የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ

Apr 20, 20191 min

"ሕይወት ቅኔ"

Updated: Jun 9, 2019

ሕይወት ማለቅ ቅኔ

ለእኔ ማለት የእኔ::

ወይም ሕይወት ሞፎ

የእኔነት ቀፎ::

በራሴ ውስጥ ያለ ያገር ፍቅር ወኔ

ባህል ኪነ ጥበብ ማህሌተ ቅኔ::

በመብላት … በማግሳት … ሕይወት ከታመነ

ጓዱ በዓለም የለም አካሉ ካልሆነ::

ካለዚያም መቀመጥ … መወዘፍ በሶፋ

ከሆነ የሕይወት እሷነት ይጥፋ::

ወይም እኔነቴ በእኔ ዘንድ አይኖርም

ወደ ኋላ አይሔድም … ወይ ወደላይ አይበርም

እሱም … እኔም … ግጥሜም ..

እንድንቆይ ባንድ ዕድሜ

እኔ ግጥም ልጻፍ … ታግሎ ይኑር ግጥሜ

ካሊያ ግን አልገፋም ኑሮን በዝም ትርጉም

ኑሮ እራሷ ትሁን የረከበች እርጉም

ሕይወት ከነምኗ . . .

ትበል እልም … ድርግም

አያልነህ ሙላቱ ‹‹ከድጡ ወደ ማጡ! የግዛተ -

ደርግ ግጥሞቼ ፲፱፻፷፰-፹፪›› (2004)

    390
    0