top of page
  • Writer's pictureየመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

ጠጠር እና ተራራ (ኢዱና አህመድ)

Updated: Feb 10, 2021



https://en.meskanmedia.com/post/%E1%8C%A0%E1%8C%A0%E1%88%AD-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%89%B0%E1%88%AB%E1%88%AB-%E1%8A%A2%E1%8B%B1%E1%8A%93-%E1%8A%A0%E1%88%85%E1%88%98%E1%8B%B5

በጠጠር የሚመሰል አቅምና ጥረት ይዘህ እንደ ተራራ የገዘፈ አቅምና ጥረት ካላቸው ጋር አትጋፋ:: ነገር ግን ከተራራው በመጠን እጅጉን የምትለያዩ ቢሆንም እንኳን እራስህን ከተራራው ጋር ካጣበቅህ ወይም የተራራው አላማና እቅድ የሚስማማህ ከሆነ ወይም እራስህን ከተራራው ጋር እንዲስማማ አድርገህ ካዘጋጀኸው ከተራራው ልትቀራረብና ልትመሳሰል ከመቻልህ በላይ ቀስ በቀስ ከተራራው አናት ላይ የመሆን እድልህ የሰፋ ነው የሚሆነው። ወይም ተራራውን ተራራ ካስባሉት ጠጠሮች መካከል እንደ አንዱ ልትሆን የምትችልበት እድልህ የሰፋ ነው የሚሆነው። ታዲያ ወዳጄ አለማወቅ እና አለመቻል በራሱ ወንጀልና በደል አይደለምና ያላወከውን ልትጠይቅና የተሻለውን ልተከተል የግድ ይልሃል። የሚጠበቅብህ የተሻለውን ሃሳብ ለመቀበል እራስህን ማዘጋጀት ብቻ ነው። ምን መሰለህ ወዳጄ ሁሌም ቢሆን የተሻለው ደህና ሃሳብ አንተን ወደ ከፍታው ማማ ሊያፈናጥጥህ ስለሚችል መቀበሉንና መከተሉን እንደ መርህ በመወሰድ እና የተሻለውን አካልን ደግሞ በእቅፍ ተቀብለህ እንዲመራህ ልትፈቅድለት ይገባል። ሌላው ወዳጄ በተሻለው አካልና ሃሳብ መመራት ስልጣኔ ቢሆን እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። በተጨማሪም በተሻለው ሃሳብ እና አካል በመመራትህ ወይም በመበለጥህ ያነስክ መስሎህ ከታየህ ዛሬ ላይ ሆነህ መኪናና ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀም አልነበረብህም። ለምን ቢባል ተንቀሳቃሽ ስልክ እና መኪና እንዲሁም በርካታ የምንገለገልባቸው ቁሶች ከአንተ እና ከእኔ በተሻለው ሃሳብ እና አካል የተሰሩ ናቸውና።

ለአቅም መለኪያ ጠጠር እና ተራራ ለምን ብሎ የሚጠይቅ ጨዋና ብልህ ከተገኘ? አዎን… ወዳጄ የሰው ፍጡር ሆኖ ሁሉንም ያወቀ በራሱ የበቃ እና የተብቃቃ ካለመኖሩ ባሻገር እንደ ሰው እኩል ቢሆንም አቅሙ ግን የተለያየ ነው። ታዲያ መለያየቱ ወይም መበላለጡ ካለ የአቅም ደረጃው መኖሩ ደግሞ እሙን ሲሆን ተራራ እና ጠጠር የሚለው ከእዛ የመነጨ ተደርጎ ቢወሰድ መልካም ነው። ታዲያ… በጣም ብዙ ጠጠሮች ተሰባስበው በአካል የገዘፈ ተራራን መፍጠር ቢችሉም ብዙ ደደቦች (ከይቅርታ ጋር) ቢሰባሰቡም ወይም የብዙ ደደቦች ሃሳብ ቢሰባሰብ የአንድ አዋቂ እና ጠንካራ ግሰለብ አቅምን ሊተካ አይችልም።

አቅምህን አውቀህ እና የሌላውን አቅም ከግንዛቤ ውስጥ አስገብተህ ተቀባብሎና ተከባብሮ መኖሩ የግድ ይልሃል። ጠጠሩ ወዳኜ ሆይ ይህ የማይሆን ከሆነ በተራራው ተጨፍልቀህ እና ተውጠህ መኖር ወይም መጥፋት ይሆናል መጨረሻህ።


በኢዱና አህመድ

ሪያድ ሳኡዲ አረቢያ

108 views0 comments
bottom of page