የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

Mar 18, 20191 min

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች (ክፍል - 04)

19. እመክርህ ነበረ መች እሺ ትላለህ

ሀሳብህ ብዙ ነው መንገድ ታበዛለህ

መተማ ለመዝመት አሁን ትሄዳለህ

(መመልስክን እንጃ እዛው ትቀራለህ)

በድርቡሽ ጎራዴ ራስህን ታጣለህ::

20. አንድ ዓመት ሲቀረው ምኒልክ ሊነግሥ

አላህ መተማ ላይ ይስላል መቀስ

በደም አጨማልቃ የምትቆራርስ

እራስ የምትቆርጥ ያውም የንጉሥ

አንደዜ ተመታች የማታላውስ::

21. አራት ወር ሲቀረው ምኒልክ ሊነግሥ

በመተማ በኩል ትጨሳች ጭስ

ጭሷ በራስ ገብታ (የምታስነጥስ) ትጨርሳለች ጭስ

እጅግም አትበጀው ለአጼ ዮሐንስ

አላህ ሽቶበታል አንገቱን ሊቀምስ::

22. እውቀትም የላቸው አሉን ጥንብ እርኩስ

ብለው ሰደቡን ደብተራና ቄስ

ሄጄ ልናገረው ለአጼ ዮሐንስ

ፈርጀለት ነበር መቅደላ ሲፈርስ

እንዴት የነቢ አሽከር ይሆናል እርኩስ?

23. የሰማም ያልሰማም ያልቅስ

መች እኔ እፈራለሁ ደብተራና ቄስ

መተማን ድል አድርጎ እሱ ቢመለስ

እንግዲህ የኔ ጫት ጥንብ ናት እርኩስ?

መተማ ካልሄደ እኔም ጫት አልቀምስ::

    200
    0