top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ጠቃሚ ምክር ለእርስዎ !


  • ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም:: ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ!

  • ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም:: ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!

  • ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም :: በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ!

  • አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም:: ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!

  • ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም:: በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!

  • ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም:: ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ!

  • ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም:: ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ

  • ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም:: ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ!

  • ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም:: ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!

  • ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም:: ምንም ቁም ነገር ሰትሳራ አትሙት ማለት እንጂ!

  • ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም:: ልብህን ጊዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈህ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!

  • እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነት ተናገር ማለት አይደለም:: ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት እንጂ!

  • አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትጋጭም ማለት አይደለም:: ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!

  • ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም:: ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!

  • ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክ ነህ ማለት አይደለም:: አምሮብሃል ማለት እንጂ!

  • አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም:: ብልህ ሁን ማለት እንጂ

225 views0 comments

Recent Posts

See All
bottom of page