕረሽን ምክኒያት የሚመጣውን መከፋት ለመሸፋፈን ወይም ለመቋቋም አልኮልና እና

ሌሎች ሱስ አምጪ ነገሮችን አብዝቶ መጠቀም፣ ቁማር አብዝቶ መጫወት፣ ህይወትን ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ ማሽከርከር፣ ብስጩ መሆንና በቀላል ነገሮች መናደድ ያስከትላል፡፡

በተለይ ብስጩ መሆን ለቤተሰብ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡

የሚወዱትን ሰው ያጡ አንዳንድ ወንዶች ‘ጠንከር እንዲሉ’ እና ሀዘናቸውን እንዳይገልፁ የሚደረገው ክልከላ እርማቸውን እንዳያወጡና የተወሳሰበ ሀዘን (Complicated grief) ውስጥ እንዲገቡ ሲያደርጋቸው ያጋጥማል፡፡

አብዛኛው ዲፕረሽን ውጤታማ በሆነ መልኩ የሚታከም በመሆኑ ጥሩ ስሜት ካልተሰማ ወይም የፀባይ ለውጦች ካሉ ከአእምሮ ሀኪም ወይም ከስነ ልቦና ባለሞያ ጋር በመነጋገር መፍትሄ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአእምሮ ህመም ፆታ፣ ብሄር፣ የትምህርት ደረጃ ሳይለይ ሁላችንም ላይ ሊከሰት የሚችል፤ ውጤታማ ህክምና ያለው ህመም ነው፡፡


መልካም ጊዜ!

61 views0 comments
bottom of page