አላማችን

 የማህበረሰባችን ታሪክ ፣ ቋንቋ ፣ ባህል እንዲሁም እሴቶች ጠፍተው  እንዳይቀሩ አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር መረጃዎችና ማስረጃዎችን ለተተኪው ትውልድ እንዲተላለፉ ማድረግ ነው። በተጨማሪም የስነ ፅሁፍና ስነ ግጥም ክህሎት ያላቸውን የማህበረሰባችን አካላት እና ለደጋፊዎቻችን ኢትዮጵያውያን የማበረታታት፣ ድጋፍ የማድረግ እንዲሁም ስራቸው ለሚድያ እንዲበቃ ጥረት እናደርጋለን።

አላማችን ፍፁም ሰላማዊ ፣ ያለተዛባ እና ከወገተኝነት የፀዳ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ማድረስ ብቻ ነው። በተወሰነ መልኩ ከስያሜያችን በመነሳት የማህበረሰባችን ጉዳዮችን የማጉላቱ ስራ የምንሰራ ሲሆን እላይ ከተጠቀሱት ልናከናውናቸው ካቀድናቸው ነጥቦች ጎን ለጎን አብሮ የሚሄድ ይሆናል። 

ስለ እራሱ የሚያውቅና የሚያሳውቅ ፣ እራሱን የሚወድና የእራሱ የሚወድ እንዲሁም እራሱን የሚያከብርና የሚያስከብር በሌሎች ላይ ወሰን ያልፋል ወይም የሌሎች ድምቀትና ፍካት አይገነዘብም የሚል እምነት የለንም ። እራስን መውደድና እራስን ማክበር የፍቅር መጀመሪያ ነው። ፍቅር ካለ ደግሞ ሁሉም አለ። 

Copyright © 2018 Meskan Media Network - All Rights Reserved. E-mail : meskanmedia@gmail.com

  • YouTube - White Circle
  • White Spotify Icon
  • White Apple Music Icon
  • White Amazon Icon
  • White Facebook Icon
  • Twitter Clean