የመስቃን ብዙሃን መገናኛ አውታረ መረብ
ጥቅስና አባባሎች

ሁለት ጊዜ ነው የዶሮ ልደት አንዱ በእንቁላል ሌላው በጫጩት።
ሆዴ በጀርባዬ ቢኾን ገፍቶ ገደል በጣለኝ።
ሆደ ሰፊ ይሻላል ከአኩራፊ።
ሁለት አይወዱ ከመነኾሱ አይወልዱ።
ሀብታም ለሀብታም ይጠቃቀሱ ደሃ ለደሃ ይለቃቀሱ።
ሁለተኛ ጥፋት ቆሞ ማንቀላፋት።
ሁሉ ሆነ ቃልቻ ማን ይሸከም ስልቻ።
ልብ ካላየ ዐይን አያይም።
ሁሉም ከኋላው ያገኘዋል እንደ ስራው።
ሀብታም በገንዘቡ ደሃ በጥበቡ እርስ በእርስ ይቀራረቡ።
ሁሉን ቢናገሩ ሆድ ባዶ ይቀራል።
ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም።